Christian Books & Magazines - Free Berea Magazine 5 | Page 33

አሁን አሁን ግን ከመስማት ወደ ማዳመጥ ፤ ከማዳመጥ ወደ መወዛወዝ ፤ ተሸጋግረናል ። ይህ አካሄድ ከተጀመረ ወዲህ ይመስለኛል መዝሙሩን ከዘፈን መለየቱ ለጆሮም ለአይምሮም እየከበደ የመጣው ። ያ የያኔው የመዝሙር ድባብ አሻራው ጠፍቶ መድረክ ሁሉ ድብልቅልቁ ወጥቷል ። ምነው ጌታን ከማስመረር አልቻልኩም ? አግዘኝ ! ማለቱ አይበጅም ? እሱኮ ደካማን መርዳት ልማዱ ነው ። ውሸት ሆነ ሀሜት ፤ ስርቆት ሆነ ዝሙት ፤ ሰድብ ሆነ ሙግት ፤ ጥላቻ ሆነ ምቀኝነት ፤ ስካር ሆነ ሞቅታ ፤ ዘፈን ሆነ እስክስታ ፤ ለተጠቀሱም ላልተጠቀሱም ሀጢያቶች መድሀኒቱ ማመቻመች ሳይሆን ምክርና ተግሳጽን ተቀብሎ ፤ ለመንፈስ ቅዱስ ወቀሳ ልብን ሰጥቶ ፤ በንስሃ መመለሱ ጌታንም ያስደስታል ፣ ከጎደፈ ህሊናም ነጻ ያወጣል ። እናም ሀጢያትን ማባበል በዝቶ እንደ መዝሙር ለጥናት ከማቅረብና በበደል ላይ በደል ከመጨመር የዳዊት ልጅ ሆይ ማረን ብሎ መመለሱ አማራጭ የሌለው ምርጥ ሀሳብ ነው ።
ይቺን “ ላለመስማማት መስማማት ” ን ስጽፍ በዚሁ የቤርያ ፕሮግራም ላይ አንድ ወንድም ያለው ትዝ አለኝ ። “ አሁን አሁን ክርስቲያን ባክእስላይድ ማድረግ ትቷል ። ይህ ችግር እንደበፊቱ ጎልቶ አይታይም ፤ ምክንያቱም ቤቱም ደጁም በጣም
ተቀራርቧል ። ከጌታ ቤት ውጪ የሚደረገው ነገር ሁሉ ቤቱም ከተደረገ ድሮስ ሰዉ ምን ውጪ አስኬደው ?” እንዲሁ በስም ክርስትና ያለ ቅድስና የበግ ለምድ ለባሽ የቀበሮ ባታይ ሆኖ መኖር ፤ ተመሳስሎ ማደናገር . . . አይገርምም ! . . . ይህንም ያንም እያደረጉ ደግሞ በጠረጴዛ ዙሪያ ምክክር ሲጀመር የራስን ምኞት ላለመጣል “ ላለመስማማት መስማማት ” ብሎ እውነትን ማድበስበስ ያሳዝናል ። እና ይህንን ሁሉ ጉድ ተሸክመን ግማሽ ልጩ ግማሽ ጎፈሬ ከመሆን ፤ እንዲሁም በራድ ወይም ትኩስ ሳንባል ጌታንም ምሳሌ ፈላጊውንም ከምናስነቅፍ ፣ ቆርጠን ተከትለን የቁርጥ ቀን ልጆች ብንሆን ስሙን እናስከብራለን ። አለዚያ ግን እንዲህ አይነቱን ቁስል ላይድን ማባበሉ ታማሚውን ከመግደል አልፎ ጦሱ ለሌሎች ይተርፋል ። ክርስቶስን ተከታይ የሆነ ክርስቲያን የአባቱን ፍቃድ ሊፈጽም እንጂ የልቡን ሀሳብ ሊያከናውን አልተጠራም ። ገላትያ 5 ፤ 17 ላይ “ የምትወዱትን ልታደርጉ አትችሉም ” ተብሎ ተጽፎልናልና ። ቆይማ ወገኖቼ . . . በእርግጥ ሰው ሁሉ በአረማመዱ ፤ ባኗኗሩ ፤ በአነጋገሩ ፤ ባስተሳሰቡ ፤ ወዘተረፈ እንደመንትዮች ቁርጥ አንድ ይሁን ተብሎ ድርቅ አይባልም ። ቢባልም ደግሞ ሊሆን የማይችል ነገር ነው ።
ግን ... ግን ... የእግዚአብሔር ልጆች ሁሉ የክርስቶስ መልክ አላቸው ፤ በአረማመዳቸውም እሱን ይመስሉታል ። በዚህ ከተስማማን ደግሞ ለእውነትና ለመልካም ነገር ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ ወይም አድር ብዬ ሆኖ “ ላለመስማማት መስማማት ” የምትለው ብሂል ላይ ሙጭጭ ማለት እውን ያዋጣል ትላላችሁ ? የለም የለም የእኔ ምላሽ በትልቁ አ-ያ-ዋ- ጣ-ም ! ነው ። አንባቢዎቼ ሆይ እናንተ ይህቺን “ ላለመስማማት መስማማት ” ን ወደመምረጥ ካዘነበላችሁ አልተግባባንም ማለት ነው ።
ይልቅስ “ ላለመስማማት መስማማት ” በምትል መዘዘኛ ቃል መሸነጋገሉን ትተን ሃጢያትን “ እንቢ !” ቅድስናን እሺ በማለት እንደሚገባ እየተመላለስን የእውነትን ወንጌል ሰንደቅ አድርገን ጌታን ብንጠብቅ ይበጀናል ። እናም የሃሳቤ ራስጌና ግርጌ ውሻ በቀደደው ጅብ ይገባልና ፤ “ ላለመስማማት መስማማት ” እያልን ከሀጢያት ጋርስንጫወት ከቅድስና እንዳንጎድል ልባሞች ብንሆን ይበጀናል የሚል ነው ። ብርሀን ከጨለማ ጋር ምንም ሕብረት የለውምና ፤ ማቅናት ያለብንን ካላቀናን ከተጠያቂነት አንድንም ። አዳኝ የሆነውን ከርስቶስን ፤ ጽድቁን ምህረቱንና እውነቱን ተናግረን ታማኝ ባላደራ መሆን ከሁሉ ሊበልጥብን ይገባል ። እናም በሀጢያት ላይ ቆራጦች ሆነን ይህቺን የለበጣ ቃል “ ላለመስማማት መስማማትን ” ከልባችንም ፤ ከአንደ በታችንም ፤ ከመቅደሱና ከቅዱሳንም ፤ አርቀን ጥርት ያለውን የእውነትን ወንጌል በኑሯችንም ፤ በአንደበታችንም ፤ እ ን ደ ታ ዘ ዝ ነ ው ለ ዓ ለ ም እ ና ው ጅ እ ላ ለ ሁ ።
ጨረስኩ ተባረኩልኝ
33