Christian Books & Magazines - Free Berea Magazine 5 - Page 54

የሚለጥፉትን አይተውና አንብበው ከመጽናናት ይልቅ በቅናትና በብስጭት ራሳቸውን ለአላስፈላጊ በቀልና ከማን አንሼ አይነት ውድድር የዳረጉ ብዙ ናቸው። በዚህ በፌስ ቡክ ወንጌልን ለማስፋፋት የሚሞክሩ ጥቂት ሰዎችን ባውቅም አብዛኞቻችን ግን የቀናችንን ዋናና ሰፊ ጊዜ የምናባክነው በዚህ መሆኑን ስናስብ መጨረሻችን ያስፈራል። ክርስቲያኑ ሕብረተሰብ ኢንተርኔትና ሶሻል ሚዲያዎችን በአግባቡና ራሱን በመግዛት ከተጠቀመበት ልክ እንደ መድኀኒቶች ጥቅሙ የትየለሌ ነው። ነገር ግን አጠቃቀሙ ላይ ራስን መግዛት ይጠይቃል። ኢነተርኔትን ካላግባብ ለረጅም ጊዜ ከተጠቀመ ወይም አልጠቀምም ቢል ደግሞ ጉዳቱ ትልቅ ነው። 5.ጊዜ ማባከን:- በኢነተርኔት ስለሚጠፋው ጊዜ ከላይ እንዳነሳሁት ብዙ ሰዎች በቀን ውስጥ ከሁለት እስከ አራት ሰአት የሚሆን ጊዜአቸውን በኢንተርኔት ላይ የሚያሳልፉ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ግንባር ቀደሙን ስፍራ ይዞ ያለው ፌስ ቡክ ነው። በርካታ የህመም ማስታገሻ መድኀኒቶችን ሰዎች አለአግባብና ሳያስፈልጋቸው እየወሰዱ ሱሰኛና የመድኀኒቶቹ ጥገኛ እንደሚሆኑ ሁሉ በርካታ ሰዎች ኢንተርኔትንና ሶሻል ሚዲያን ከሚያስፈልገው መጠን በላይ እየተጠቀሙ የችግሩ ሰለባ ሆነዋል። ነጻ ኢንተርኔት በየስልኮቻችን ውስጥ ስላገኘን ብቻ 24 ሰአት ካላግባብ ከተጠቀምንበት ሕይወታችንን የሚያቀጭጭና የሚገድል መርዝ ነው። ክርስቲያን ከዓለምና ከአለማዊነት ተለይቶ ሀጥያትንና ሐጥያታዊ ምኞትን የሚክድ መሆን አለበት። ሰይጣን የሚያዘጋጅልንን ወጥመድ ማለፍ ከቻልን ዓለምና ስጋ የሚያዘጋጁልንን የኢንተርኔት ሱሰኛ መሆንን ማለፍ አንቸገርም። ሁሉን ሚዛኑን በጠበቀ መንገድ ልናደርገው ይገባናል። በቀን ውስጥ ብሩህ ሆነን በንቃት ስራችንን መስራት የምንችልበትን ወርቃማ ጊዜ በፌስ ቡከ ማባከንና በዘመን መቀለድ እየተለመደ የመጣ የኢንተርኔት ውጤት ችግር ነው። ጌታችን በመጣ ጊዜ ሲተጉ የሚያገኛቸው ባሪያዎች ብፁአን እንደሆኑ ቃሉ ይናገራል። እንግዲህ ጌታ በመጣ ጊዜ ፌስ ቡክ ላይ እንዳያገኘንና ስለስንፍናችን እንዳይዘልፈን እንፍራ። በሕብረተሰቡና በቤተክርስቲያን ላይ አለማዊነትን፣ የሞራል ውድቀትንና የልፍስፍስ ክርስትና መሰረታዊ ምክንያቱ ቴክኖሎጂው ሳይሆን እኛ ስለ ቴክኖሎጂ ያለን የተሳሳተ አስተሳሰብና አጠቃቀማችን ነው። ቴክኖሎጂን በመጠቀምና ባለመጠቀም መሀከል ያለው ልዩነት አንድ ሐኪም ያዘዘልንን መድኀኒት በመውሰድና ባለመውሰድ መሀከል ያለውን አይነት ነው። አንድ ሰው ህይወቱን አደጋ ላይ በሚጥል ህመም ቢታመምና ሀኪም ለበሽታው መድኀኒት ቢያዝለት መድኀኒቱን በታዘዘው መሰረት መዋጥ ይጠበቅበታል። ከታዘዘለት በታች ቢወስድ ወይም አልወስድም ቢል ህመሙ እስከሞት ሊያደርሰው ይችላል። ከታዘዘለት መጠን አብዝቶ መድኀኒቱን ቢወስድ ደግሞ መድኀኒቱ መድኀኒት መሆኑ ቀርቶ በሰውነቱ ውስጥ መርዝ ይሆንና ይገለዋል። ለዚህ በሽተኛው ሰው የሚበጀው የታዘዘለትን መድኀኒት በመጠኑና በሰዓቱ መውሰድ ነው። 54 ቴክኖሎጂን እንደመገልገያ መሳሪያ ብቻ አድርገን ከወሰድነውና ከተገለገልንበት ከጉዳቱ ይልቅ ጥቅሙ ያመዝናል። ቴክኖሎጂን ከመጠቀሚያ መሳሪያነቱ ባለፈ የሕይወታችን መሰረትና ቀዳሚ አድርገንና እስትንፋስ ሰጥተን እንደጉዋደኛና የቅርብ አማካሪ ወደማድረግ ስንመጣ በሕብረተሰባችን ላይ አሁን የምናየውን ጉዳት እንደሚያስከትል ልንክደው አንችልም። በመጨረሻም፣ በኢሜል፣ በስልክ ቴክስ