Christian Books & Magazines - Free Berea Magazine 5 | Page 28

አሁን ነገሩ ተቀይሮ ለሁሉ መጸለይ ደስ ይለኛል ። ጌታ አሮጌውን አስጥሎ አዲስ አለማምዶኛል ። ይሄው ከ 2010 ጀንዋሪ ጀምሮ ኑሮዬን ካምላኬ ጋር አድርጌያለሁ ። የሚገርመው ደግሞ በስጋም በመንፈስም የተወለድኩት በጌታ ልደተ ወር መሆኑ ነው ።
ከክርስትና ልምምድዎ ምን ያስደስትዎታል ? ጸሎት ! ጸሎት ! መጸለይ በጣም ደስ ይለኛል ። በጸሎት ጌታ ከብዙ ፈተና አውጥቶኛል ። ብዙ ምስክርነቶች አሉኝ ፤ ሳልናገር የማላልፈው ግን ከቬጋሱ የቤርያ ኮንፍራንስ ስመለስ ወድቄ የጎድንህ አጥንት ተሰንጥቋል ተብዬ ዶክተሮች ለቀዶ ጥገና ( ሰርጀሪ ) ካሰናዱኝ በኋላ በቤርያ የጸሎት አገልጋዮች ተጸልዮልኝ በሚደንቅ ሁኔታ ሰርጀሪም ሳልደረግ ጌታ ፈውሶኛል ። ሁለት ሶስቴ እኔም ሀኪሞችም ተሰፋ በቆረጥንበት ነገር ላይ ጌታ ጣልቃ እየገባ እንደቃሉ ከሚያሰደነግጥ ነገር ሁሉ አሰመልጦኛል ። ባለፈው ዓመት ደግሞ ለአትላንታው ኮንፍራንስ ትኬት ቆርጬ ከተዘጋጀሁ በኃላ ድንገት ሁለቱም እግሮቼ አልንቀሳቀሰ አሉ ። ከቤርያ አስተባባሪዎች አንድ ወንድም ሲደውልልኝ ታምሜያለሁ አልመጣም አልኩት ። ይህንን ሲሰማ ፤ አንተማ አትቀርም እንጸልያለን አለና ጸለየልኝ ። ሰንት ቀን ታስሮ የቆየ እግሬ ከጸለየልኝ በኋላ መራመድ ቻለ ። የጓጓሁለትንም ፕሮግራም ተካፍዬ ተባርኬ በሰላም
ተመለስኩ ። ጌታ በነገር ሁሉ እየረዳኝ ይኸው በጤንነት አመልከዋለሁ ::
በምስክርነታቸው ተደንቄ የመጨረሻ ጥያቄዬን አቀረብኩላቸው ። ጌታን የማገልገል እቅድ አለዎት ? ካለስ በየትኛው የአገልግሎት ዘርፍ መሰማራት ይፈልጋሉ ? አዎ ጌታን የማገልገል እቅድ አለኝ ። ወንጌልን ለማዳረስ ከቤርያ ጋር በገንዘብ እያገለገልኩም እየተባረኩም ነው ። በተለይም ያደኩበት አካባቢ በወንጌል ለመድረስ ፣ ጌታ የሰጠኝን መልሼ ለሱ በመስጠት ፣ ለተለያዩ አብያተ ከርስቲያናት ፣ ለህጻናት መርጃ ድርጅቶችና ወንጌልን ይዘው ለሚሮጡ ሁሉ በተቻለኝ አቅም ድጋፍ አደርጋለሁ ። ይህን አሉና በእርካታ ስሜት ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ሃ--ሌ-ሉ-ያ ! ጌታ ኢየሱሰ በክብር ይመጣል ! አሉ እኔም በረጂሙ አ -ሜ -ን ! አልኩኝ ።
ጌታ ይህንን ድንቅ ራእይ ለሁላችንም ያብዛልን ብዬ በጸሎት እንደጀመርን በጸሎት እግዚአብሔርን አመስግነን ተለያየን ።

ሰላሜ ሙሉ ሆነ ።

ከእህት ቅድስት ወረታ
ዮሐንስ ወንጌል 1 ፥ 12 “ ለተቀበሉት ሁሉ ግን ፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው ፤” የታደገኝና ከሞት ያዳነኝ ጌታ ስሙ ይባረክ ።
የክርስቶስ ሰላምና ጸጋ ለሁላችሁም ይብዛ ። ግራ በተጋባሁበትና ነፍሴ ተጨንቃ በብዙ ባዘንኩበት ወቅት የቤርያን መስመር እህቴ ሰጠችኝ ። ከዛም ወደመስመሩ እየገባሁ ለጥቂት ቀናት ከሰማሁ በኋላ አንድ ቀን ጌታን የምትቀበሉ ሲባል ጌታን ተቀበልኩኝ ። ተጸለየልኝ ። እግዚአብሔር ይመስገን ከዚያች ጌታዬን ካገኘሁባት ከተባረከች ቀን ጀምሮ ሰላሜ ሙሉ ሆነ ።
የዮሐንስ ወንጌል 14 ፥ 27 “ ሰላምን እተውላችኋለሁ ፥ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም ። ልባችሁ አይታወክ አይፍራም ።” የቤርያ አገልጋዮች እኔን በሚመቸኝ ሰዓት በሚገባ ተከታትለውኝ
. የደህንነት ትምህርት . የደቀ መዝሙር ትምህርት . . መጽሐፍ ቅዱስ እንዴት እንደማጠናና እንዴት እንደምጸልይ አስተምረውኛል ።
ከትምህርቶቹ በተጨማሪም በጸሎትና በምክር ይህንን ውድ አዳኜን ጌታ ኢየሱስን በደንብ እንዳውቀው
28