Christian Books & Magazines - Free Berea Magazine 5 | Page 43

አግድም አደጉ - ከገጽ 12 የቀጠለ ......
የሚለውን ቃል የሚጠቀመው በዐላፊ ጊዜ ነው ( ዕብ 11 ÷ 1 )፤ ነገር ግን ተስፋ በትንቢታዊ ( በመጻኢ ) ጊዜ ነው ጥቅም ላይ የዋለው ። ስለዚህ እምነት አሁን በእጃችን ያለ ነገር እንጂ ( ማር 11 ÷ 23 )፣ ወደ ፊት በእጃችን የሚገባ ጒዳይ አይደለም 16 ። ስለዚህ ፣ ተስፋ የምታደርገውን ነገር ትተህ ፣ ያለህን እምነት በመጠቀም የምትፈልገውን ነገር አሁን በእጅህ አስገባ ” 17 ይሉናል ።

አዎንታዊ አዋጅ

እንደ እንቅስቃሴው መምህራን ትንታኔ ፣ ማንኛውንም ነገር እንደምናገኝ ብናምንና ያመንነውን ነገር እንዳገኘነው ብናውጅ ያሻነውን ( የፈለግነውን ) ነገር በእጃችን እናስገባለን ( ሮሜ 10 ÷ 10 )። ይህ የከጀልነውን ( ያሻነውን ) ነገር የምናገኝበት “ ቀመር ” ወይም “ ሕግ ” ነው 18 ። የምናገኛቸው ክፉም ሆኑ ደግ ነገሮች ፣ በእምነት ሆነን በቃላት በምንገልጻቸው ንግግሮች ይወሰናሉ 19 ። እንቅስቃሴው ይህን ባዕድ ሐሰብ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ለማስደገፍ ሙከራ የሚያደርገው በሚከተሉት ሁለት መንገዶች ነው :— አንደኛው ፤ አምላክ ዓለማትን ለመፍጠር እንደ ግብዐት ( መሣሪያ ) አድርጎ የተጠቀመው ቃላትን ነው ( ዘፍ 1 ፤ መዝ 33 ÷ 6:9 ፤ ዕብ 11 ÷ 3 )። ይህም ቃላት በጽንፈ ዓለም ( በሁለንታ / በአጽናፈ ዓለም ) ውስጥ እጅግ ኀይለኛ ነገር መሆኑን የሚያመለክት ነው ። 20 ሁለተኛ ፤ በርካታ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባባት ፣ ሰዎች በሚናገሩት ነገር ዕጣ ፈንታቸው እንደሚወሰን ይገልጻሉ ። ይኸውም የምንናገራቸው ማናቸውም ነገሮች ፣ የሕይወትም ሆነ የሞት ኀይል አላቸው ( ምሳሌ 18 ÷ 21 )። መጽሐፍ ቅዱስ ለምትናገሩት ነገር ጥንቃቄ ይኑራችሁ የሚለው ፣ ቃላት ክፉም ሆነ ደግ ነገር የማድረግ ኀይላቸው ከፍተኛ ስለሆነ ነው ( ምሳሌ 6 ÷ 2 ፤ ማቴ 12 ÷ 37 ) 21 ። “ እምነት ” እና “ ዐዋጅን ” በተመለከተ አንድ የእንቅስቃሴው መምህር የሰጡት ገለጻ እስካሁን የተመለከትነውን ነገር በጥሩ መንገድ ይሰበስበዋል :— “ እምነት ፈጣሪ ኀይል ነው ። ቃል ደግሞ ይህን ፈጣሪ ኀይል የሚሸከም መሣሪያ ነው ። እምነት እግዚአብሔርን ለሥራ የሚቀሰቅሰው ሲሆን ፣ ፍርሓት ደግሞ ሰይጣንን ለሥራ ያነሣሣዋል ” 22 ። “ አንዲት ጠንቋይ እንዲህ የሚል ነገር ነግራኛለች :— ‘ በጥንቈላ አዕዋፍን እንዲሁም ሰዎችን በቃል እንዴት
እንደምንገድል ተምረናል ። ሊሸነፉ የሚችሉበትን የተወሰኑ ቃላት በመናገር ፣ በአዕዋፋትም ሆነ በሰዎች ላይ በሽታን እንዴት ማምጣት እንደምንችል ተምረናል ። ቃል በመናገር አዕዋፋትን እገድላለሁ !’ አለችኝ እኔም ፣‘ እግዚአብሔር ሆይ ሰይጣን ይህ ዐይነቱ ኀይል እንዳለው አላውቅም ነበር ’ አልሁት ። እግዚአብሔርም ፣‘ ሰይጣን በቃል ይገድላል ፤ አንተ ደግሞ በቃል ሕይወትን መስጠት ትችላለህ ’ አለኝ ። እኛ ክርስቲያኖች በአፋችን ላይ ያለውን የቃል ኀይል በውል አናውቀውም 23 ። ስለዚህ ፣ ‘ ወደ እግዚአብሔር ፊት ቀርባችሁ ጌታ ሆይ ፈቃድህ ቢሆን ’ የሚል ፣ እምነትን የሚገድል ጸሎት በፍጹም ! በፍጹም ! አትጸልዩ ። ትሕትና ይመስላችሁ ይሆናል ፤ ነገር ግን ጅልነት ነው ። ይህን ማለታችሁ እግዚአብሔርን ሞኝ ነህ እንደ ማለታችሁ ነው ። ይህ ዐይነቱ ጸሎት እምነታችሁን ከመሠረቱ በመንቀል ፣ ፍርሓት በሕይወታችን እንዲነግሥ በማድረግ ሰይጣን እንዲሠራ ያደርገዋል ” 24 ። አሁን ደግሞ የመጨረሻውን ነጥብ ማለትም እንቅስቃሴው ስለ ጸሎት ያለውን ትምህርት በአጭሩ እንመልከት ።

