Literary Arts Magazine Spring 2012 | Page 117

Amharic ለመጀመሪያ ዕትም ጋዜጣችሁ፣ እንዲህ ብዬ የምላችሁ፣ በትክክለኛ ፋና ዕዉቀት ጐዳና ላላችሁ፣ የደረጃ ስድስት ተማሪያችሁ፣ ጥሩኝ ዓለማየሁ ዋቻሞ ብላችሁ፣ መልካም አስተማሪ ጋዜጣ ትሁንላችሁ:: አረ ጐበዝ በርታ፣ በምንም ነገር ሳትረታ፣ ሰው ትሆናለሀና አታመንታ፣ በትምህርት ነውና የሚገኘው እመርታ፣ በርታ በርታ በርታ በርታ፣ አንድ ቀን ደርሰህ ታቀልጣለህ እልልታ፣ ዕውነት ነው ጊዜህን ሰውተህ ነው የምትማረው፣ የማይካድ ሀቅ ነው ትልቅ ውሳኔ ነው የወሰንከው፣ ከበረታህ ካለፍህ ይህን ቀን በድል ተጠናቆ ስታየው፣ የዚያኔ ነው የቀለም ጀግንነትህን የምታስመሰክረው:: ካርሎስ ሮዛሪዮ ዓለም አቀፍ የቋንቋ ትምህርት ቤታችን፣ የወደፊት ትልቁን ራዕያችንን በስርዓት ማሳኪያችን፣ በሰሜን አሜሪካ ዋና መናገሻ በሆነችው ዲሲ ተከፍቶልን፣ ደረጃ የጠበቁ ስመ ጥሩ መምህራን ተመድበውልን፣ የጥራት ቁጥጥሩ ተደርጐ በዚህም ዓመት አለፈለን፣ ለሚቀጥሉት ሰባት ዓመታት እውቅና አገኘልን፣ ለዚህም በድጋሚ እንኳን ደስ ያለን:: በሉ ደህና ሁኑ በሚቀጥለው እትም እንገናኝ የምላችሁ፣ ባለፈው መንፈቅ የደረጃ ስድስት ተማሪ ጓደኛችሁ፣ አሁን ከእናንተ ጋር ወደ ደረጃ ሰባት ያለፍኩላችሁ፣ በውጤቴም አስተማሪዬንና ተማሪ ጓደኞቼን አስደሳቺያችሁ:: Alemayehu Kabisso From: Alemayehu Wachamo Kabisso Teacher: Chirs Ladd, Level 6, AM 117 By Victoria Nwankwo. Digital Photography. እንኳን ደስ ያላችሁ፣ Teacher: Krisy Li Puma, Digital Photography Extra Curricular (Spring) በቋንቋችን