Christian Books & Magazines - Free Berea Magazine 5 | Page 47

የእምነት እንቅስቃሴ መምህራን አሉታዊ ዐዋጅ የሚሉትን አስተምህሮ በቃለ እግዚአብሔር ላይ ለማስደገፍ የሚጠቀሙባቸው ጥቅሶች ፣ መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል ያለውን ኀይል ለመግለጽ ፣ የሚጠቀምባቸውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ነው ። ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል ኀይለኛ የሆነበት ምክንያት የእግዚአብሔር ስለሆነ ( እግዚአብሔር ስለተናገረው ) እንዲሁም እውነት ስለሆነ እንጂ ( ሮሜ 4 ÷ 16- 21 )፣ ቃላት በራሳቸው ኀይል ስላላቸው አይደለም ። ዘማሪው ፣ “ እርሱ ተናግሮአልና ሆኑም ፤ እርሱ አዘዘ ፤ ጸኑም ” ( መዝ 33 ÷ 9 ) ያለበት ምክንያት ፣ “ ምድር ሁሉ እግዚአብሔርን እንዲፈራው ፤ በዓለም የሚኖሩም ሁሉ ከእርሱ የተነሣ እንዲደነግጡ ” ( ቊ10-11 ) ነው ። እንግዲህ ፍሬ ነገሩ እዚህ ላይ ነው :— እግዚአብሔር ያለው ወይም የተናገረው ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል ፤ ሰዎች ያሉት ግን ( በነሲብና በግምት ) ሊፈጸምም ላይፈጸምም ይችላል ። ዘማሪው ፣ “ ሰብአውያን የሚናገሩት ቃል እውን እንዲሆን ፣ በእምነት ተሞልተው ይናገሩ ” የሚል ምክር አይመክርም ። ይልቁንም ዘማሪው እስራኤል አምላኳ የሆነውን እግዚአብሔርን እንድትፈራ ፣ ምሕረቱንም ተስፋ እንድታደርግና ርዳታውንም እንድትሻ ይመክራል ( ቊ16-22 )።
የቃለ እግዚአብሔርን ሥልጣን ኀይል በማተም ከሚታወቁ ክፍሎች መኻል ኢሳይያስ 55 ÷ 11 አንዱ ነው ፣ “ ከአፌ የሚወጣ ቃል እንዲሁ ይሆናል ፤ የምሻውን ያደርጋል ፤ የላክሁትንም ይፈጽማል እንጂ ወደ እኔ በከንቱ አይመለስም ”። እግዚአብሔር እንዲህ ያለበት ምክንያት እስራኤል የተሐድሶ ዘመኗ የእግዚአብሔርን ምሕረት ለማግኘት ፊቷን ወደ አምላኳ እንድትመልስ ለመግለጽ ነው ( ቊ 6- 13 )። ይህ የሚሆንበት ምክንያት ፣ እግዚአብሔር ፍጹም ስለሆነ ፣ መንገዱ ከሰብአውያን መንገድ ሰማይ ከምድር እንደሚርቅ የራቀ ስለሆነ ፣ እርሱ የሚለው ሁሉ እውነት እንደ ሆነ እርግጠኞች ነን ( ቊ . 8-9 )።
መጽሐፈ ምሳሌ ቃላት መንፈሳዊ ኀይል አላቸው የሚል ትምህርት አያስተምርም ። እንዲያውም በርካታ የመጽሐፈ ምሳሌ ክፍሎች ፣ የሰብአውያን ቃላት በራሳቸው ኀይል እንደ ሌላቸው ያስተምራሉ ( እባክዎን እነዚህን ክፍሎች በጥሙና ያንብቧቸው ምሳሌ 14 ÷ 23 ፣ 17 ÷ 10 ፣ 26 ÷ 23:26 ፣ 29 ÷ 19 )።
