Christian Books & Magazines - Free Berea Magazine 5 | Page 44

የእምነት እንቅስቃሴ ስለእምነት የሚያስተምረው ትምህርት ግምገማ
የእምነት ግምገማ
ይፋ ማረግ ማለትም ማወጅ ነው ። ስለዚህ በጸሎታችን ልንከውነው የሚገባን ነገር ፣ እግዚአብሔር ቃሉን እንዲያከብር ማዘዝ ብቻ ነው ። የእንቅስቃሴው ሌላ መምህር ይህን ጒዳይ በሚከተለው መልክ ያብራሩታል :—
“ አማኞች እንደ መሆናችሁ መጠን ፣ በኢየሱስ ስም የማዘዝ መብቱ አላችሁ ። ቃሉን መሠረት እስካደረጋችሁ ድረስ ፣ ቃሉን እውን እንዲያደርግ የማዘዝ መብት አላችሁ ። ምክንያቱም መሠረት ያደረጋችሁት ቃሉን ነውና ። ታማኝ የሆነ ሰው ቃሉን እስከሰጣችሁ ድረስ በቃሉ የታሰረ
ነው ” 27 ።

የእምነት እንቅስቃሴ ስለእምነት የሚያስተምረው ትምህርት ግምገማ

የእንቅስቃሴው አንጋፋ መምህራን በሦስት መሠረታውያን ነጥቦች ላይ ስለእምነት ያላቸውን አስተምህሮ በቅኝት መልክ ተመልክተናል ። ከዚህ በመቀጠል ይህ ትምህርት ምን ያህል ትክክል ነው የሚለውን ጒዳይ ፣ በቃለ እግዚአብሔር ወደ መመርመሩ እንዘልቃለን ።
የብሉይም ሆነ የሐዲስ ኪዳን ቅዱሳት መጻሕፍት ፣ እግዚአብሔር እምነት አለው የሚለውን ትምህርት በጭራሽ አያስተምሩንም ። ምክንያቱም እምነት ማለት በአንድ ሰው ወይም በተወሰነ ነገር ወይም ደግሞ በተለየ አካል መተማመን ወይም መመካት ማለት ነውና ። “ እግዚአብሔር እምነት አለው ” የሚለውን ዐረፍተ ነገር መጠቀም የምንችለው ፣ እግዚአብሔር በራሱ ኀይልና ጥበብ ይተማመናል እንዲሁም የሚያውቃቸው ነገሮች እሙን መሆናቸውን ያምናል በሚለው ትርጒሙ ወይም ዐውድ ብቻ ነው ። ነገር ግን የእምነት እንቅስቃሴ መምህራን እግዚአብሔንም ሆነ ሰዎችን አስመልክተው እምነት የሚለውን ቃል የሚጠቀሙት ፣ አንድ ሰው የሚያምነውን ወይም የሚፈልገውን ነገር በአንደበቱ በመናገር የሚያገኝበት ወይም እውን ያልሆነውን ነገር እውን የሚያደርግበት ፣ ዘላለማዊ ከሆነው መንፈሳዊ ሕግጋት ጋር ተጣምሮ የሚሄድ ኀይል አድርገው ነው ። ይህ ዐይነቱ ትምህርት አንዳችም የመጽሐፍ ቅዱስ ድጋፍ የሌለው መሆኑ ብቻ ሳይሆን ፣ ከብሉያትም ሆነ ከሐዲሳት ትምህርት ጋር በቀጥታ የሚጋጭ ነው ።
ክርስቲያኖች ሁሉ የሚያድን እምነት እንደ ተሰጣቸው እሙን ነው ፤ ነገር ግን ሕዝበ ክርስቲያን ሁሉ ተኣምር የመሥራት እምነት የለውም ። በርግጥም እምነት የአምላክ ችሮታ ( ስጦታ )
44
