ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ ሚያዝያ 2006 / April 2014 / እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 08 | Page 10

በዚሁ ጽሑፋችን አንስተናል። ተገናኝተው እነሱ ሰለካሄዱት ወጎችም ከብዙ በጥቂቱ ጠቅሰናል። ይህ ደግሞ ከገባንበት ላበሪንቱ ለመውጣት በሚደረገው ጥረትና ሙከራ ትንሽ የተስፋ ጭላንጭል የሚያሳይ ይመስለናል። ፖለቲካና የፖለቲካ መፍትሔዎች በንግግር እንጅ በጡንቻ አይፈቱም። ድል አድራጊውም ይመስለዋል እንጂ ድሉ ቋሚ አይደለም። ሁሉ ነገር ይቀየራል ። ይለወጣል። ይሻሻላል። ያልፋል። ሰውም ይሞታል አዲስ ነገርም ይበቅላል። ከጨለማ በሁዋላ የጸሃይ ብርሃን ቦግ ይላል። ጥያቄው ዱሮም አሁንም በምን አይነት ሥርዓት ውስጥ በእሱም ሥር እንኑር የሚል ነው? ሰው ሰይጣን ነው። ሰይጣንም ሰው ነው። ሁሉ ሰው ግን ሰይጣን አይደለም። በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረ ማንም መብቱን የማይረግጠው ነው። መልካም ንባብ። ይልማ ኃይለ ሚካኤል ዋና አዘጋጅ —- —- ለ አእምሮ ሚያዝያ 2006 / April 2014 / እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 08 ~ 10 ~