Christian Books & Magazines - Free Berea Magazine 5 | Page 20

መልእክት ካለህ ?
ፓ / ር አህመድ ፦ በመጨረሻ ለቤርያ አገልጋዮች እና ተጠቃሚዎች የማስተላልፈው መልዕክት : ስለቤርያ በጥሩም በመጥፎም ከሰዎች ሰምቼ ነበር ። አሁን ግን ይበልጥ እያወቅሁ ስመጣና ሰዎች እየዳኑና እየተማሩ ሲመጡ ሳይ ፣ የእግዚአብሄርን ስራ አየሁ ። በብዛት ወደ ቤርያ የሚገቡትን ተገልጋዮች ሳይ ደግሞ የእግዚአብሔር እጅ እና አጀንዳ ያለበት መሆኑን አውቄአለሁ ። እዚህ ውስጥ የምታገለግሉትን ሁሉ በትክክለኛው የእግዚአብሔር አጀንዳ ውስጥ ስላላችሁ ይህንን አገልግሎት በትጋት እንድትቀጥሉና እንድታገለግሉ አበረታታችኋለሁ ።
በዚህ ዘመን ላላችሁ ቅዱሳን ሁለት መልእክቶችን ማስተላለፍ እወዳለሁ ። 1ኛ ክርስቶስ ቤተክርስትያንን የተከለበት ዓላማ የጠፉትን ለመፈለግ ነው ። ቤተክርስትያን ትልቁ አጀንዳዋ መሆን ያለበት ወንጌልን ወደ አልተዳረሰው ማድረስ ነው ። በሳምንት አንድ ቀን ስለከተማችሁና ህዝቡ ብትጾሙና አንድ ሰዓት በቀን እየጸለያችሁ አንድ ነፍስ በዓመት ወደ ጌታ ብታመጡ እንዲሁም

ከእህት ሰላማዊት ገ / መድህን

ወንጌልን ለማገልገል የሚማርን አንድ ሰው ብትደግፉ ትልቅ ስራ በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ ታደርጋላችሁ ።
2ኛ . እግዚአብሔር የሰጠንን አገልጋዮች ብናከብርና ብንሰማቸው እግዚአብሔር ጨምሮ ሌሎችንም ይሰጠናል ። አንድ ጊዜ የተነሱትን ተቀባብለን ተጠቅመንባቸው ቁጭ አናድርጋቸው ። ነገር ግን ሲደክሙ እንጸልይላቸው ፣ ሲያጠፉ ደግሞ አባቶች የሆንን እንምከር እንገስጻቸው ። ከዚያም ደግሞ በፍቅር እንያዛቸው ።
አገልጋዮች የሆንን ደግሞ ቢቻለን የሚመክረንና የሚያሳድገን የወንጌል አባት እና መካሪ ቢኖረን በጣም ጥሩ ነው ። ሳንመከርና ሳንገሰጽ ዝም ብለን በራሳችን ብቻ ያደግን ባንሆን መልካም ነው ። በተረፈ ወንጌል ለሁሉም ሁሉም ለወንጌል እንዲነሳ ጥሪዬን እያስተላለፍኩ ጊዜህን ወስደህ ቃለ መጠይቅ ስላደረግህልኝ እግዚአብሔር ይባርክህ እላለሁ ። ለቤርያዎች ሁሉ እጸልያለሁ ።
ፓ / ር አህመድ አላ
ለክብሩ ይወራ !
“ አዋጅ ፣ አዋጅ ” ተብሎ ሲወራ ውድቀቴ እልልታውን ሲያቀልጥ የድነት ጠላቴ ከሳሽ ሲጠቋቆም ልብሴን አሳድፌ ፤ ጻድቃን ሲተክዙ ስሙን አስነቅፌ ፣
ያወደሱኝ ሁሉ ሲጸየፉ አይቼ ፤ አከተመ አልኩኝ ዙሪያዬን ሰምቼ ፣ በጨለማ ጎጆ በተከርቸም በሬ ፤ በሃዘን ተውጬ ስተክዝ በነውሬ ፤ ጌታ ዘለቀና ዘረጋልኝ እጁን ፤ ምንስ ይለካዋል ጸጋ ምሕረቱን ።
በጸጸት ወቀሳ ሙግት ተከብቤ ፤
በደሌ ሳያንሰው ስሙን ማሰደቤ ፤ ጸጋ ጨመረልኝ ስሙ እንዲጠራ ፣ እናም መነሳቴ ለክብሩ ይወራ ።
ፓ / ር ወርቁ ለገሰ
20
ሁሉ ቢሟላልኝ ቢትረፈረፍ ቤቴ በዓለም ብልጭልጭ ሞልቶ ፍላጎቴ በትምህርት ቀልሜ በችሎታ አምሬ ብዙዎችን ሲያጓጓ እንደዚህ መኖሬ ታዲያ ምነው ጠፋኝ የኑሮ ትርጉሙ ስኬታማ የመሆን የመትረፍረፍ ጥቅሙ ዓላማ አስፈለገኝ ለመግፋት ሕይወትን ወድጄ ፈቅጄ የምሰጥለትን አሁን ተገለጠ በራልኝ እውነቱ የጌታ የመሆን ትርጉም ሚስጥራቱ እኔ የእኔ የለም ሁሉ በእርሱ ነው እኔ የሱ ውጤት እርሱም ሰሪዬ ነው
አትንኩኝ ማለትን መኩራራቴን ትቼ መውጣቴን መግባቴን ለእርሱ ሰጥቼ እንደ አምባሳደር ልክ እንደ እንግዳ ትቼው እንደምሄድ ሁሉንም በሜዳ መውጣቴ መግባቴ አንደበት ሃሳቤ ተግባር ጊዜያቴ ንብረቴና ሃብቴ ለጌታ ክብር ይሁን ብየ ካስረከብኩት ለእርሱ ለመኖር እጄን ከሰጠሁት ክብርም ቢመጣ ከፍ ከፍ የሚያደርግ መከራም ቢከተል እጅግ የሚያስጨንቅ መዋረድም ቢሆን መመስገን ለእርሱ ነው የእኔ የምለው የለም ሁሉምየእርሱ ነው ።