ነው ። የእምነት እንቅስቃሴ መምህራንም በዚህ እውነት ይስማማሉ ( ሮሜ 12 ÷ 3 ፤ ኤፌ 2 ÷ 8 )። ነገር ግን እግዚአብሔር ፣ “ ተራራን የሚያናውጥ ” እምነት ለሕዝበ ክርስቲያን ሁሉ አልሰጠም ።
ጳውሎስ እንደሚለው ይህ ዐይነቱ እምነት ከመንፈሳዊ ስጦታዎች መኻል አንዱ ነው ( 1ቆሮ 12 ÷ 9 ፤ 13 ÷ 2 ፤ ሮሜ12 ÷ 3:6 )። ሐዋርያው ጳውሎስ ክርስቲያኖች ሁሉ አንድ ዐይነት ስጦታ የላቸውም የሚለው ከዚህ የተነሣ ነው ( ሮሜ 12 ÷ 4-6 ፤ 1ቆሮ 12 ÷ 4-6 : 14-19 : 28-30 ። ጌታችን ፣ “ ተራራን ስለሚነቅለው ” እምነት ሲያስተምር ( ማቴ 21 ÷ 21 ፤ ማር 11 ÷ 23 )፣ ሕዝበ ክርስቲያን ሁሉ የዚህ ዐይነቱ እምነት ባለቤት ነው አላለም ። ይህ አይነቱ እምነት ስጦታ ነው ፤ መንፈስ ቅዱስ ራሱ ፣ “ እንደ ፈቀደ ” የሚሰጠው ( 1ቆሮ 12 ÷ 11 )።
አንዳንዴ እግዚአብሔር ለማመን አስቸጋሪ የሆነውን ነገር እንድናምን እምነት ይሰጠናል ። ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ ፣ ይህ ዐይነቱ እምነት ክርስቲያኖች ሁሉ ፣ ሁልጊዜ ገንዘባቸው ያደረጉት ጒዳይ ነው አይልም ።
ክርስቲያን ያልሆኑ ሰዎች እምነት አላቸው ስንል ፣ በተጨባጭ የተረዱትን ነገር መቀበላቸውን በሚገልጽ ትርጒም ብቻ መሆን አለበት ( ሥነ ዕወቅት በሚባለው የፍልስፍና ጥናት ውስጥ ዕውቀት ፣ እምነትን ፣ እውነትንና ማስረጃን ይፈልጋል የሚባለው በዚህ ምክንያት ነው )። ክርስቲያናዊው እምነት ሰዎች ሁሉ ያላቸው ነገር ሳይሆን ፣ እግዚአብሔር አምላክ ሰዎች ለድነታቸው በኢየሱስ ክርሰቶስ አዳኝነትና ጌትነት ላይ እንዲታመኑ ፣ የሚሰጣቸው ሰማያዊ ስጦታ ነው ።

የእምነት ግምገማ

ቃለ እግዚአብሔር እምነት ፣ “ ኀይል ነው ” አይልም ። ሰዎች እምነትን እንደ መሣሪያ በመጠቀም እውን ያልሆነውን ነገር እውን የሚያደርጉበት ወይም መንፈሳዊውን ቁሳዊ የሚያደርጉበት ወይም ደግሞ እግዚአብሔርን የሚያስገድዱበት መሣሪያ ነው የሚለው ትምህርት ፍጹም ስሕተት ነው ። መምህራኑ ይህን ትምህርት በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ለማስደገፍ የሚጠቀሙባቸውን ሁለት የሐዲስ ኪዳን ምንባባትን እንመልከት ። አምላክ ቃልን በማወጅ ፣ እውን ያልሆነን ነገር መፍጠር ይችላል የሚለው ጥቅስ የሚጠቀሰው ፣ “ ለሙታን ሕይወት በሚሰጥ የሌለውንም እንዳለ አድርጎ በሚጠራ ” የሚለው የሮሜ 4 ÷ 17 ክፍል ነው ። ነገር ግን የሌለውን ነገር እውን ማድረግ የሚችለው አብርሃም ሳይሆን ፣