Christian Books & Magazines - Free Berea Magazine 5 | Page 52

ቴክኖሎጂ ወንጌልን ወዳላመኑት በቀላሉ ለማዳረስ፣ መንፈሳዊ ትምህ ርቶችንና ፕሮግራሞችን በማያመች ሁኔታ ላሉ ክርስቲያኖች ለማዳረስና ለማበረታታት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ይናገራሉ፡፡ የነዚህን ጽንፈኛ ሐሳቦች ምንነት ለማየትና ሀሳቦቹን አስታርቀን እንደክርስቲያን ልንወስደው ስለሚገባን አቁዋም ለማወቅ አስቀድመን ስለጥቅሙ ከዛም ስለጉዳቱ እንመልከት። ቴክኖሎጂ በተራቀቀበትና በ መላው አለም በተሰራጨባቸው ጥቂት አስርት አመታት ውስጥ ወንጌልን በዘመናት ታይቶ በማይታወቅ ፍጥነት ለማሰራጨት እንደረዳ ጥናቶች ይጠቁማሉ። በጌታ ቤት ያሉትን በእምነታቸው እንዲጸኑ በስልክ፣ በቴሌቭዥን፣ በ ሬዲዮና በመሳሰሉት የሚደረገው የወንጌል ስርጭት ጥቅሙ ከፍተኛ ነው። አሁን ባለንበት ዘመን ብቻ ሳይሆን በየዘመናቱ ቤተክርስቲያን የቴክኖሎጂ ቀዳሚ ተጠቃሚ እንደሆነች ታሪካችን ምስክር ነው። በ 14 ኛው መቶ ክፍለዘመን ተንቀሳቃሽ የህትመት ስራ ያስተዋወቀው ጀርመናዊው ዮሀንስ ጉተንበርግ ስራውን ሲጀምር ካሳተማቸው መጽሐፍቶች ውስጥ መጽሐፍ ቅዱስ ቀዳሚው ነበር። በ15ኛው መቶ ክፍለዘመን ዊሊያም ታይንደል የተባለ አሜሪካዊ መጽሀፍ ቅዱስን ወደእንግሊዘኛ በመተርጎም የህትመት ቴክኖሎጂ ቀዳሚ ተጠቃሚ ሆኖ ነበር። በ1644 ዓ.ም የእንግሊዝ ፓርላመንት የህትመት ስራ ሰዎች ሃሳበቸውን ያለገደብ በመግለጽ በህብረተሰቡ ላይ በተለይም በቤተክርስቲያን ላይ ጉዳት ያመጣሉ በሚል ምክንያት የህትመትን ስራ ባጠቃላይ ለማገድ ሞክረው እንደነበር ታሪክ ይመሰክራል። ከ500 በላይ አመታት ካለፈ በሁዋላ በዚህ ዘመንም ለቴክኖሎጂ በጎ ህሊና የለንም። በ1939 ዓ.ም ቲዮዶር ኤፕ የተባለው ሰው 52 “ወደቃሉ እንመለስ” የሚል የክርስቲያን ሬዲዮ ስርጭት ፐሮግራም ለመጀመሪያ ጊዜ ማሰራጨት ጀምሮ ነበር። በ1957 ዓ.ም ዶክተር ቢሊ ግርሀም የጀማ ወንጌል ማሕበርንና በቴሌቭዥን ወንጌልን ለአለም ማሰራጨት ጀምረው በሚሊዮን የሚቆጠሩ የአለም ህዝቦችን በወንጌል ደርሰዋል። በዘመናችን በመላው አሜሪካ ከ2000 በላይ አባላት ያሉአቸው ከ800 በላይ አብያተ ክርስቲያናት ያሉ ሲሆን የነዚህ አብያተ ክርስያኖች አገልግሎትና ህልውና በቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ ነው። ዋይክሊፍ በመባል የሚታወቀው የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ማህበር በሚመጡት 50 አመታት በቴክኖሎጂ በመታገዝ በዓለም ላይ ባሉ ቁዋንቋዎች ሁሉ መጽሐፍ ቅዱስን መተርጎም ይቻላል ብለው ያምናሉ። በ1993 ዓ. ም የመጽሐፍ ቅዱስ መግቢያ (Bible Gateway) የተባለው ድርጅት ለመጀመሪያ ጊዜ ነፃ የመጽሐፍ ቅዱስ ቅጂዎችን በኢንተርኔት የበተኑ ሲሆን አሁን ባለንበት ዘመን ከ 1000 በላይ መጽሐፍ ቅዱስና መጽሐፍ ቅዱስ ነክ የሆኑ አፕስ (APPS) መኖራቸውን ይናገራሉ። በሁለተኛ ደረጃ ቴክኖሎጂ በክርስትና ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እንዳለው የሚያምኑ ሰዎች እንደሚሉት ደግሞ ይሄ ሁሉ የቴክኖሎጂ እርዳታ፣ የወንጌል ስብከት፣ በስልኮቻችንና በኮምፒዩተራችን ላይ ያለው መንፈሳዊ ንባብና መንፈሳዊ መረጃ፣ በሶሻል ሚድያ የሚደረግ የወንጌል ስርጭት፣ ክርስቲያኑን ሕብረተሰብ ወደሚፈለገውና ወደሚጠበቅበት መንፈሳዊ ብስለትና እውነተኛ ደቀ መዝሙርነት ከማድረስ ይልቅ ቸልተኛና ግዴለሽ አድርጎታል ይላሉ። በኢንተርኔትና ሌሎች የ ቴክኖሎጂ ውጤቶች ወንጌልን ለመስማት በበዛልን መጠን የክርስቲያኖች ሕብረት፣ እውነተኛ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መረዳትና የወንጌል እውቀት ቀንሶአል በማለት ይሞግታሉ። ለምሳሌ በአሜሪካ ውስጥ በተደረገ ጥናት 70 በመቶ የሚሆኑ ዕድሜአቸው ከ18 እስክ 34 ዓመት ያሉ ወንዶች ቢያንስ በወር አንድ ጊዜ ወሲባዊ የሆኑ(ፖርኖግራፊ) ኢንተርኔት ክፍሎችን ይጎበኛሉ። ይህንን አሐዝ አሳሳቢ የሚያደርገው ደግሞ ከነዚህ ወንዶች ሀምሳ በመቶ በላይ የሚሆኑት ክርስቲያኖች ወይም ክርስቲያኖች ነን የሚሉ መሆናቸው ነው።(Jason King) በ2015 በተደረገ አንድ ጥናት በአሜሪካን ሀገር ከሚደረጉ የትዳር ፍቺዎች መሀል 85 በመቶ የሚሆነው ለፍርድ ቤት የሚቀርብ አቤቱታ መዝገብ ውስጥ ፌስቡክ ለትዳራቸው መሻከር እንደ እማኝ ተደርጎ ቀርቦአል። (Journal of Computers in Human Behavior) ለምሳሌ በፌስ ቡክ ከሌላ ወንድ ጋር ግንኙነት ጀምራለች፣ በፌስ ቡክ ከሴቶች ጋር ያወራል፣ በፌስ ቡክ የእከሊትን (የእከሌን) ፎቶ ለጥፎት አየሁኝ፣ የ