Christian Books & Magazines - Free Berea Magazine 5 - Page 38

እዛም ቤት እሳት አለ ከእህት ለምለም የኋላእሸት ቤተሰብ በአምላካችን በእግዚአብሔር በኤደን ገነት ውስጥ የተመሰረተ፥ የመጀመሪያው ተቋም ነው:: በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ ዘፍጥረት 1 (27-28) እንደተጻፈው እግዚአብሔር ቤተሰብን ሲያይ የሚያየው ባልና ሚስቱን፤ ከዛም ልጆቻቸውን፥ ብሎም ቀጣዩን ትውልዳቸውን ነው:: ስለዚህ ትውልድ የሚጀምረው ከቤተሰብ ነው ማለት ነው:: እንደ እግዚአብሔር ሃሳብ የተባረከ ትውልድ ለማፍራት የሚቻለው ደግሞ፥ ልጆች በአባትና በእናት ስር በፍቅርና በስነስርዓት ተኮትኩተውና ታንፀው ሲያድጉ ነው:: ነገር ግን ይሄ የእግዚአብሔር ተቋም(ቤተሰብ)፥ በተለይም ወላጅነት፥ ከፍተኛ ተግዳሮት እንደገጠመውና አሳዛኝና አስቸጋሪ ቦታ ላይ እንደሚገኝ ይታያል:: ለዚህም ምክንያቱ፥ ወላጆች እግዚአብሔር በቃሉ እንዳዘዘን ዘፍጥረት 18(19) ልጆቻችንን የእግዚአብሔርን መንገድ ይጠብቁ ዘንድ አላስተማርናቸውምና ነው:: ስለዚህ ይሄ ትውልድ በከፊል እግዚአብሔርን የማያውቅና የማይፈራ፥ ግብረገብነት የጎደለው፥ ወላጆችን የሚያሳዝንና የጥፋትን ጎዳና የተከተለ ሆኗል:: ኖሮን ሊሆን ይችላል:: ነገሩን ብናስተውለው ግን የደረሱበት ሥልጣኔና የሚኖሩበት በረከት፥ የአባቶቻቸው አምላክ እግዚአብሔር ከለቀቀላቸው ታላቅ ምህረት የተነሳ ነው ብዬ አምናለሁ:: ምክንያቱም የቀደሙት አባቶቻቸው ወደዚች ምድር የመጡት፥ በነፃነት ጌታን ለማምለክ ፈልገው ስለነበረ፤ ጌታ የሰጣቸውን ይችን ምድር፥ ራሳቸውንና ትውል