Christian Books & Magazines - Free Berea Magazine 5 | Page 22

ደግሞ በመገረምና በጥርጣሬ ተሞልተው እሺ ዘዴው ምን ይሆን ? በሚል ጥያቄ ያዳምጡታል ። ትንሽ ከጠየቁት ፣ ከድነት ጋር አብረው የማይሄዱ ጥቅሶችን በመጥቀስ አደናግሯቸው የ ዘ ወ ት ር ማ ሳ ረ ጊ ያ ው በሆነው “ ገሃነመ እሳት ትገባላችሁ ” ማ ስ ፈ ራ ር ያ ያጅበዋል ። ማስፈራሪያው የበዛባቸው ሰዎች አሳዬን ከርቀት ሲያዩት አቅጣጫ ይቀይራሉ ። አብሮ ለመቀመጥና ለመወያየት አይመችም ይሉታል ። እነኛ ዓመታት ለአሳዬ ፍሬ አልባ የምስክርነት ጊዜያት ነበሩ ።
ጌታ የተገለጸላቸው አገልጋዮች እንኳን ለጥቂት ጊዜ በመሰወር ራሳቸውን በቃሉ አስታጥቀው ለአገልግሎት እንደወጡ ያልተረዳው አሳዬ መጽሐፍ ቅዱስን በሚገባ ካለማጥናቱና እምነቱን ለማካፈል የሚያግዙ ጥቂት የቃሉን ክፍሎች ካለማወቁ የተነሳ ምስክርነቶቹ ወደ ምትሃታዊ ማስፈራርያ እና ፍቅር የለሽ ክርክሮች በማምራት ይጠቃለሉ ነበር ። ለመታዘዝ ቅን ልብ ቢኖረውም ፣ ምን እንደታዘዘ በደንብ አልተረዳም ነበር ። “ ያላዋቂ ሳሚ …. ይለቀልቃል ” እንደሚባለው ሆኖበት ሰዎች እንዲድኑ ፍላጎት ቢኖረውም ፣ ለድነት የእርሱ ድርሻ ምንድነው የሚለውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሃሳብ አለመረዳቱ አገልግሎቱን አንካሳ አደረገው ።
አሳዬ ፣ አንድ ቀን መጽሐፍ ቅዱሱን ይዞ እየዘመረ ወደ ቤተ ክርስትያን ሲገባ ከአሁን በፊት ሲመሰክርለት ተከራክሮት ከአልተግባባው ሰው ጋር ተገጣጠመ ። ከዚህ ሰው ጋር ለመጨረሻ ጊዜ የተለያየው “ ጌታን ተቀበል ” ሲለው ስለሳቀበት “ አንተ እርኩስ መንፈስ አለብህ ፣ ገሃነመ እሳት ነው
22
የምትገባው ” በማለት በዛቻ እና በቁጣ አስበርግጎት ነበር ።
የዕለቱ ፕሮግራም ሲጀመርም ፣ “ ይህ ሰው ተሳስቶ ይሆናል ወደ እዚህ የመጣው ” ብሎ በአይነ ቁራኛ ተከታተለው ። ሆኖም ሰውዬው በረጋ መንፈስ ፕሮግራሙን ተካፍሎ ከሚያውቀው ወንድም ጋር ወጥቶ ሄደ ። ነገሩን ለማጣራት ምሽት ላይ ይህን ሰው ይዞ ወደመጣው ወንድም ቤት ስልክ ደወለ ። የተደወለለት ወንድምም ሰውዬውን ከስድስት ወራት በላይ እንደሚያውቀውና ይጸልይለት እንደነበርም ነገረው ። ቀስ እያሉ ጥሩ ጉዋደኝነት ለመመስረት እንደበቁና አልፎ አልፎም እየጋበዘው አብሮት ወደ ቤተክርስትያን ይመጣ እንደነበር ገለጸለት ። ከዚያም አልፎ ፣ ያለውን እያካፈለው በችግሩ ይረዳው እንደነበር አስረዳውና