Christian Books & Magazines - Free Berea Magazine 5 - Page 41

15 ዓመት ጸሎት ከት/ቤቶች ከታገደ በኋላ የታየ የወጣቶች የሞራል ውድቀት ሰንጠረዥ ከመንግስት መስሪያ ቤቶች በተገኘ ማስረጃ የተደገፈ በፊት ከነበረበት በሚጸለይበት ጊዜ ጸሎት ከታገደ ከ15 ዓመት በኋላ የወጣቶች እርግዝና ከ 15-19 ዓመት እድሜ 1.5% 187% ጨመረ የአባለዘር በሽታ 0.4% 226% ጨመረ የወጣት ጠበኝነት በፊት ከነበረበት 544% ጨመረ የተለያዩ እጽዋት መጠቀም በፊት ከነበረበት ከቁጥጥር ውጭ ሆነ የ S.A.T. ውጤት/ደረጃ የ S.A.T. ውጤት/ደረጃ ክርስቲያን ት/ቤቶች ለ15 ዓመት አንድ አይነት ነበረ ከመንግስት ት/ቤት ውጤት በ50ው ስቴቶች 1,000 ብቻ ነበሩ ለ 15 ዓመታት ሳያቋርጥ አሽቆለቆለ:: በክርስቲያን ት/ቤት 100% ይበልጣል በ50ው ስቴቶች ወደ 32,000 ተከፈቱ ነገሩን ለማጠቃለል ያህል፥ እንዲህ በጥቂት በጥቂት እያለ የሰፋ እና መውጫ የሌለው የወጣቶች አስቸጋሪነት በጣም የከፋበት ጊዜ ላይ በመደረሱ በግለሰቦች ደረጃ(grass root) መንግስትም በተለያየ ተቅዋም እየተረዳ ይሄንን ችግር ለመቅረፍ ሰፊ ጥረት እየተደረገ ነው:: እንደ ክርስቲያን የመፍትሄ ሀሳቦች:- 1) እስካሁን እንዳየነው በሐገሩ ትውልድ ላይ ተሞክሮ ያልሠራና የራሳቸውን ህዝብ አስጨንቆ መውጫ ያሳጣ ችግር ብሎም ቤተክርስቲያኖቻቸውን ሁሉ ባዶ ያደረገና ተተኪ ትውልድ ያሳጣ አካሄድ ውስጥ በፈቃዳችን አንግባ:: 2) ከጣራችን በታች በእግዚአብሔር ቃል የተመራ የቤታችን አስተዳደር ይኑረን እንጂ ፥ በልጆቻችን አንመራ:: 3) አባቶች ወይም ባሎች የክህነት ቦታቸውን ይያዙ፥ እናቶች ወይም ሚስቶች ደግሞ የረዳትነታቸውን ሥፍራ ይዘው በአንድነትና በፍቅር ልጆቻቸውን ይንከባከቡ:: 4) በምንም አይነት መልኩ ልጆች ወላጆችን እንዲመሩ አንፍቀድላቸው:: ወላጆቻቸውን እያከበሩ እና እግዚአብሔርን እየፈሩ እንዲኖሩ እንርዳቸው እንጂ፣ ወላጆቻቸውን እየደፈሩና እያቃለሉ የእርግማን ልጆች አርገን ወደጥፋት አንስደዳቸው:: 5) ከሁሉም በላይ እግዚአብሔር አምላካችንን፥ ያዳነንን ጌታችንን እንፍራ እንጂ ልጆቻችንን አንፍራ:: መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 2(29-30) 6) ዘመናት ወደማይሽሩት ወደ አምላካችንና ወደ አባታችን ቃል ዞር እንበልና እንደቀደሙት አባቶቻችን በመጀመሪያ ራሳችንን፥ ከዛም ልጆቻችንን እና ቤታችንን በጽድቅና በፍርድ እንምራ:: አብርሃም በእውነት ታላቅና ብርቱ ሕዝብ ይሆናልና፥ የምድር አሕዛብም ሁሉ በእርሱ ይባረካሉና። ጽድቅንና ፍርድን በማድረግ የእግዚአብሔርን መንገድ ይጠብቁ ዘንድ ልጆቹንና ከእርሱ በኋላ ቤቱን እንዲያዝዝ አውቃለሁና፤ ይህም እግዚአብሔር በአብርሃም ላይ የተናገረውን ነገር ሁሉ ያመጣ ዘንድ ነው። ኦሪት ዘፍጥረት 18:18-19 41