Christian Books & Magazines - Free Berea Magazine 5 | Page 53

የዘመኑን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ሰዎችን ለማስደመም የምታደርገውን ጥረት እውነተኛ ወንጌልን ከማስፋፋት ይልቅ ውድድርንና የታይታ ሕይወትን አስፋፍቶአል ይላሉ ። ሲታይም የቤተክርስቲያን አባላት በቁጥር እየበዛን ቢሆንም በሕይወት ጥራትና እውነተኛ ደቀ መዝሙርነት እየዘቀጥን ያለንበት ዘመን ነው ። ቤተክርስያን የዘመኑን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ሰዎችን ለመሳብ እያደረገች ያለው ጥረት ቁጥር ላይ እንጂ ጥራት ላይ ያተኮረ ስላልሆነ የለብታ ሕይወትን እያስፋፋ ነው ። ሰዎችን ወደ ሕይወት የሚጠራ በጸሎትና በእምነት የጠላትን አሰራር እያፈረስን መንፈስ ቅዱስ በሰዎች ልብ ስለሀጢያታቸው እንዲወቅስ በመጋበዝ መሆኑ ቀርቶ ቤተክርስቲያን በዘመኑ ያለው ቴክኖሎጂና ኢንተርኔት ላይ መደገፍዋ ለዚህ የተፍረከረከና የለብታ ሕይወት እንደዋና ሰበብ የሚጠቀስ ነው ።
ቴክኖሎጂ በክርስትና ላይ ያለው ሌላው ችግር አማኞች ሕይወታቸውንና ወሳኝ የሆኑ የቀኑን ጊዜአቸውን ለቴክኖሎጂና ኢንተርኔት መስዋእት አድርገው በማቅረብ ለሌሎች በሕይወታቸው መሰረታዊ ለሆኑ ጉዳዮች ወደሁዋላ መቅረታቸው ነው ። ሰዎች ላመኑበት ነገር ደም በማፍሰስ ፣ ገንዘባቸውን በመስጠትና ጊዜአቸውን በመሰዋት ታማኝ ሎሌ መሆናቸውን
መግለጽና ማምለክ የተለመደ ነው ። ማንኛውም በሕይወታችን የሚመጣ መስዋእትን የሚጠይቅ ነገር አምልኮና ሐጢያት ነው :: በሚቺጋን ዩኒቨርሲቲ በተደረገ ጥናት የሕብረተሰብ መረጃ መረቦች ( ሶሻል ሚዲያ ) ሰዎችን ጸረ- ሶሻል አድርገው ለብቸኝነትና ስር የሰደደ ድብርት ( ዲፕሬሽን ) እየዳረጉ ይገኛሉ ። ጥናቱ እንዳመለከተው ሰዎች በፌስ ቡክና ሌሎች የሶሻል መረጃ መረቦች የሚያሰራጩት ስኬታቸውንና ያሸነፉትን የህይወታቸውን ክፍል ብቻ ስለሚሆን ሌሎች ይህንን ሕይወት ሲመለከቱ ከራሳቸው ሕይወት ጋር በማወዳደርና እያለፉበት ያለውን አስቸጋሪ ጎዳና በማማረር የበታችነትና የመጉደል ስሜት እንዲሰማቸው ማድረጉ ነው ። ቤተክርስቲያኖችም በቴሌቭዥንና በኢንተርኔት በሚያደርጉት ስርጭት አውነተኛ ወንጌልን ከማሰራጨት ይልቅ ለታይታና ለውድድር የሚያደርጉት ጥረት እየበዛ መሄዱ የሚጠቀስ ነው ። በዘመናችን እንደምናየው አንዳንዶች ራሳቸውን እንዲሁም የማገልገል ችሎታቸውንና ብቃታቸውን የሚያስተዋውቁበት መድረክ ሆኖአል ።
በአጠቃላይ ኢንተርኔት በክር ስቲያኑ ላይ እያስከተለ እንዳለ ከሚገለጡ ችግሮች መሀል የሚከተሉት ይገኙበታል : 1 . ሰዎች ራሳቸውን ከሕብረት
መለየትና ብቸኛ ማድረግ ። ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከመጠን ያለፈ የኢንተርኔት ሱሰኛ መሆን ለሀዘንና እንደ ዲፕሬሽን ላሉ ዘላቂ በሽታዎች እንደሚያጋልጥና በኢንተርኔት ሱሰኛ የሆኑ ሰዎች በመሀበረሰቡ ውስጥ ያላቸው ድርሻ የበዛ እንደሆነ ይናገራሉ ።
2 . ሱሰኛ ማድረግ ፡ ስለሱሰኛነት ስናነሳ ሰዎች ቶሎ የሚያስቡት ርኩሰትን ( ፖርኖግራፊን ) እና የመሳሰሉትን ስለሚመለከቱ ወንዶች ብቻ ቢሆንም ማንኛውም አእምሮአችንን የተቆጣጠረ ነገር እኛን ባሪያዎች እንዳደረገንና እኛም የዛ ነገር ሱሰኛ እንደሆንን ማመን ይገባናል ። ለደቂቃ ስልካቸውን ሳይከፍቱ ቴክስት ሳያደርጉ ወይም የከረመ ቴክስት ደግመው ሳያነቡ መቀመጥ እስከማይችሉት ወጣቶች ጀምሮ ጠዋታና ማታ ከፌስ ቡክ ላይ እስከማታአጡአቸው ሰዎች ጭምር ሱሰኝነት ነው ።
3 . ስንፍና ። በዘመናችን እየታየ የመጣው አንዱ የኢንተርኔት ችግር ሰዎች ሳይሰሩና ሳይለፉ ምኞታቸውን እንዴት በቀላሉ መፈጸም እንደሚችሉ ማሰባቸው ነው ። ሰዎች አጠገባቸው ያለውን ስራ መስራትና በሚገባ መጠቀም ትተው ህይወታቸውን ለማያውቁት ሌላ ዓለምና ሌላ ሕይወት ባሪያ አድርገው ከኖሩ በርግጥ ባሪያዎች ናቸው ።
4 . ርኩሰትና የሀጥያት ልምምድ- ቴክኖሎጂዎች በተለይ ኢንተርኔትን በይፋ ሰዎች መጠቀም ከጀመሩ በሁዋላ ወንጀሎችና ሐጥያታዊ ልምምዶች እየሰፉ መጥተዋል ። በኢንተርኔት ወሲብ ከሚፈጽሙት ጀምሮ በኢንተርኔት ወሲባዊ ድርጊቶችን ማየትና መፈጽም ከመቼም በላይ እየበዛ የመጣበት ወቅት ነው ። በርካታ ክርስቲያኖችን በዚህ ዘመን ባሪያ አድርጎ ከያዘው ነገር አንዱ ፌስ ቡክና ዩ-ቲዩብ ነው ።
በፌስ ቡክ ገጻቸው ላይ ሌሎች
53