Christian Books & Magazines - Free Berea Magazine 5 | Page 39

ልጆቻችንን ልናሰለጥን ይገባናል እንጂ ፤ ይህንን ያለመጥቀሙ በገዛ ህዝባቸው የሚነገርለትን አዲስ አካሄድ ልንወርስ አይገባንም እላለሁ :: ይህ ሁኔታ እንዳለ ሆኖ ወደራሳችን ህብረተሰብ ስንመለከት ደግሞ ፥ አብዛኞቻችን ያለንበት ሁኔታ እንደሚጠቁመን ጎልተው የሚታዩ ችግሮች አሉ :: እነርሱን በዝርዝር እንያቸው ::
1 . የቤተሰብ መዋቅራችን መዛባት ፥ 2 . በሁለት ባህል መካከል ግራ መጋባት ፥ 3 . እኔ እንዳደኩኝ ልጄን አላሳድግም በሚል አስተሳሰብ ልጆቻችንን በስርዓት መምራት አቅቶን መረን መልቀቅ ::
እነዚህን ሦስቱን ዋና ዋና ተግዳሮቶች ዘርዘር አርገን እንመልከት ::
1 . የቤተሰብ መዋቅር መዛባት : -
እንደ እግዚአብሔር እና እንደ ክርስቲያን ቤተሰብ ፥ የቤተሰብ መዋቅር ሊሆን የሚገባው እንደሚከተለው ነው ::
ሀ ) ጌታ ኢየሱስ የቤተሰቡ መሪ ፥
ለ ) ባል ( አባት ) ከጌታ በታች የቤቱ ራስ ፥
ሐ ) ሚስት ( እናት ) የባልዋ ረዳት ፣ የልጆቿ ተንከባካቢና አስተማሪ ፥
መ ) ልጆች በወላጆቻቸው የሚመሩ ፣ የሚታዘዙና የሚያከብሩ ፥
ነገር ግን ቤተሰቡን በሚመለከት የሚደረገው ነገር ሁሉ ፥ በልጆች ፍላጎት ላይ የተመሰረተ ስለሆነ በአንደኛ ደረጃ
ቤቱን የመምራት ስልጣን የያዙት ልጆች ናቸው :: ሁለተኛዎቹ ደግሞ እናቶች ሲሆኑ ብዙ ቤተሰብ ውስጥ አባቶች ወይም ባሎች ይሄ ነው የተባለ እንቅስቃሴ ሳያሳዩ ዝም ብለው ተቀምጠዋል ማለት ይቻላል :: የዚህ አይነቱ የተገላበጠ የቤተሰብ መዋቅር እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ካለመሆኑም ሌላ ፥ ቤታችንን ከበረከት የሚያጎድል ነው :: ዘፍጥረት 18 ( 18-19 )
2 . በሁለት ባህል መካከል ያለ ግራ መጋባት : -
በሌላው በኩል ደግሞ በራሳችንና ባለንበት ሃገር መካከል ባሉ የተለያዩ ባህሎች ውስጥ ስለምንኖር ፥ ግራ ተጋብተናል :: ምንም እንኳን ብዙ መልካም ታሪክና ባህል ቢኖረንም የሚታየው ግን : -
ሀ ) ከባህላችን ውስጥ መልካሙን ወስደን የማይጠቅመንን ከመተው ይልቅ ፥ የኛ የሆነውን በሙሉ እርግፍ አድርገን ትተናል ::
ለ ) በደንብ መርምረን ያል ተረዳነውን ያለንበትን ሃገር ባህል በመከተል ፥ ልጆቻችንን ስንንከባከብ ውጤቱ ከነሱ ልጆች ይልቅ በኛ ልጆች ላይ የከፋ ሆኗል :: ይሄንንም የምናየው የአሜሪካውያኑ ልጆች ቢያንስ እስከ 13 ዓመታቸው ወይም ከዛ በላይ ወላጆቻቸውን ይታዘዛሉ :: እኛ ጋ ስንመጣ ግን ገና በ4 እና በ5 ዓመት እድሜያቸው ከጃችን የወጡ ወይም የማይታዘዙ ሆነዋል ::
3 . እኔ እንዳደኩኝ ልጄን አላሳድግም ማለት : -
ሀ ) በዚህ እኔ እንዳደኩኝ ልጄን አላሳድግም በሚል ሐሳብ
ለራሳቸው ቃል የገቡ ወላጆች ፥ ልጆቻቸውን የራሳቸው እድገት ቁጭት መወጫ አድርገዋቸዋል ማለት ይቻላል :: ቤትና ቤተሰብ በጥበብና በእግዚአብሔር ቃል እንጂ በቁጭት አይመራም ::
ለ ) ሌላው ደግሞ ረጅም ሰዓት ወይም ከአንድ በላይ ሥራ በመስራት ልጆቻችን የሚያስፈልጋቸውን ብቻ ሳይሆን የጠየቁትን ሁሉ ለማሟላት ደፋ ቀና ስንል ፥ ከነሱ ጋር በመሆን ፍቅር ስላልሰጠናቸውና ስነስርዓትም ስላላስተማርናቸው ነፍሳቸውንና መንፈሳ ቸውን ለጥፋት ዳርገናል ::
የሚገርመው ነገር የሰዎች ልጆች ችግር ሁሉ ተመሳሳይ ነውና የዚህም አገር ሰዎች ፥ አሁን እኛ በምናልፍበት መንገድ ቀደም ሲል አልፈዋል ። በስልጣኔ እንደሚቀድሙን እንዲሁ በጥፋቱም መንገድ ቀድመውናል ::
ይህም ሁኔታ የጀመረው ከ50 ዓመት በፊት ነው :: ይኸውም አሁን እኛ እንደመሰለን እነሱም አዲስና ዘመናዊ የስልጣኔ መንገድ መርጠው በመከተል ፥ ከእግዚአብሔር መንገድ ፈቀቅ በማለታቸው ነው ::
ዶ / ር ጀምስ ዳብሰን የችግሩን አጀማመር ሲያብራሩ ፥ በ1960ዎቹ ውስጥ ወላጅ ሁሉ የስልጣኔ መንገድ በመከተል የልጆቻቸውን አስተዳደግ በሚከተለው አኳኋን ስለቀየሩት አሁን የደረሱበት ደረጃ ቀስ በቀስ ደርሰዋል ብለዋል :: ይኸውም : - እኔ እንዳደኩኝ ልጄን አላሳድግም ማለትና ልጄ የራሱን መንገድ ይምረጥና ለራሱ ይወስን እንጂ ፥ የኔን እምነት አልጭንበትም የሚሉት ናቸው ::
በነዚህ ዘመናዊ በሚባሉት ሐሳቦች
39