Christian Books & Magazines - Free Berea Magazine 5 - Page 26

ከቤርያ መጽሔት ዝግጅት እህት ራሔል አሸናፊ የአቶ ጌታቸው አሸኔን የሕይወት ምስክርነት በጽሁፍ አቅርባልናለች። አቶ ጌታቸውን በቤርያ መጽሔት ስም የሚባርክ የህይወት ምስክርነታቸውን ስላካፈሉን ተባረኩ እንላለን። በእኔ የሚያምን ሁሉ በጨለማ እንዳይኖር፤ እኔ ብርሀን ሆኜ ወደአለም መጥቻለሁ። ዮሐ 12፤46 ጨዋታችንን ከመጀመራችን በፊት አብረን ጸለይን። ከዚያም ሙሉ ስማቸውን ጌታቸው እሸቴ አሸኔ እባላለሁ በማለት አስተዋወቁኝ። እዚህ ሀገር በአያት ስም መጠራት የወግ ነውና አሸኔ እያሉ ይጠሩኛል። ባለቤቴ ጸሀይነሽ ዮሴፍ ተድላ ትባላለች። አምስት ልጆችን አፍርተናል። የተወለድኩት ሜጫ ሲሆን ፤ ያደግኩት ግን ተጉለትና ቡልጋ አውራጃ ነው። የአንደኛ ደረጃ ትምህርቴንም ያጠናቀቅኩት እዛው ተጉለት ሳሲት በምትባል የገጠር ት/ቤት ነው። ከዚያም ከቤተሰብ ጋር ወደ አ/አ መጣሁ። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴንም በተፈሪ መኮንን እና በባፕቲስት ሚሽን ት/ቤት አጠናቅቄ ወደስራው አለም ተሰማራሁ። እ/ኢ/አ በ1963 ዓ/ም በማታው ትምህርት ክፍል ከአምስት ኪሎ በምህንድስና ተመረቅኩ። ከዚያም በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ተቀጥሬ እየሰራሁ ሳለ ለውጥ መጣና የተክለሀይማኖት ወረዳ አዝማችና፤ የከተማ ትርፍ ቤትና ቦታ ጉዳይ ሰራተኛ አድርገው መደቡኝ። ስራው ብዙ ውጥረት ነበረበትና ደስተኛ አልነበርኩም። ያም ሆኖ “ቤት አላግባብ መልሰሀል” በሚል ሰበብ ከርቸሌ አወረዱኝ። ከጥቂት የእስር ቤት ቆይታ በሁዋላ ነገሩ ተጣርቶ በነጻ ተለቀቅኩኝ። ከዚያም ጥቂት እንደሰራሁ የጎንደር ከተማ ስራ አሰኪያጅ አድርገው ወደ ጎንደር ላኩኝ። ከጎንደርም ወደ ሁመራ ለስራ ሄጄ በግርግሩ ምክንያት ብዙ ጓደኞቼን ሳጣ እኔ ግን በሚደንቅ ሁኔታ ከተተኮሰብኝ ጥይት ተርፌ ወደ አ/አ ተመለስኩ። 26 ከጥቂት ቆይታ በኋላም የትምህርት እድል እንዲሰጠኝ ለፖላንድ መንግስት አመልክቼ ስለተፈቀደልኝ ወደፖላንድ ሔድኩኝ። ፖላንድ ትምህርት ላይ ሳለሁ የእረፍት ጊዜዬን የማሳልፈው ወደ አሜሪካ እየመጣሁ ነበረና አገሩን በደንብ ተለማመድኩት። ማስተርሴን ከሰራሁ በኋላ ትምህርቴን የመቀጠል ሀሳብ ቢኖረኝም፣ ልጆቼን ወደማስተማሩ ልቤ ስላዘነበለ ለዶክትሬት የጀመርኩትን የከፍተኛ ትምህርት በማቋረጥ ስራ ፈልጌ ያዝኩ ። ብዙም ሳልቆይ እግዚአብሔር ረዳኝና አምስቱን ቤተሰቦቼን በአንዴ አመጣሁ። የቤተሰቦቼ መምጣትም ደስታ መሆን ሲገባው ታላቅ ፈተና ውስጥ ከተተኝ። አሉና ጥቂት ዝም አሉ። ዝምታቸው አስደንግጦኝ ምነው ምን ችግር ተፈጠረ ? አልኳቸው። ፈጠን ብለው ቤተሰቦቼ በሙሉ ጴንጤ ሆነው መጡ። እኔ በሕይወቴ እንደ ጴንጤ የምጠላው ነገር አልነበረም። ይግረምህ ብለው የገቡ እለት ማታውኑ እንጸልይ አሉኝ በጥብቅ ተቃወምኩዋቸው። እዚህ አገር ስራ እንጂ ይሄ አያዋጣም ብዬ ላስፈራራም ሞከርኩ። ባለቤቴም ከነሱ ጋር አብራ ጌታን ተቀበል ስላለችኝ በቤተሰብ ውስጥ ከባድ ብጥብጥ ተነሳ። በዚሁ ምክንያት ልለያት ሁሉ አስቤ ነበር። ይህ ሁሉ ሲሆን ግን እነሱ መጸለያቸውን አላቋረጡም። እንደውም ክጓደኞቻቸው ጋር ልብሴ ላይ ሳይቀር እጅ እየጫኑ ይጸልዩ ነበር። ሆኖም ግን በእንቢተኝነቴ ጸንቼ ብዙ ቆየሁ። አንድ ቀን ልጄ የአዲስ ኪዳን መልእክት የያዘ 12 ካሴት አምጥታ ስጠችኝ። እንደልማዴ ብቆጣትም አግባብታ “ግዴለም ስማው” ብላ ትታልኝ ሄደች። ከዚያ ቀስ እያልኩ ካሴቱን ስሰማ ያው የማውቀው የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ሆኖ አገኘሁት። በልቤም ታዲያ ይህንን ከሆነ የሚያስተምሩት ክፋቱ ምኑ ላይ ነው? እያልኩ እራሴን መጠየቅ ጀመርኩ። ባዳመጥኩት ቁጥር እግዚአብሔርን የማወቅ ፍላጎቴ እየጨመረ መጣ። እናም የልብስ መስቀያ ክፍል (ክሎዜት) ውስጥ ተደብቄ መጸለይ ጀመርኩ። ሁሌም ጌታ ሆይ እራስህን ግለጥልኝ፤ መንገድህን አሳየኝ፤ በየት በኩል ነው የማገኝህ? እያልኩ እጸልይ ነበር፦ ሲሉ ከአፋቸው ነጠቅ አድርጌ ክሎዜት ውስጥ? አልክዋቸው አ _ _ _ዎ! አሉና በረጂሙ መለሱልኝ። ሁለታችንም ተሳሳቅን። በልቤም ለካ ክሎዜት ውስጥ ልብስና ጫማ ብቻ