Literary Arts Magazine Spring 2016 | Page 63

Poetry

ቢዘጋም ቁልፍ አለ

By Kedija Manora , ESL 7

ገና ምድሪቷን የረገጥኩኝ እለት ፣ ህልሜን አጣሁት ካኖርኩበት ፣ የምናገረው አይገባቸው ፣ የሚናገሩትን አለሰማቸው ፣ እኔም በሁኔታው ግራ ተጋብቼ ፣ ዋ ! ጊዜ !... ይላል ያገሬ ሰው ፣ እኔማ ባገሬ እባል ነበር ልሳነ ክሌ ፣ ታዲያ ! ምን ያደርጋል ፣ ነበር ነበርን ትቶ ያልፋል ታዲያ የኔን ግራ መጋባት የተመለከተ አንድ ወዳጄ ፣ አይዞሽ ግራ አይግባሽ ፣ ቢዘጋም ቁልፍ አለ !
ለአንደበትሽ መፍቻ ፣ ለማንነትሽ መግለጫ ፣ ትምህርት አለና ከወደ ካርሎስ ፣ በፍፁም ስጋት አይግባሽ ፣ ብሎ መንገድ ቢያመላክተኝ ፣ እኔም የሸከፍኩትን ጓዜን አኑሬ ፣ ብዕሬን ይዤ ገሰገስኩ ፣ አንደበቴን ለማላቀቅ ስለቸኮልኩ ፣ ታዲያ ምስጋና ይግባውና ለዚያ ለወዳጄ ይሄው ዛሬ 3 ፣ 4 ፣ 5 ፣ 6 እያልኩ ፣ ደርሻለሁ ከሰባት ፣ እውነትም ቢዘጋም ቁልፍ አለ ፣ ለማይከፈለው የ / ት ቤቴ ውለታ ፣ እስኪ ላመስግን በብዕሬ ላንዳፍታ !
In Our Own Words 2016 59