Christian Books & Magazines - Free Berea Magazine 5 | Page 9

አሁን ከምንነጋገርበት ርእሰ ጒዳይ የተለየ ቢሆንም ጳውሎስ ሲናገር “ አሁን ጠግባችኋል ፤ አሁን ባለጠጋ ሆናችኋል ” ይላል ( 1ቆሮ 4 ፥ 8 )። “ ጠግባችኋል ” ሲል “ ልባችሁ አብጧል ” ማለቱ ሳይሆን “ ሙሉ ሆናችኋል ” ማለቱ ነው ። እግዚአብሔር እንዲመረምረን መፈለግ ትልቅ ነገር ነው ። ነቢዩ እንዲህ ብሎ ይጠይቃል ፤ “ ምን ይዤ ወደ እግዚአብሔር ፊት ልምጣና በልዑል አምላክ ፊት ልስገድ ? የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የአንዱን ዓመት ጥጃ ይዤ በፊቱ ልምጣን ? እግዚአብሔርስ በሺህ አውራ በጎች ወይስ በእልፍ የዘይት ፈሳሾች ደስ ይለዋልን ? ወይስ የበኲር ልጄን ስለ በደሌ የሆዴንም ፍሬ ስለ ነፍሴ ኀጢአት እሰጣለሁን ? ሰው ሆይ ፤ መልካሙን ነግሮሃል ፤ እግዚአብሔር ከአንተ ዘንድ የሚሻው ምንድር ነው ? ፍርድን ታደርግ ዘንድ ፤ ምሕረትንም ትወድድ ዘንድ ፤ ከአምላክህም ጋር በትሕትና ትሄድ ዘንድ አይደለምን ?”( ሚል6 ፥ 6-8 )።
እስከ አሁን ድረስ የተባለውን ነገር ለመጠቅለል እንሞክር ። የብልጽግና ወንጌል ምንድን ነው ? ሰዎች የወንጌሉን ኢየሱስ መስበክ ትተው ለሰዎች ጆሮ የሚጥም ነገር የሚሰብኩት ለምንድን ነው ? እነዚህ ጥያቄዎች ሙሉ ትንተና የሚሹ ጥያቄዎች ናቸው ። ሆኖም አጭሩ መልስ በምድራዊው መመዘኛ ስለተወረሱና እንደ አሜሪካን ኮርፓሬሽኖች “ የሥሥት ” መንፈስ ስለወረደባቸው ነው ። የብልጽግናን ወንጌል የሚሰብኩ ሰዎች የኢየሱስ
ወንጌል ጨርሶ አልገባቸውም ። የወንጌሉ ጭብጥ ምን እንደሚያስተምርና ኢየሱስ ለምን ዓላማ ወደዚህ ምድር እንደ መጣ ከቶ አልገባቸውም ። ኢየሱስም ሆነ ሐዋርያቱ ስለ ብልጽግና አላስተማሩም ። ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ተልኮ የመጣው ሰዎችን ሊያበለጽግ ሳይሆን ሰዎችን ከእግዚአብሔር ሊያስታርቅ ነው ። ከዚህ ጭብጥ መራቅ ከእግዚአብሔር ሐሳብ መራቅ ነው ። ዛሬ ሰዎች የሚበለጽጉበትን መንገድ ብንመለክት በእውነተኛው ይዘገንናል ፤ ይሰቀጥጣል ። ከአሜሪካን ኮርፖሬሽኖች መካከል ብዙዎቹን ለምሳሌ ብንወስድ ትርፋማነታቸው የተመሠረተው በጉልበት ብዝበዛና በሥሥት ስሌት ላይ እንደ ሆነ ብዙዎች ይናገራሉ ( በ2008 ተከስቶ የነበረውን ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ልብ ይሏል ፤ ሥሥትና ቀቀት የወለደው ቀውስ ነበር )። 6 አያሌ ኮርፖሬሽኖች ፋብሪካዎቻቸውን ከአሜሪካ ነቅለው ወደ ምሥራቅ አገሮችና ወደ ላቲን አሜሪካ አገሮች አሁን ደግሞ ወደ አፍሪካ አገሮች የሚወስዱት ይበልጥ ትርፋማ ለመሆን ነው ። ትርፍ ማግኘት በራሱ ወንጀል አይደለም ። በብዝበዛ ላይ የተመሠረተ ትርፍ ግን ወንጀል ነው ፤ በደል ነው ። ሰዎች ድሀ ስለሆኑ ብቻ መበዝበዝ የለባቸውም ። ድህነት ነውር አይደለም ፤ ብዝበዛ ግን ከነውርም ነውር ነው ። እንደሚባለው ከሆነ ሰዎች ከምንጊዜውም ይልቅ ድሀ እየሆኑ የመጡት ኢፍትሐዊ ሥርዐተ ማኅበር በመስፈኑ ነው ። በመደብ ፣ በዘርና በብዝበዛ ላይ የተመሠረተ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ሥርዐተ ማኅበር ያደኸያል ፤
እርስ በእርስ ያቆራቁሳል ። እናም ጥቂት አገሮችና ጥቂት ግለሰቦች ብቻ እየበለጸጉ

