Christian Books & Magazines - Free Berea Magazine 5 | Page 35

በዚህ መረዳት ስናየው ትዳርን በሙላት የሚገልጸው “ ቃል ኪዳን ” የሚለው ስያሜ ነው ። ቀጣዩ ጥያቄ ፣ ቃል ኪዳን ምንድነው ?” የሚለው ይሆናል ። “ ትዳር ቃል ኪዳን ነው ። አንድ ሲደመር አንድን አንድ የሚያደርግ ቃልኪዳን ።
አዎ ትዳር ሁለት ወገኖች ጥቅምህ ጥቅሜ ፣ ጉዳትህ ጉዳቴ ፣ ወዳጅህ ወዳጄ ፣ ጠላትህ ጠላቴ ፣ ከማለት ባለፈ ሕይወትህ ሕይወቴ ፣ ሞትህም ሞቴ የሚሉበት የአንድነት ኪዳን ባለፈ ሕይወትህ ሕይወቴ ፣ ሞትህም ሞቴ የሚሉበት የአንድነት ኪዳን ነው ። ኪዳኑ ደግሞ ከሁሉ ነገር በከበረው በእግዚአብሔር ቃልና ሕይወትን በሚወክለው በደም ይታተማል ። እናም ሁለት የነበሩት በቃል ሲጣመሩና በደም ሲታተሙ አንድ ይሆናሉ ። በቃል ኪዳን አማካኝነት ሁለትነት ይሞትና አንድነት ይወለዳል ።
ይህ አንድነት እንዲያድግ ግን ሁለት ተጻራሪ ሃሳቦች ፣ ሁለት ዓላማዎች ፣ ሁለት እኔነቶች ፣ ሁለት ቀዳሚ ማንነቶች … ሊሞቱ ይገባል ። “ እኔ ”፣ “ ለእኔ ”፣ “ የእኔ ” ባጠቃላይ “ እኔነቶች ” ተሰውተው አዲስ የጋራ አንድነት ሲወለድ ጣፋጭ የቃል ኪዳን ትዳር ይገለጣል ። ጥቅምን ፣ ምቾትን ፣ ስምን ፣ ክብርን ፣ ጊዚያዊ ደስታን እና ግለ ተኮር አጀንዳን አራግፎ ቃልኪዳንን የሚያስቀድም ሰው ስኬታማ ትዳር ይቋደሳል ።
ሲሆን ትዳር በመንግስታት ያልታወጀ የጦርነት ቀጠና ይሆናል ። ትዳሩ የጦርነት አውድማ የሆነበት ሰው ተጠይቆ “ ትዳር ከጦርነት የሚለየው ሁለት ጠላቶች ሲታኮሱ ውለው በአንድ አልጋ ላይ ማደራቸው ብቻ ነው ።” ማለቱ አንጀት ያላውሳል ። የትዳሩን ሰቆቃ ይገልጻልና ። ሆኖም ግን ለራስ ጥቅምና ፍላጎት መኖር ያቆሙ የአንድ ወንድና የአንድ ሴት ትዳር የቤተ ክርስቲያንን እና የጌታችን የመድሃኒታችንን የኢየሱሰ ክርስቶስን ስእል ማሳየት ይችላል ። ለአንድ ቡድን የሚሰሩና ስኬታቸውም የጋራ ስኬት ብቻ መሆኑን የተገነዘቡ የትዳር ባለ አደራዎች ከብዙ ብክነትና ክስረት ይድናሉ ። ሌላው የቃል ኪዳን መልእክት ቃል ኪዳን በእግዚአብሔር አይን መውጫ በርና መክፈቻ የሌለው ቁልፍ ፣ ደምን የሚቀይጥ ፣ እዳን ፣ ችግርን እና በረከትን የሚያጋራ ፣ ጠላትና ወዳጅን የሚያወርስ ፣ አዲስ ራዕይን እና አዲስ ማንነትን የሚያላብስ ተቋም መሆኑ ነው ። ነገሮች እንደጠበቅነው ባልሆኑ ጊዜና ባልተሟሉም ጊዜ ሮጦ የማይመለጥበት ፣ በትርፍና በኪሳራ ስሌት እንደኮንትራት የማይሰረዝ ፣ ይልቁን ቃልኪዳንን የተረዱ ከጠላት የፍቺ ጥቃት ሃሳብ ያርፋሉ ። ቃል ኪዳንን የተረዱ ድል በቡድን ብቻ መሆኑን ይረዳሉ ። ስለዚህም በትዳር አጋራቸው ላይ ነጥብ ከማስቆጠር ይልቅ
ድካማቸውን በማገዝ ለቡድን አሸናፊነት እንዲተጉ ያደርጋቸዋል ። ቃልኪዳኑን ለሚጠብቁ ሁሉ ደግሞ የቃልኪዳን አምላክ ረዳታቸው ይሆናል ።
ታዲያ ትዳርን በተመለከተ ከተዛቡ አመለካከቶች አንዱ “ ትዳርን ” እንደ ኮንትራት መቁጠር ነው ። ኮንትራት ሰዎች ከኮንትራቱ የሚወጡበትን አንቀጽ ያሰፍሩበታል ። ኮንትራት ሁለት ሰዎችን አንድ አያደርግም ። ይልቁኑ በሁለትነት እስከጊዜው ለጥቅም ብቻ የሚያስተሳስር የሰው ኪዳን ነው ። እናም የሰው ኪዳን ሲፈርስ አዲስ ኮንትራት ከሌላ ሰው ጋር ይገባሉ ። ትዳር ግን ከዚህ እጅግ የተለየ ብቻ ሳይሆን የከበረ ነው ። የኪዳኑም መስራች ሰው ሳይሆን እግዚአብሔር ነው ። ስለዚህም ትዳር ጥቅማችንና መብታችን በተነካ ቁጥር ካላፈረስነው የምንለው የኮንትራት ጥምረት አይደለም ። እስከ ሞት ተቻችሎ ፣ ተሸካክሞ ፣ ተጠባብቆ ፣ ተደጋግፎ ፣ ተፈቃቅሮ የሚጓዙበት የዕድሜ ልክ ቃል ኪዳን እንጂ ።
መዝሙረ ዳዊት 103 ፡ 17-18 “ የእግዚአብሔር ምሕረት ግን ከዘላለም እስከ ዘላለም በሚፈሩት ላይ ፥ ጽድቁም በልጅ ልጆች ላይ ነው ። ቃል ኪዳኑን በሚጠብቁ ፥ ትእዛዙንም ያደርጉአት ዘንድ በሚያስቡ ላይ ነው ።” አሜን !
በተቃራኒው ግን ትዳር መከራ የሚሆነው የሁለት ማንነቶች ፣ ዓላማዎች ፣ እኔነቶችና ግለኝነቶች ትግል ሲሆን ነው ። ያኔ ነው ትዳር የጦርነት አውድማ የሚሆነው ። በአንድ ጣራ ስር የሚኖሩ የሁለት ራዕይ ባለቤቶች ፣ የሁለት ተቀናቃኝ ፍላጎት አስፈጻሚዎች ፣ የሁለት ተፎካካሪ ጥቅም አስጠባቂዎች ፣ የሁለት ቤተሰብ መብት አስከባሪዎች ፣ የሁለት ቡድን ተጋጣሚዎች መድረክ
35