Christian Books & Magazines - Free Berea Magazine 5 - Page 24

በማድረግ ስህተት እንሰራለን። ሆኖም ግን ሊሰሙት ለሚወዱና ለመስተካከል ፈቃደኛ ልብ ላላቸው፤ አስተካክሎ ፍሬያማ ለማድረግ ጌታ ሁሌም ዝግጁ ነው። ዛሬ ላይ ቆመን ትላንት ትዝ ሲለን በጸጸት እንሞላለን። ያለፈውን ስህተታችንንና ያስከተለውን ውድቀት ስናስብና አሁን እየተለማመድን ያለውን የእግዚአብሔርን ፀጋ ስናይ በውድቀት ያሳለፍነው ጊዜ ይቆጨናል። በርግጥ እግዚአብሔር የት ላንት ሕይወታችንም አምላክ ነው። ያለፈውን ትዝታ የሚያመጣው ለወደፊት መንፈሳዊ ሕይወታችን እድገት እንዲሆን ነው። እርሱ ባይረዳንና እጃችንን ይዞ ባያወጣን የወደቅንበትን ጭቃ እያቦካን በዛው የስህተት አረንቋ ውስጥ እንከርም ነበር። ሆኖም ጌታ ክንደ ብርቱ ስለሆነ ሲያሻግረን ያለፈውን የልጅነት ዘመን ውድቀትና ድክመት ፈጽሞ በማስወገድ በህሊናችን ላይ አሻራውን እንዳይተው አድርጎ ነው። እውነት ነው ለብዙዎቻችን የሚያስቆጩ ወርቃማ የምስክርነት እድሎች አምልጠውናል። ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ያለፈውን አለማወቅ፣ ድክመትና ጸጸት ለውጦ የወደፊት ሕይወታችን የሚመሰረትበት አስተማማኝ መሰረት ሊያደርገው ይችላል። መመለስ የማንችለውን ያለ ፈውን ዘመን ትተን፣ በእግዚአብሔር ምህረት በዕድሜያችን ላይ በ ተጨመረልን ዘመን በማስተዋል ከጌታ ጋር አብረን ለመስራት እንነሳ። ለክርስትያኖች በምድር ሳለን ብቻ ልናደርገው የታዘዝነው ነገር ላልዳኑት መመስከር ነው። በሰማያዊው ዓለም እንመስክር ብንል 24 እንኳን የምንመሰክርለት ያልዳነ ሰው አናገኝም። መስክረው ሰዎችን ወደ ጌታ ያመጡት በሽልማታቸው ሲደምቁ አይተን መመስከር ቢከጅለን እንኳን የሚታሰብ አይደለም። ታድያ ብዙዎች ይህን ዕድል በምድር ሳሉ ለምን አይጠቀሙበትም ብለን ስንጠይቅ፣ ተግዳሮቶቹን ማየት ግድ ይለናል። Everyday Evangelism የተባለው አገልግሎት በ2016 በሰሜን አሜሪካ ያደረገው ጥናታዊ መረጃ “95% የሚሆኑት ክርስትያኖች በዓመት ውስጥ ለአንድም ሰው አይመሰክሩም” ይላል። ለዚህም በዋናነት የሚጠቀሰው “በቂ አይደለሁም” የሚለው ፍርሃት ሲሆን ሌላው ምክንያት ደግሞ “ምስክርነትና ሰዎችን ወደ ጌታ መጋበዝ የተወሰኑ አገልጋዮች ስራ ነው” የሚለው የተሳሳተ መረዳት እንደሆነ ይታመናል በማለት ጥናቱ ያስረዳል። በማያያዝም ከጥናቱ በመነሳት የአገልግሎቱ መሪ ሲናገሩ “የዳኑ ክርስትያኖች እምነታቸውን ለሌሎች እንዴት ማካፈል እንደሚገባቸው ራሳቸውን ካዘጋጁ ወይም ስልጠና እና ትምህርት ከተሰጣቸው፣ ምስክርነትን ያለማቋረጥ በደስታ ያደርጉታል። በዚህ ተግባራቸውም አስደናቂ የሆነ ውጤትን ያያሉ።” በማለት በአነስተኛ ዝግጅት እና ስልጠና ብዙ ፍሬዎችን ማየታቸውን ይገልጻሉ። “ክርስትያኖች እምነታቸውን እንዴት ለሌሎች ማካፈል ይገባቸዋል?” በሚል ርዕስ ባካሄዱት ስልጠና በርካታ ክርስትያኖች በመንፈስ ቅዱስ በመታገዝ ከፍርሃታቸው ተላቀው የታላቁ ተልዕኮ አስፈጻሚ መሆን እንደቻሉ ይመሰክራሉ። የሆኑ ወገኖችን የሚገጥመው ችግር ሰዎች ለማዳመጥ ያላቸው ጊዜ በጣም አጭር መሆኑ ነው። የምዕራባዊው ዓለም ነዋሪዎች ዘና ብለው ጊዜ በመስጠት ለማዳመጥ ፈቃደኞች አይደሉም። ታድያ መስካሪዎች ለድነት መሰረታዊ የሆኑትን ትም ህርቶች ማለትም፡1.ጸጋ፦ የእግዚአብሔርን ነፃ ስጦታ (ሮሜ 6:23፣ ኤፌ 2:8-9) 2.ሰው፦የሰውን ኃጢአተኛነት(ሮሜ 3:23፣ማቴ 5:48) 3.እግዚአብሔር፦ ጻድቅ፣ ህላዌና ልእልና፣ ፍርድ እና ፍቅር (1 ዮ፤ 4:8) 4.ኢየሱስ ክርስቶስ፦ ፍጹም ሰው፣ ፍጹም አምላክ፣ ስለ ኃጢአተኛው መሞቱና መነሳቱን፣ (ዮ 1:1-14, ኢሳ 53:6) እንዲሁ በማመን 5.ተስፋ፦ የተሰጠንን የዘላለም ሕይወት ተስፋ (ያዕ 2:19፣ ሐዋ 16:31) በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ እነዚህን አምስት መሰረታዊ ነጥቦች አስረድቶ ሰዎችን 8blbBbl8b`8bh8b"H8bixb#8b&8c"bh8bH8b"8bixbxbboBb8b-xbn8c"b*8b8bxch8bixbxbbnboxbH8b8b`b"Bbxbxb`8bmH8bxbxbbH8bhbb*8bxb'H8bh8bb!Bbxb+xb8b*b,boxbxbH8bh8c.8b#bmxch8b8bxb'Bbh8b-xb#xc(8b8b-xb"b"b8c"c 8bH8c"b8b8b+xbaBb8b!b8bhbn8bH8b8b'xbxb*bhH8bb"8b'H8b8bb*bboBb,bxb,8b&xbH8b8bbb+xc(8bxbH8b&8b!8bH8c#xbBbxb"bn8bb#xch8bb"8bxc#xc!xbmH8b#xbxb&8b,8bxb+Bb-xbxb8c(8'8baxb8b,c#bxb#xbh8bmH8b`8b*8b+xbmb'b"bh8bmx'H8bxbxb8b&bhb"8bH8b&8b8c"8b+Bb8b&c"8bhbn8bxbBb`8c)xbl8b¸b8b'xb-xbmBb#8b"bH8b"8b&8b&8b-xb8b+H8cb8b`b8b8bxbxb8blbboxbH8bmxbl8bH8bixbH8c"b