ለ አእምሮ / Le'Aimero ለ አእምሮ ልዩ እትም / ታህሳስ/ጥር 2006 / 01 / 2014 – አዲስ ዓመት | Page 16

በፖለቲካ ቲዎሪ አንጻር -የኢኮኖሚ ቲዎሪውን ለጊዜው ቦታው ስለ አልሆነ እንተው- የሰው ልጆችን የመናገር የመጻፍ የመመራመር የመተቸት የመፈላሰፍና የመቃወም …. ሰበአዊ መብትን የሚያውቅና የሚቀበል እንድ ሕብተረሰብ ቢኖር ይህ እኛ በዓይናችን የምናየው -ብዙዎቹ ተሳስተው የሚሉት – የቡርጁዋ ! …የለም በትክክል ለመናገር የምዕራቡ የሊበራሉ ዲሞክራቲክ ሕብረተሰብ ብቻ ነው። ቻይና እንደ ሌኒንና የስታሊን ራሺያ ይህን ዛሬማድርግ አትፈልግም። የምዕራቡሕብረተሰብከድንበሩ አልፎ ለእኔና ለአንተ / አንቺ መብት ይቁም አይቁም፣መቆም አለበት የለበትም የሚለው፣ …ይህ መቼም አሁን ሌላ ጥያቄ ነው። ጥያቄው!ዋናው ጥያቄ አንተ እራስህ ምንታስባለህ ነው? ምን ዓይነት የፖለቲካ ሥነ-ሥርዓት ነው አንተ/አንቺ የምትፈልገው/ጊው? የሚለው ነው። ወሳኝ ጥያቄው! ጨዋታው ያለው „እኛ ምን ዓይነት ሥርዓት እንፈልጋለን? „ የሚለው ግልጥ የሆነ ጥያቄ ላይ ነው። ታሪክ ደግሞ በበቂ ለጥያቄው መልስ ሰጥታበታለች። —— ይልማ ኃይለ ሚካኤል —————