Christian Books & Magazines - Free Berea Magazine 5 | Page 36
ከአትላንታ ኮንፍረንስ ትዝታዎች
4ተኛውን የቤርያ ዓመታዊ ኮንፍራንስ ያደረግነው፤አምና ጁን 2015 በአትላንታ ከተማ በምትገኘው የኢትዮጵያ
ወንጌላዊት ቤተርክርስቲያን ነበር:: በኮንፍራንሱ ላይ የተገኛችሁ ሁሉ እግዚአብሔር መልካም ጊዜ እንደሰጠን ምስክሮች ናችሁ::
ክብር ሁሉ ሁሉን ላደረገው ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ይሁን::
የቤርያ አመታዊ ኮንፍራንስ የሚደረግባቸው ቀኖች፤ ዓርብ ቅዳሜና እሁድ ናቸው:: ነገር ግን ሐሙስ ማታ ኮንፍራንሱን
ለማዘጋጀት እድል የደረሳቸው ቅዱሳን የአቀባበል ምሽት ያደርጋሉ:: በዚህም መሰረት በአትላንታ የሚገኙ ቅዱሳንም ከሌላ ቦታ
ለመጡ ወገኖች ሞቅና ደመቅ ያለ ቤተሰባዊ አቀባበል አድርገው ነበር:: ይህ ቀን በጣም ደስ የሚል ነው:: ቤተሰብ ብዙ ጊዜ ቆይቶ
ሲገናኝ የሚታየው ደስታ በሁሉም ፊት ላይ የሚታይበት የመጀመሪያ ቀን፤ ከዛም ዓርብ ጠዋት መደበኛው ኮንፍራንስ ተጀምሮ
እሁድ ማታ እስከሚያልቅ ድረስ......ጌታን አብረን አመለክን…..ቃሉን ተካፈልን…...ማእድን ቆረስን…. አዎ ሁሉንም አብረን::
ክብር ለኢየሱስ ይሁን::
መዝሙረ ዳዊት 133
1 ወንድሞች በኅብረት ቢቀመጡ፥ እነሆ፥ መልካም ነው፥ እነሆም፥ ያማረ ነው። ቅዱሳንን በመቀበል የተጋችሁ
የአትላንታ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን ወገኖቻችን፥ እግዚአብሔር አምላክ በሚያስፈልጋችሁ ሁሉ ይባርካችሁ እንላለን:: በጌታ ፍቅር
እንወዳችኋለን::
የዘንድሮው ኮንፍራንሳችን የሚካሄደው በአሜሪካ ዋና ከተማ በዋሽንግተን ዲሲ በምትገኘው በዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ
ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን ነው:: ይህንን የአንድነታችንን ጊዜ በዚህ ቤተክርስቲያን እንድናደርግ የፈቀዱልንን የቤተ ክርስቲያኑዋን
ዋና መጋቢ:· ፓስተር ሐንፍሬ አሊጋዝን
· ፓስተር የትናየት ኃይሌን
· ፓስተር ጆርጅ ገላትያስን
· ፓስተር አብተው ከበደን
· ፓስተር አማኑኤል ኃይሌን፥
· የቤተ ክርስቲያኑዋን ሽማግሌዎች፥ አገልጋዮችና ምእመናኑን በሙሉ ጌታ ይባርካችሁ፥
እንዳከበራችሁንም እግዚአብሔር ያክብርልን እንላለን::
ወደ ሮሜ ሰዎች 12፥13 ቅዱሳንን በሚያስፈልጋቸው እርዱ፤ እንግዶችን ለመቀበል ትጉ።
እግዚአብሔር ቢፈቅድና ብንኖር ጌታ የሚሰራውን ድንቅ ይዘን በሚቀጥለው መጽሔታችን እስከምንገናኝ የሰላም አምላክ
ከሁላችን ጋር ይሁን፤ አሜን። ከመጽሔት ዝግጅት ክፍል::
36