Christian Books & Magazines - Free Berea Magazine 5 | Page 48

የጸሎት ግምገማ
የምትል ” ነበረች ፤ ነገር ግን ይህን ማለቷ ያለችውን እንድትሆን አላደረጋትም ። እንዲያውም እውነቱ ከተናገረችው ነገር ተቃራኒ ሆኖ ስለተገኘ ነው ራሱ ጌታ ጐስቋላ ነሽ ፣ ምስኪን ነሽ ፣ ድኻ ነሽ ፣ ዕውር ነሽ እንዲሁም የተራቈትሽ ነሽ የሚላት ።

የጸሎት ግምገማ

እግዚአብሔር የሰጠንን ነገር ስጠን ብሎ መጸለይ እንደማያስፈልግ ፣ እንደ እንቅስቃሴው መምህራን ሁሉ እኛም እናምናለን ። እግዚአብሔር ኀጢአታችንን እንዲዋጀን ልጁን ልኮልን ሳለ እንደ ገና ላክልን ብለን መጸለይ አያስፈልገንም ፤ እንዲህ ዐይነቱ ጸሎት ስሕተት ነው ( ሮሜ 9 ÷ 15-18 ፤ ያዕ 4 ÷ 6-10 )። የእንቅስቃሴው መምህራን ፣ በዮሐንስ 14 ÷ 3-14 እንዲሁም 15 ÷ 7 “ ጠይቁ ” የሚለው ቃል ፣ “ ፈልጉ ” የሚል ትርጒም አለው ማለታቸው ስሕተት ነው ። በአማርኞቹም ሆነ ተኣማኒነት ባላቸው የእንግሊዝኛ ቅጆች ላይ “ ኤቴዎ ” የሚለው የግሪክ ቃል የተተረጐመው ፣ “ ፈልጉ ” ተብሎ ሳይሆን ፣ “ ጠይቁ ” ተብሎ ነው ። ቃሉ የሚገኝበትን ሌላ ዐውድ ስንመለከት ፣ እውነቱ ይኸው ሆኖ ነው የምናገኘው ( ሉቃስ 23 ÷ 23 ፤ 23 ÷ 52 ፤ 7 ÷ 7-11 )። ኧረ ለመሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ ፣ እግዚአብሔር ቃሉን እንዲያከብር “ እዘዙት ” ይላልን ? በርግጥስ ይህ ዐይነቱ አስተሳሰብ ከልዑል አምላክ ለምኖ ማግኘት ከሚፈልግ የሰው ልጅ የሚጠበቅ መንፈስ / አተያይ ነውን ?
እንደ እንቅስቃሴው አስተምህሮ ፣ “ ፈቃድህ ቢሆን ” ብሎ መጸለይ ስሕተት ነው ። ይህ ትምህርት ጒልሕ የሆኑ ሀሉት መሠረታውያን ችግሮች አሉበት ። አንደኛው ቃለ እግዚአብሔር ፣ “ ፈቃድህ ቢሆን ” ብለን መጸለይ እንዳለብን ያበረታታል ። ጌታ ስለ ጸሎት ባስተማረው ስፍራ ( ማቴ 6 ÷ 10 )፣ “ ፈቃድህ ይሁን ” ብለን መጸለይ እንደሚገባን ገልጾልናል ። ጌታ ራሱ በዚህ መልክ ይጸልይ እንደ ነበር መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምረናል ( ማቴ 6 ÷ 39 )። ያዕቆብም ፣ “ ብንኖር ጌታም ቢፈቅድ በሉ ” ሲል ይመክረናል ( ያዕ 4 ÷ 15 )፡፡ ሐዋርያው ዮሐንስም ፣ “ በእርሱ ያለን ድፍረት ይህ ነው ፤ እንደ ፈቃዱ አንዳች ብንለምን ይሰማናል ” ( 1ዮሐ 5 ÷ 14 ) ይላል ። የሐዋርያው ጳውሎስም ጸሎት የእግዚአብሔርን ፈቃድ ማዕከል ያደረገ ነበር ( ለምሳሌ ሮሜ 1 ይመለከቷል )። ሁለተኛው ቃለ እግዚአብሔር ከበሽታችን ሁሉ እንደምንድን ወይም የገንዘብ ችግር ሲያልፍ እንኳ አንደማይነካን ያስተምረናልን ? በማርቆስ 11 ÷ 24 ኢየሱስ ፣ “ የጸለያችሁትን የለመናችሁትንም