ጸሎት

እንደ እንቅስቃሴው መምህራን አስተምህሮ ፣ እግዚአብሔር አስቀድሞ የሰጠንን ነገር ስጠን ብሎ መጸለይ እንዲሁም ፣ ቀድሞ ያደረገውን ነገር አድርግ ብሎ መማጸን ስሕተት ነው ። እግዚአብሔር ቀድሞውንም ቢሆን በክርስቶስ ወጆአዊ ሥራ ድነትን ፣ የኀጢአት ይቅርታን ፣ ፈውስን እንዲሁም ብልጥግናን ሰጥቶናል 25 ። ስለዚህ ቀድሞ የሰጠውን ነገር ስጠን እንዲሁም ቀድሞ ያደረገውን ነገር አድርግ ብሎ መጸለይ ፣ የሰንካላ እምነት ዐይነተኛ ምልክት ነው ። ስለዚህ ፣ “ ፈቃድህ ቢሆን ” ብሎ መጸለይ ስሕተት ነው ፤ ምክንያቱም ድነት ፣ ፈውስ ፣ የኀጢአት ይቅርታ እንዲሁም ብልጥግና ቀድሞውኑም ቢሆን የእግዚአብሔር ፈቃድ ናቸውና ። ስለዚህ በአንድ ርእሰ ጒዳይ ላይ ከመጸለያችን በፊት ፣ የእግዚአብሔር ፈቃድ የሆነው የቱ ነው የሚለውን ጥያቄ ከቃለ እግዚአብሔር አንጻር መመለስ ያስፈልጋል ። ይህን ካረጋገጥን በኋላ ፣ እነዚህ ነገሮች የእኛ መሆናቸውን በእምነት ሆነን በቃላት ይፋ ማድረግ ማለትም ማወጅ ነው ። ስለዚህ በጸሎታችን ልንከውነው የሚገባን ነገር ፣ እግዚአብሔር ቃሉን እንዲያከብር “ ማዘዝ ” ብቻ ነው ( ዮሐ 14 ÷ 13-14 እንዲሁም 15 ÷ 7 ባሉት ክፍሎች “ ጠይቁ ” የሚለው ቃል ይህ ዐይነቱን ትርጒም ወክሎ እናገኘዋለን ) 26 ይንን ካረጋገጥን በኋላ ፣ እነዚህ ነገሮች የእኛ መሆናቸውን በእምነት ሆነን በቃላት
43