የብዙ ብልጥግና

መሠረቶች ብዝበዛ ፣ ሙስናና ዝምድና እንደ ሆኑ ማንም አይክድም ።

ብዙዎች የሚደኸዩት ለምንድን ነው ? በማለት መጠየቅ ይኖርብናል ። ፍትሕ ሲጠፋ ብዝበዛ ይሰፍናል ። ነገር ግን በብዝበዛ ላይ የተመሠረተ ትርፋማነት በማንኛውም መመዘኛ “ ስኬት ” ሊባል አይችልም – ቅልጥጥ ያለ ዝርፊያና ቅሚያ እንጂ ። በዚህ ዐይነት መንገድ የሚገኝ ሀብት ክርስቶሳውያንን ሊያጓጓ አይገባም ። በንጹሕ ላብ የሚገኝ ትርፍ እንዳለ አይካድም ። እግዚአብሔር የእጃችንን ሥራ ከባረከ እርሱ ይበቃናል ። ዓለማዊው ፋይዳና መመዘኛ እንዳይወርሰን መጠንቀቅ ይገባናል ። በነቢያቱ ዘመን በሐሰተኛ ሚዛን እየሸጡ የበለጸጉ ( ሆሴ 12 ፥ 8 ) ወይም ሰዎችን ለባርነት እየሸጡ የበለጸጉ ( ዘካ 11 ፥ 5 ) እግዚአብሔር የባረካቸው ይመስል ምስጋና ሲያቀርቡ ነበር ። እግዚአብሔር ግን በድርጊታቸው ከመሳለቅ በስተቀር ከንቱ ውዳሴአቸውን አልተቀበለውም ። ይህ የሚያሳየው ብልጽግና የመባረክ ምልክት አለመሆኑን ነው ። 7
ቤተ ክርስቲያን የዓለም ፍልስፍና የሚስተጋባባት መድረክ እንድትሆን መፍቀድ ትልቅ ስሕተት
4 ከዚህ የሚከተሉትን መጻሕፍት ያነቧል ፤ Jonathan Tasini , The Audacity of Greed : Free Markets , Corporate Thieves , and Looting America ( 2010 ). Kenneth R . Gray , Corporate Scandals : The Many Faces of Greed ( 2005 ). Arianna Huffington , Pigs at the Trough : How Corporate Greed and Political Corruption are Undermining America ( 2009 ). 5 Bradley A . Koch , The Prosperity Gospel and Economic Prosperity : Race , Class , Giving , and Voting ( Indiana University : PhD
Diss , 2009 ) 14-21 . 6 Richard N Longenecker , Galatians , WBC ( Dallas : Word Bokks ) 133-134 . እንዲሁም F . F . Bruce , The Epistle to the Galatians , NIGTC ( Grand Rapids : Eerdmans , 1990 ) “ who has hypnotized you ?” 148 . Marion L . Soards and Darrell J . Pursiful , Galatians , SHBC ( Georgia : Smyth & Helwys Publishing , 2015 ) 120-121 .
9