Christian Books & Magazines - Free Berea Magazine 5 | Page 25

ያላስፈላጊ ክርክር ውስጥ በመግባት ሰዎችን ወደ ጌታ እንዲመጡ እንኳን ሳንጋብዝ እንለያያለን ። እንዲያውም እልህ ውስጥ ከተን እንሸኛቸዋለን ። ከላይ የተጠቀሱት አምስት ነጥቦችና ዘጠኝ ጥቅሶችን ለማስታወስ አምስቱ ጣቶችህን መጠቀም ይረዳሃል ።
የተሰጠንን የድነት በረከት ለራሳችን ብቻ ቀብረን ይዘነው ይሆን ? ለእግዚአብሔር በመታዘዝ ይህን በረከት ለሌሎች ማፍሰስን ካላወቅን ፣ ሌሎች የእግዚአብሔርን ማንነት በሕይወታችን ማየት አይችሉም ።
የዚህ ጽሑፍ ዓላማ በምስ ክርነታችን መ ክ ሊ ታ ች ን ን እንዴት እንደምታበዛውና ልክ በአሳዬ ሕይወት እንደሆነው እኛም በመታዘዝ ፍሬያማ የምንሆንበትን መንገድ ለማሳየት ነው ። በሌሎች ድካም ዘና እንድንል አለያም እንድንዝል ሳይሆን በድካማችን የሚያግዘን ጌታ እንዳለና ልባችንን አነሳስቶ ፣ በጥበብ ሞልቶ ፣ ለሰማያዊ ሽልማት እንደሚያበቃን በማመን ነው ። ልብ እንበል ! አባቶች “ ከመጠምጠም መማር ቅደም ” ያሉት እንዲሁ አይደለምና ራሳችንን እናዘጋጅ ።
የ ጌ ታ ሰላምና ጸጋ
ይብዛላችሁ ።
ኮነ ፍስሐ

ወንጌል የወለደው ፅናት

ትርጉም በወንድም ሚካኤል ዓለሙ
በጣም ሀብታም ከሚባሉ የእስልምና እምነት ተከታይ ቤተሰብ ውስጥ በምቾት ያደገውና መዝናናትና መጫወት የሚወደው ሀሰን ፥ በድንገት ባህሪው ተቀይሮ ስራው መጽሐፍ ቅዱስ ማንበብ ብቻ ሆነ :: በዚህ ድርጊቱ ደስ ያልተሰኙት አባት ፥ ልጃቸው ሀሰን በእስልምና ከፍተኛ ኮሌጅ ትምህርቱን እንዲከታተል ቢያስመዘግቡትም አሻፈረኝ አለ :: ይባስ ብሎ ኢሳ ( ኢየሱስ ) ጌታ ነው ፥ እኔም የእርሱ ተከታይ ነኝ ብሎ አረፈው :: ሀሰን ክርስቲያን መሆኑን የሰሙት ቤተሰቦቹ እጅግ በማዘን ብሎም በመቆጣት ፥ ሊያግባቡትና ሊያስፈራሩት ሞከሩ :: እርሱ ግን ጭራሹኑ ብሶበት የመጽሐፍ ቅዱስን ትክክለኛነትና ኢሳም እውነተኛ አምላክ እንደሆነ ደጋግሞ ማስረዳትና ማስተማር ቀጠለ :: አባቱም ፥ ድርጊቱ ቢያበሳጫቸው ፖሊሶችን በመጥራት ልጃቸው ከሀዲ እንደሆነና እስላማዊው የሳውዲ አረቢያ መንግስት ፥ አስፈላጊውን እርምት እንዲሰጠው አሳልፈው ሰጡት ::
ፖሊሶቹ ሀሰን የጀመረውን እምነት እንዲያቆም ካለበለዚያ ግን የሚጠብቀው አንገቱን መቀላት እንደሆነ ቢመክሩትም ፤ በንቀት አይን እየተመለከታቸው ምርጫዬ መቀላት ነው ! እምነቴን አልክድም ! ብሎ ጠንክሮ ቆመ :: የሀሰን ቤተሰቦች ካላቸው ክብር የተነሳ ፥ ፖሊሶቹና ባለስልጣኖቹ እምነቱን እንዲቀይርና ተመልሶ እስላም እንዲሆን ከማስፈራራት እስከ መግረፍ ቢደርሱም ፤ እርሱ ግን አቋሙን ሊቀይር አልቻለም :: በመጨረሻም ሀሰን ላይ የሚወሰደው የቅጣት እርምጃ ሌሎችን እንዲያስተምር የከተማው ሰው በተሰበሰበበት እንዲሰቀል ተፈረደበት :: ነገር ግን ከፍተኛ ክብር ላላቸው ቤተሰቦቹ ሲባል አንድ እድል እንዲሰጠው ተወሰነ :: ሀሰን በብዙ ሺህ ህዝቦች መካከል ለመሰቀል ወደመስቀያው ቦታ በወታደሮች ታጅቦ ተወሰደና አንገቱ ላይ ገመድ ገባ :: ለቤተሰቦቹ ሲባል የተሰጠው እድል ፥ ምናልባትም ስቅላትን ፈርቶ ፣ የጀመረውን እምነት ክዶ ወደ እስልምና ቢመለስ በማለት ነበር ለመጨረሻ ጊዜ እንዲናገር የተፈቀደለት ። ይህንኑም ፥ አዛዡ ወታደር ወደ ሀሰን ጆሮዎች ተጠግቶ “ ይቺን የመጨረሻ እድል ተጠቅመህ ህይወትህን አትርፍ ” ብሎ በሹክሹክታ ነገረው ። ከዚያም መነጋገሪያውን በመያዝ “ ሀሰን የቃፊር እምነትን በመካድ እስልምናን እንደገና ለመቀበልና ለመታዘዝ ቢስማማ በማለት ክቡር ፍርድ ቤት ለቤተሰቦቹ ሲል ይህን የከበረ እድል ሰቶታል ” አለ .:: ወደ ሀሰንም ዞር ብሎ “ ሞትን ወይም ደግሞ እስልምናን መምረጥ ያንተ ድርሻ ነው ” በማለት መነጋገሪያውን ሰጠው :: ሀሰን በፈገግታ ፊቱ እያበራ እንዲህ ሲል ንግግሩን ጀመረ ::
“ በሁለት ነገር ውስጤ ተወጥሯል ፥ ደስታና ሀዘን አለ ::” እንደመሳቅም
በገፅ 31 ይቀጥላል
25