Christian Books & Magazines - Free Berea Magazine 5 | Page 21

ሕይወት ቢመሰክር

ከወንድም ኮነ ፍሰሐ

ስለ ክርስቶስ መጠላትን በትንሹ ለመቅመስ በሰሜን አሜሪካ ጎዳናዎች ላይ ለምስክርነት መውጣት በቂ ነው ። በጥቂት ሰዓት ውስጥ ጥላቻ ፣ ስድብና ግልምጫ ይፈራረቁባችኋል :: አላዋቂ ሁዋላቀር ትባላላችሁ ፡፡ በዚያው መጠን ደግሞ ከባህር ማዶ መጥታችሁ ወንጌልን በአደባባይ መመስከራችሁ ከብዙዎች አድናቆትን እና ፈገግታን ያተርፍላችኋል :: ሆኖም ብዙዎች ተስፋ ቆርጠው ወደ ኋላ አፈግፍገው ወደ ተዉት ወደዚህ ጥሪ ከመሰማራትዎ በፊት ፤ ስራው ባለቤት እንዳለውና ባለቤቱ ማን እንደሆነ ተረድተው ፤ በቃሉ እውቀት እንዲታጠቁና ጸጋው እንዲበዛልዎት ጸልየው ፣ ከዚህም በላይ ለስራው ባለቤት ለመታዘዝ ፈቃደኛ መሆንዎን ማረጋገጥ የማይታለፍ ዋነኛ ጉዳይ ነው ። የዚህ ጽሁፍ ዓላማ በመለኮታዊ ምሪትና በጽናት ጎዳና ስለተጓዙ መስካሪዎች ሕይወት መናገር ቢሆንም ፣ ወደዛ ደረጃ ለመድረስ ያለውን ተግዳሮት ማንሳቱና ስህተቱን መንቀሱ በዛ ያለውን ድርሻ ይዟል ።

የወንጌል ምስክርነት ዋናው ቁልፍ ኃይልን በሚሰጠው በክርስቶስ ተደግፎ የማዳኑን ጸጋ ለሌሎች ማድረስ ነው ። መታዘዙ የእኛ ድርሻ
ሲሆን የውጤቱ ጉዳይ ደግሞ ሰዎችን ወደራሱ የሚጠራው የስራው ዓለቃ ( የባለቤቱ ) ሃላፊነት ነው ። ሆኖም ለስራው ባለቤት መታዘዝና “ በኅይሉ ችሎት ” መደገፍ ካልቻልን ሰዎች ወንጌልን ላለመቀበላቸው የማይመስል ምክንያት እየሰጠን ዘመኑን መዋጀት ሲገባን ፣ ችግር ተራኪ ጋዜጠኛ ሆነን እንቀራለን ። በብዙ ወኔ ተሞልተውና በከፍተኛ ስሜት ተነሳስተው ፤ ነገር ግን ብቻቸውን ወጥተው አንድም ሳይማርኩ የተመለሱ ብዙ ናቸው ። ከጌታ ጋር አብረው ወጥተው ዘርን ዘርተው ሌላም ማርከው የሚመለሱም በርካቶች ናቸው ። የሰዎችን ጆሮ እንጂ ልብ አለማግኘቱ አማሮት ከምስክርነት አገልግሎቱ ተለይቶ የነበረው የአሳዬ ገጠመኞች ለሁላችንም ትምህርት ይሰጡናል ።
የሰሜን አሜሪካ ነዋሪ የሆነው አሳዬ በመጀመርያው የምስክርነት ዓመታት ሰዎችን መስክሮ ከማምጣት ይልቅ እንዲሸሹ ያደረገባቸውን ሁኔታዎች ሲያስብ በጣም ይገረማል ። ከአስር ዓመታት በላይ ባስቆጠረው የክርስትና ጉዞው በመጀመርያዎቹ የሞቅታ ዓመታት ውስጥ ስንት ሰው ወደ ጌታ አመጣህ ? ብትሉት ፣ ካመጣሁት ይልቅ ያባረርኩት ይበልጣል ቢላችሁ ልትደነግጡ ወይም አማኝ መሆኑን ልትጠራጠሩ ትችላላችሁ ።
በነዚያ የክርስትናው የመጀመርያ ዓመታት የነበረው የመመስከር ፍላጎቱና ድፍረቱ ከፍተኛ ቢሆንም ፣ ፍሬ ያልታየበት ነበር ። የዚህም ምክንያቱ በቃሉ ብስለት ያልነበረውና በጸሎት ያልተደገፈ መሆኑ ነው ። እርሱ በደንብ ያላወቀውን ጌታውን ለሌሎች ለማሳወቅ ሩጫ የጀመረው ጌታን በተቀበለ በወሩ ቢሆንም የስራውን ባለቤት ለምን ጠራኸኝ ? ምን ልታዘዝ ? ብሎ አልጠየቀም ። ወደ ራሱ የጠራውን ጌታ ከተደበቀበት ፈልጎ ያገኘው ይመስል ለሌሎች ለማሳየት ቸኩሎ ነበር ። አሳዬ ኢየሱስን “ ጌታዬና አምላኬ ” ብሎ እንደተቀበለው አላስተዋለም ። በራሱ ኃይል ተደግፎ ነበር አገልግሎት የጀመረው ። ሆኖም በውጤቱ ሰዎች እሱን እንዲመለከቱ አደረገ እንጂ ማንንም ወደ ጌታ አላመጣም ። እስቲ ጥቂቶቹን የአሳዬን የየዋህነት ዘመንና የምስክርነት ገጠመኞች እንመልከት ።
ለአሳዬ የመጀመርያው ችግሩ ምስክርነቱ “ ጌታ ከእንደዚህ አይነት ችግር ውስጥ አውጥቶ እንደዚህ አይነት ስኬት ላይ አደረሰኝ ” በሚል ግለ ታሪክ ላይ የተመሰረተ መሆኑ ነበር ። ብዙዎች ሰሚዎቹ “ እንኩዋን ደስ ያለህ !” በሚል ምላሽ ያቆማሉ ።
በዓለም ኑሮ የተሳካላቸው እየሳቁበት ሲሄዱ ፣ ያልተሳካላቸው
21