በቅርቡም ሰውዬው እራሱ ጌታን ለመቀበል ወስኖ እቤቱ ድረስ እንደመጣና በሚቀጥለው እሁድ ቤተክርስትያን አብረው እንደመጡ ነገረው ። አሳዬ ስልኩን በንዴት ጆሮው ላይ ዘጋበት ። የአሳዬ ንዴት በጌታ ላይ ነበር ። “ እኔ በየመንገዱ ስመሰክር እውላለሁ አንተ ግን ለሌሎች ሰዎችን እቤታቸው ድረስ ትልክላቸዋለህ ”። በማለት አኩርፎ ምስክርነት አቆመ ።
ከስድስት ወራት በሁዋላ እንደገና የመመስከር ፍላጎቱ አገረሸበትና በሺህ የሚቆጠሩ በራሪ ወረቀቶችን ( Flyers ) አሳትሞ በርካታ የሃገሩ ሰዎች በሚያዝወትሩበት ጎዳና ላይ በመቆም ማደል ጀመረና ለሳምንታት እየወጣ ፣ ያሳተመው ፍላየር እስኪያልቅ ድረስ አሰራጨ ። ሆኖም ውጤቱ አሁንም ዜሮ ሲሆን ብዙዎቹ ሳያነቡ ይወረውሩት ነበር ። ከዕለት ወደ ዕለት በሰዎች ላይ ንዴቱ እየጨመረ መጣ ። “ ይህ አመጸኛ ህዝብ የሚያስፈልገው ድምጽ ማጉያ
ነው ” ብሎ በሳምንቱ በድምጽ ማጉያ ሰፈሩን ቀውጢ አደረገው ።
ብዙም አልቆየ “ የማህበረሰቡን ጸጥታ ማወክ ” በሚል ክስ በፖሊስ ተይዞ ወደ ማረፍያ ቤት ተወሰደ ። እስር ቤቱ እንዲናወጥ ሌሊቱን ሙሉ አጥብቆ ቢጸልይም ምንም ተዓምር ሳያይ ሌሊቱ ነጋ ። ጠዋት ላይ ወገኖች ዋስ ሆነው አሳዬን አስፈቱት ። ዋስ የሆኑለት ወገኖች በምስክርነቱ እንዲገፋበት አልደገፉትም ። አንዳንዶች ጸልይበት ሲሉት ሌሎች ደግሞ በድፍረት “ መጀመርያ ቁጭ ብለህ ተማር ” በማለት ገሰጹት ። አሳዬም የጌታ ፈቃድ አይደለም ፣ ይህ ሰዎች የማይሰሙበት የመጨረሻው ዘመን መሆን አለበት በማለት ምስክርነትን ለዓመታት አቆመ ።
“ አንዴ የተመታ ሁለቴ ይፈራል ” እንደሚባለው አሳዬ በመንፈሳዊ ሕይወቱና በቃሉ እውቀት እያደገ ቢመጣም እንደ አብዛኛው የዘመኑ ክርስትያን ለሌሎች ለመመስከር ፍርሃት ያዘው ። አሳዬ ፣ ራሱ ይዞት የተነሳው የራሱ ሕልም ነበረው ፣ ለዚያ ሕልም ደፋ ቀና እያለ ሳይታክት በየመንገዱ መሰከረ ፣ ያ ሕልም ግን ዋጋ አስከፍሎታል ። አሁን ፣ ቀደም ባሉት ዓመታት ያጠፋው ጥፋት ቀስ እያለ ገብቶታል ። ይሁንና ለመመሰከርና ሰዎችን ወደ ጌታ እንዲመጡ ለማድረግ የተለየ ጥረት ግን አልነበረም ።
ጥቂት ዓመታት ካለፉ በኋላ ለብ ያለውና ለነፍሳት ግድ ያልነበረውን የአሳዬ ሕይወት በድንገት የሚቀይር አጋጣሚ ተፈጠረ ። ለሶስት ቀናት የተሰጠው “ እምነታችንን ለሌሎች እንዴት እናካፍል ” የሚለው ትምህርትና መነቃቃት ለአሳዬ ትልቅ ለውጥ አመጣ ። አሳዬ ንስሃ ገባ ። አምላኬና ጌታዬ ብሎ የተቀበለው ኢየሱስ የስራው