ሁሉ እንዳገኛችሁት እመኑ ፤ ይሆንላችሁማል ” ሲል ፣ እምነት የምናምነውንና የምንናገራቸውን ማናቸውንም ነገሮች እውን የሚያደርግ ኀይል ነው ማለቱ ነው ? በፍጹም አይደለም ። በክፍሉ ትምህርት መሠረት ነገሮችን እውን የሚያደርገው ፣ ራሱ እግዚአብሔር እንጂ እኛ አይደለንም ።
ቃለ እግዚአብሔር ፣ “ በእኔ ብትኖሩ ፣ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ ፣ የምትወዱትን ሁሉ ለምኑ ይሆንላችሁማል ” ( ዮሐንስ 15 ÷ 7 ) ይለናል ። “ የምንወደው ነገር ሁሉ ” ሊሆንልን የሚችለው ፣ እኛ በጌታ ስንኖርና ቃሎቹም በእኛ ሲኖሩ ነው ፤ ይኸውም :
1 . ክፉ ባልሆነ ልብ ( ምኞት ) ጸሎታችንን ማቅረብ ( ያዕ 4 ÷ 3 )፣
2 . ከሰዎች ጋር ያለንን ግንኙነት ማስተካከል ፣ ( 1ጴጥሮስ 3 ÷ 7 )፣
3 . እንደ ፈቃዱ መጸለይ ( 1ዮሐ 5 ÷ 14 )።
ይህን አሟልተን ፣ “ የምንወደውን ነገር ሁሉ ” እንዲሰጠን መጸለይ እንችላለን ፤ ነገር ግን የሚሆንልን ፣ ልዑል እግዚአብሔር ፣ “ ይረባቸዋል ስለዚህም ይሁንላቸው ” ብሎ የሚፈቅድልን ነገር ብቻ ነው ፤ ያውም በራሱ የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ። ምክንያቱም የሚያስፈልገንን ነገርም ሆነ ፣ መቼ በትክክል እንደሚጠቅመን እርሱ ያውቃልና ። እኛ እግዚአብሔርን ልናስገድደው የምንችል ትናንሽ አማልክት ሳንሆን ፣ በሚያስፈልገን ነገር ሁሉ በእርሱ ላይ የምንደገፍ ፣ ጸሎታችን ያልተሰማ በመሰለን ጊዜ እንኳ በእርሱ የምንታመን የእግዚብሔር የጸጋ ልጆቹ ነን ።

ማጠቃለያ

የእምነት እንቅስቃሴ መምህራን እምነት ፣ አዎንታዊ ዐዋጅና ጸሎትን በተመለከተ ያላቸው ትምህርት ፣ በግማሽ እውነት ላይ መሠረት ያደረገ ነው ። ነገር ግን ተደባልቆ የቀረበው ገሚሱ ውሸት ፣ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያለመሆኑ ብቻ ሳይሆን ፣ እጅግ ሲበዛ ገዳይ እንዲሁም የማታ ማታ ብዙዎችን መና ያስቀረ ትምህርት ነው ። በእግዚአብሔር የምንታመን ከሆነ ፣ እግዚአብሔር አስደናቂ ነገር እንደሚያደርግ እሙን ነው ፤ ነገር ግን እኛ በእርሱ በመታመናችን እግዚአብሔር ተገዶ ተኣምራትን ያደርጋል
48