Christian Books & Magazines - Free Berea Magazine 5 | Page 29

“ ፍቅር ለባልንጀራው ክፉ አያደርግም ፤ ስለዚህ ፍቅር የሕግ ፍጻሜ ነው ።” ሮሜ 13:10
ረድተውኛል ።
ከድቅድቅ ጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃን ያመጣኝ ከዘላለም ሞት አስመልጦ የዘላለምን ህይወት በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል የሰጠኝ እግዚአብሔር አምላኬ ለዘላለም ይባረክ ።
በቤርያ የስልክ አገልግሎት በእውነት ጌታ ይክበርበት :: ጌታ በሙላት ሲሰራና ክብሩን ሲገልጥ ሲምርና ሲያድን በዚሁ አገልግሎት ጌታን ባገኙ በብዙዎችና በራሴም ሕይወት አይቻለሁ ። የቤርያ አገልጋዮች ጌታን የሚታዘዙና የጌታ ፍቅር ያላቸው እንዲሁም ጌታ የሚጠቀምባቸው ናቸው ። የጌታን ፍቅር በነሱ አይቻለሁ ። ከእነርሱም ብዙ ተምሬአለሁ ።
ይህ መስመር ውዱን አዳኜን ጌታየን ኢየሱስ ክርስቶስን ያገኘሁበት የተጽናናሁበት በጌታ ያደኩበትና የተጠቀምኩበት ነው ።

“ ሰላምን እተውላችኋለሁ ፥ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም ።

ልባችሁ አይታወክ

አይፍራም ።”

የዮሐንስ ወንጌል 14 ፥ 27

እየተስተዋለ

አለቅነትህን ሺህ ጊዜ ማወጁ ከሹማምንት ቁንጮ ራስክን መፈረጁ የሰጠህን ክብር አላግባብ ማዋሉ ስምህን ለማግነን ትርጉም መቀየሩ እኔ ነኝ ፈላጩ እኔ ነኝ ቆራጩ ለእልፍኝ ላደባባይ ለቤቱ ለውጩ
ብሎ መነሳቱ ፤ ን-ገ-ረ-ኝ ወንድሜ ከወዴት ያደርሳል መውደድ ወይስ መ-ው-ረ-ድ የትኛው ይከብዳል ? ስልጣን ወይስ ፍቅር ሚዛን የሚደፋ ጎብጦ የሚያቀና ስቆ እየተከፋ
ን-ገ-ረ-ኝ ወንድሜ የቱ ነው ከባዱ ? የ-ቱ ነው ጠሊቁ ? ክርስቶስ ለቤቱ ስልጣን ሆነ ክብር ዝና አልነበር ጭንቁ እናም ቤት ሲቀና ጎጆ ሲደረባ እ-የ-ተ-ስተ-ዋ-ለ የትም አይሻገር የጎድኑን አጥንት ረዳቱን የጣለ ስ-ማ-ማ ወንድሜ ፤ አንተ እኔ-ኔ ስትል ረዳትክን ስትገፋ በቡሀ ላይ ይሉ ቆሮቆር ጨምረህ ችግር ስታሰፋ እ-ሷ ራስነትክን በበረከት ወስዳ በእንባዋ እንደዘራች በደስታ አጭዳ ስትበለጥ በልጣ አሜን ! አሜን ! ብላ በመልካምነቷ ሁ-ሉ-ን-ም ጠቅላ በገዛ ራስህ ላይ ፤ ዘውድ አርጎ ሲሾማት ፤ ጉድህ እንዳይፈላ !
እናም ቤት ሲቀና ፤ ጎጆ ሲደረባ ፤ እየተስተዋለ ፍቅርን አውጅ እንጂ ፤ እራስህን ኮፍስ ፤ ሚስትህን አሳንስ ፤ መጽሀፉም ፤ ቄሱም ፤ ዲያቆኑም አላለ ።
ከእህት ራሔል አሸናፊ

“ ፍቅር ለባልንጀራው ክፉ አያደርግም ፤ ስለዚህ ፍቅር የሕግ ፍጻሜ ነው ።” ሮሜ 13:10

29