Christian Books & Magazines - Free Berea Magazine 5 | Page 32

“ ላለመስማማት መስማማት ”

በሀገራችንም ሆነ በሌሎች ሀገሮች ብዙ አይነት አባባሎች አሉ ። ሰለ አባባል ሳነሳ አንድ ግርም የምትለኝ ቄንጠኛ አባባል አለች “ ላለመስማማት መስማማት ” አይገርምም ? እስቲ አስቡት ምን ይሉት ዘዬ ነው ? ዞሮ ዞሮ ሰው ላለመስማማት ከተስማማ ምኑ ላይ ነው ስምምነቱ ? በንግግር ፈሊጥ ሌላውን ማደናገር ካልሆነ ፤ በአጭር ቃል አልስማማም ማለት አይቀልም ትላላችሁ ? የምን ነገር እያመቻመቹ ማሳሳት ነው ? እንዲህ አይነቱን አባባል ከቅዱሳን ሰፈር ያርቀው እላለሁ ።

እና ይቺን “ ላለመስማማት መስማማት ” ተብዬዋን ቋንቋ ያለምክንያት አላመጣኋትም ። ዛሬ በዘመናችን በየስብሰባ አዳራሹ ፖለቲከኛው ፤ በየወረዳና ቀበሌው ባለስልጣኑ ፤ እያለም ሲወርድ በአገርኛው በየእድርና ማህበሩ ፤ ብሎም በየአብያተ ክርስቲያናቱ ሰዎች የተለያየ ሀሳብ ሲያነሱና ሲጥሉ ሲፋጩ ይቆዩና መሰማማት ሲቸግራቸው በዚህች አሻጥረኛ ብሂል ስብሰባቸውን ይበትናሉ ።
መቼም በዚች አዚመኛ ብሂል ጥላ ስር የማይታከክ የለም ። ነባሩም ሆነ አዲሱ ከርስቲያን ብዙ አሉታዊ ግብሮችን ተለማምዶባታል ። ቆዩማ ወገኖቼ ይቺኑ መዘዘኛ ብሂል ተገን አድርጎ በአንድ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ መጽሐፋችን ቁልጭ አርጎ ያስቀመጠውን ትልቅ ሀጢያት አንድ የሀጢያት ግብረ - አበር ወይም አስተባባሪ ሀጢያት አይደለም ብሎ ቢነሳ ትስማማላችሁ ? አትስማሙም አይደል ? እሺ ያ ሰው በሀሳቡ ቢጸናና ያንን ሀጢያት ከሀጢያት ተርታ አስወጥቶ ፤ በምን አለበትና በሰበባ ሰበቡ እያመቻመቸ ቢቀጥልበትስ መክሮና ገስጾ እንደማቅናት “ ላለመስማማት መስማማት ” ብላችሁ በቤተ-እግዚአብሔር እንደልቡ ሲፈነጭ ዝም ትሉታላችሁ ? አብራችሁትስ ትጓዛላች ? ሀጢያት እኮ ተድበስብሶ ከተሸፋፈነ መድሀኒት ሳይገኝለት ብዙ ነብስ ይቀጥፋል ። ሁላችንም እንደምንረዳው እንዲህ አይነቱ ድብስብስ ሀጢያት እንደ ወረርሺኝ ተዛምቶ ብዙዎችን ባንዴ መጠራረጉ የማይቀር እዳ ነው ። ዛሬ ዛሬ ሰው በሀጢያት ሲወድቅ መክሮና ገስጾ እንደማቅናት አይምሮው እንዳይጎዳ ፤
ከእህት ራሔል አሸናፊ
እንዳይሰበር ፤ እንዳይሰነጠር ፤ በሚል ሰበባ ሰበብ እያለሳለስን ውስጥ ውስጡን ሳይታወቀን የሀጢያት ግብረ አበሮች እየሆንን መጥተናል ። እናማ ነጩን ነጭ ፤ ጥቁሩን ጥቁር ፤ ከማለት ይልቅ ነጣ ያለ ፤ ጠቆር ያለ ፤ ወደ ነጭ ያደላ ፤ ወደ . . . ብቻ ምን አለፋችሁ እውነትን ፍርጥ አድርጎ ክፉ ሀጢያትን ክቅዱሳን መካከልና ከቤተ መቅደሱ የሚያጠራ ወገን እንደ ብርቅዬው የሀገራችን ዋሊያ እየተመናመነ መጥቷል ።
እስቲ አንዳንድ ነገሮችን ለአብነት እናንሳ ፤ የደጅ የደጁን እንተውና የቤታችንን እንወያይ ። የተጠራንበት ዓላማ እውነትን ማወጅና ወንጌልን መመስከር ሆኖ ሳለ የሀሰት ትምህርት እንደተስቦ ሲዛመት ዐይናችን እያየ ጆሯችን እየሰማ “ ላለመስማማት መስማማት ብለን ” ዝም እንላለን ? ከእውነቱ ወንጌል ውጪ የሆነ አስተምሮ ይዘው መንጋውን ሲያውኩ ፤ ወይም እውነት እንዳይገለጥ ያልተጻፈ እያነበቡ ፤ አሊያም እያነበነቡ ብዙዎችን በሰፊው ጎዳና ወደጥፋት ሲያግዙ ይህንንም በቸልታ “ ላለመስማማት መስማማት ” ብለን እንለፈው ? ክርስቲያን ክርስቶስን የመከተሉ ዋነኛ ዓላማ እውነትንና የእውነትን ወንጌል ለፍጥረት ሁሉ ማወጅ ነው ። እና እዚህ ውስጥ ከሌለን ቦታችን የትጋ ነው ? ለሚጠፉት ነብሳትስ ተጠያቂው ማን ነው ?
የሀጢያት ትንሽ እንደሌለው ልቦናችን ሲያውቅ ለሀጢያት ደረጃ አውጥተን እየመደብን ልባችን የከጀለውን ሁሉ መሞካከርም ጀምረናል ። ድሮ ድሮ አልኮል መጠጥ ባፉ ሊዞር ቀርቶ ስሙን ማንሳት እንኳን እርኩሰት ይመስለው የነበር ክርስቲያን አልፎ ተርፎ በአህዛብ ማህበር ጫወታ አድማቂ ሆኖ ከያይነቱ እየቀማመሰ “ ለሆድህ ህመም … ን ” ሆዱን ቢያመውም ባያመውም ማጣቀስ ጀምሯል ። ይህን አይነቱ የድፍረት ሀጢያት ወደ ወይን ጠጅ አትመልከት የሚለውን አስረስቶ ብዙዎችን ቢያስትም ሁሉንም ክርስቲያን ግን አያካትትም ። ቢሆንም ግን አያሌ ወገኖች ይታሙበታል ።
የዘፈን ነገርማ አይነሳ ! ያኔ በዜና መካከል ለሚመጣ ዘፈን እንኳን የቲቪ ወይም የሬዲዮ ድምጽ እናጠፋ እንዳልነበር
32