የእንቅስቃሴው መምህራን ፣ የምንናገራቸው ማና ቸውም ነገሮች የሕይወትም ሆነ የሞት ኀይል አላቸው ፣ ለሚለው ትምህርታቸው የሚጠቅሱት ሌላው ጥቅስ ፣
“ በአፍህ ቃል ተጠመድህ ፤ በአፍህ ቃል ተያዝህ ” ( ምሳ 6 ÷ 2 ) የሚለውን ነው ። ነገር ግን ክፍሉ የሚያወራው ፣ ለጐረቤቶቹ ዋስ ሆኖ ፣ በዋሱ መሠረት ስለተያዘ ሰው ነው ፣ “ ልጄ ሆይ ለጐረቤትህ ዋስ ብትሆን ፣ ስለሌላ ሰው እጅህን አጋና ብትመታ ፣ በአፍህ ቃል ተጠመድህ ፤ በአፍህ ቃል ተያዝህ ” ( ምሳ 6 ÷ 1-2 )። ቃላት የሕይወትና የሞት ኀይል አላቸው ለሚለው ትምህርት የሚጠቀስ ሌላው ጥቅስ ፣ “ ሞትና ሕይወት በምላስ እጅ ናቸው ፤ የሚወድዱአትም ፍሬዋን ይበላሉ ” ( ምሳሌ 18 ÷ 21 ) የሚለው ክፍል ነው ። ቃላት የሕይወትና የሞት ኀይል አላቸው የተባለው ፣ ቃላት የእምነትን ኀይል ስለሚያስተላልፉ ሳይሆን ፣ የምንናገራቸው ንግግሮች ጥሩም ሆነ መጥፎ ውጤት ሊያስከትሉ ስለሚችሉ ነው ። በዚህ ዐውድ የሰነፍ ንግግር ጠብን ስለሚጭር በዚህም የሰዎችን ሕይወት ስለሚቀጥፍ ነው ( ቊ 6 ( 7 )። ዘመዶቻችን ፣ “ በለፈለፉ በአፍ ይጠፉ ” እንደሚሉት መሆኑ ነው ።
ለአዎንታዊ ዐዋጅ የሚጠቀሰው ሌ ላ ው ጥቅስ ማቴዎስ 12 ÷ 36-37 ነው ። በክፍሉ ኢየሱስ ፈሪሳውያን በንዝላልነት የሚናገሩትን ከንቱ ንግግር ሲነቅፍ ይታያል ። የእንቅስቃሴው መሪዎች ከዚህ ጥቅስ በመነሣት አሉታዊ ዐዋጅ የሚያስከትለውን ጥፋት የሚገልጽ ቀመር ቀምረዋል ፣ ይኸውም ፣ “ ለምትመኘው ነገር ጠንቃቃ ሁን ፤ ምክንያቱም የተመኘኸውን ነገር ድንገት ከተናገርኸው ታገኘዋለህና ”። ነገር ግን በዚህ ክፍል ኢየሱስ ለማስተማር የፈለገው ነገር ፍጹም ከዚህ የተለየ ነው ። ይኸውም ኢየሱስ ሲያወግዘው የነበረው ንግግር ፈሪሳውያን መንፈስ ቅዱስን ( እግዚአብሔርን ) የመሳደባቸውን ጒዳይ ነው ( ቊ 31-32 )።
መንፈስ ቅዱሰንም የመሳደባቸው ውጤት ፣ በራሱ በእግዚአብሔር እንደሚፈረድባቸው ወይም እንደሚቀጡ እንጂ ፣ አሉታዊ ነገር በመናገራቸው ምክንያት ብቻ ፣ የተናገሩት ንግግር በራሱ አሉታዊ ውጤት ያመጣባቸዋል ማለት አይደለም ። ለምንናገራቸው አዎንታዊም ሆኑ አሉታዊ ንግግሮች ተጠያቂዎች መሆናችን እሙን ነው ፤ የምንጠየቀውም የተናገርነውን ነገር የምናምንና የተናገርነውም ነገር እውን እንዲሆን ጠንክረን የምንሠራ ከሆነ ብቻ ነው ።
እንደ እንቅስቃሴው መምህራን ትምህርት ከሆነ ፣ “ ጐስቋላና ምስኪንም ድኻም ዕውርም የተራቈትህም መሆንህን ስለማታውቅ ” ( ራእይ 3 ÷ 17 ) የሚለው የጌታ ንግግር የይጣን ውሸት ነው ማለት ነው ? በፍጹም አይደለም ። የሎዶቅያ ቤተ ክርስቲያንማ ፣ “ ሀብታም ነኝና ባለጠጋ ሆኜአለሁ ፤ አንድም ስንኳ አያስፈልገኝም
47