Christian Books & Magazines - Free Berea Magazine 5 | Page 49

የሚለው ትምህርት ስሕተት ከመሆኑም ባሻገር ነውረኛ አስተሳሰብ ነው ።
አዎንታዊ በሆነ ሁኔታ ማሰብም ሆነ መናገር አግባብነት ያለው ጒዳይ ነው ። ነገር ግን አዎንታዊ ዐዋጅ ፣ አዎንታዊ ውጤት ፣ አሉታዊ ዐዋጅ ደግሞ አሉታዊ ውጤት ሊያስከትል የሚችል ዘላለማዊ የሆነ መንፈሳዊ ሕግ አለ ማለት ደግሞ ስሕተት ነው ። እግዚአብሔር እንዲባርከን በሙሉ ልብ መጸለይ አለብን ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር የምንጠይቀውን ነገር እንዲያደርግልን “ ማዘዝ ” አንችልም ፤ ልናደርገውም አይገባም ። ይህ ዐይነቱ ጸሎት ትሑት ሆነን ፣ በአምላካችን በእግዚአብሔር ጸጋ ላይ ተደግፈን ጸሎታችንን እንዳናቀርብ ይከለክለናል ። ምን ያህል ሰዎች በእምነት እንቅስቃሴ መምህራን የጸሎት ቀመር ፣ “ ያዘዙት ትእዛዝ ” አልሞላ ብሎ ፣ እግዚአብሔርን ተቀይመውት ይሆን ? በርካታ ሰዎች ፣ “ በእምነት ነው ትንቢት የተናገርነው ፤ መገለጥ ያወረድነው ” ሲሉ ይሰማል ።
እግዚአብሔር የሚናገሩትን ነገር ስለሰጣቸው ወይም መገለጥ ስላሳያቸው ሳይሆን ፣ “ አመንሁ ስለዚህም ተናገርሁ ” ( 2ቆሮ 4 ÷ 13 ) ይሉናል ( ልብ ይበሉ ይህ ክፍል ፣ “ አመንሁ ስለዚህም ተናገርሁ ” የሚለው ፣ የክርስቶስን ጌትነትና ትንሣኤ ነው ። ሐዋርያው ጳውሎስ ይህን የምሥራች በመናገራችንም ፣ ከፍተኛ ችግር እንዲሁም ስደት ደርሶብናል እያለ ነው )። ይህ ፣ “ አመንሁ ስለዚህም ተናገርሁ ” የሚለው ቀመር የስንቶችን ትዳር እንዳፈረሰ ፣ ስንቶችን ከሥራ እንዳፈናቀለ ፣ አያሌ ሰዎች ጥሪታቸውን ሜዳ ላይ እንዲበትኑ እንዳደረገ እንዲያው በአጠቃላይ ትውልድን እንዳወደመ ቢያንስ በቤተ ክርስቲያን የኖርን ሰዎች ፣ በውል የምናውቀው ጒዳይ ነው ። የችግሩ ሰለባ የሆኑም ወገኖች ፣ “ ጌታ እንዲህ ተናግሮኝ በቀኑ መጨረሻ እጄን አጨብጭቤ ባዶዬን ቀረሁ ” በማለት በጌታ ላይ ልባቸው እጅግ ሲከብድ እንዲያውም አንዳንዶች ክርስትናን ላይመለሱበት ትተው ሲሄዱ ተመልክተናል ።
ወገኖቼ ማንኛውም ትምህርት የራሱ ሆነ አሉታዊም ሆነ አዎንታዊ ውጤት አለው ። ይህ እኲይ ትምህርት በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያመጣው ጥፋት ፣ እንዲህ በቀላሉ ተነግሮና ተዘክሮ የሚያልቅ አይደለም ። ምናልባት ይህ አስተምህሮ ያመጣው ውድመት ብቻ ፣ የዶክትሬት ድግሪ ማሟያ ጥናት የሚወጣው ድርሳን ይመስለኛል ። ውድ ወገኖቼ ሰው አንድ ጊዜ ይሳሳታል ፤ ምናልባትም ለተወሰነ ዓመት በስሕተቱ
ውስጥ ሊቆይ ይችላል ። ነገር ግን ዝንተ ዓለማችንን ልቡናችን እያወቀ በስሕተት ውስጥ ልንኖር አይገባም ። ይልቁንም መጽሐፍ ቅዱስ ፣ “ መታዘዛችሁ በተፈጸመ ጊዜ ፣ አለመታዘዝን ሁሉ ለመቅጣት ተዘጋጀተናል ” ( 2ቆሮ 10 ÷ 6 ) እንደሚለው ፣ የትምህርቱን ማንነት በማጋለጥ መሠረተ እምነታችንን መጠበቅ ብቻ ሳይሆን ፣ የትምህርቱን እኲይነት በማጋለጥ ክርስቲያኑን ማኅበረሰብ ልንታደግ ይገባል ። እግዚአብሔር አምላካችን በደሙ የዋጃትን ቤተ ክርስቲያን በኪነ ጥበቡ ይጠብቅ ። እኛም የድርሻችንን ኀላፊነት መወጣት እንድንችል ጥበቡንና ኀይሉን ይስጠን ።
የህዳግ መዘክር / የግርጌ ማስታወሻ
እግዚአብሔር ይባርካችሁ ።
6 Hagin , New Thresholds of Faith ገጽ 74-76ÝÝ Copeland , The haws of Prosperity , ገጽ 18-19 ፡፡
7 Charles Capps , The Tongue : A Creative Force ( Tulsa : Harrison House 1976 ), ገጽ 132 ፡፡
8 Hagin , Having Faith in Your Faith ( Tulsa Keneth Hagin ministries , 1980 ) ገጽ 3-5 ፡፡ በዚህ ክፍል “ ማንም ” የሚለው ቅጽል ፣ አማኒውን ማኅበረሰብ እንጂ ፣ የማያምነውን ሰው እንደ ማይጨምር ከክፍሉ ዐውድ ያስተውሏል ፡፡
9 Hagin , Haring Faith in Your Faith , ገጽ 3-4ÝÝ ሕጉ በማንኛውም ሰው ላይ እውን የሚሆን ሕግ ነው ከተባለ ፣ በቤተ ክርስቲያናቸው ስዎች ሕይወት ውስጥ ለምን ሳይሠራ ቀረ የሚለውን ጥያቄ መጠየቅ አግባብነት አለው ፡፡ 10 ዝኒ ከማሁ ገጽ 5 ፡፡ 11 Copeland , The Force of faith በተለይ ገጽ 13- 14:19 እንዲሁም Capps , Faith and Confession , ገጽ 44 ፡፡
12 Hagin , New Thresholds of Faith , ገጽ 7-8 እንዲሁም Right and Wrong Thinking Copeland , Our Covenant with God , ገጽ 38-39 ፡፡
13 Hagin , Real Faith , ገጽ 26 ፡፡ Knowing What Belongs to Us ገጽ 6-7:10:29 ፡፡ Price , How Faith Works , ገጽ 25 ፡፡ 14 Price , How Faith Works , ገጽ 31 ፡፡ 15 Hagin , Words , ገጽ 32 ፡፡ 16 Copeland , The Force of Faith , ገጽ 9-12 ፡፡
Price , How Faith Works , ገጽ 48 ፡፡ 17 Hagin ,
49