Christian Books & Magazines - Free Berea Magazine 5 | Page 19

እና ሌሎች ቤተ ክርስትያናትን እየተከልን እና ወንጌላውያንን እየረዳን ነበር ። እዚህ አገር ትላልቅ ህንፃ የሰሩ ለህንፃው በሚያስፈልግ ወጪ ተወጥረው የወንጌል አገልግሎት የላቸውም ። ትኩረቱ ወንጌል መሆኑ ቀርቶ ህንፃቸውን በሰው መሙላት እና ገንዘብ ላይ ሆኗል ።
3
እግዚአብሔር
ለቤተ
ክርስትያን የሰጠውን ጸጋ ተቀብሎ
አለመጠቀምን
አያለሁ ።
በብዛት
የምናያቸው
አገልጋዮች
ፓስተሮች
ብቻ
ናቸው ።
አስተማሪዎች
እና
ወንጌላውያንን
አናይም ።
በአንድ
ቤተክርስትያን
አምስት
አገልጋዮች
ቢኖሩ አምስቱም ፓስተሮች ናቸው ።
ከስጦታ ይልቅ ወደ ስልጣን ( Position
) ሄደናል ። ፓስተርነት ( መጋቢነት )
የእግዚአብሐር ስጦታ መሆኑ ቀርቶ
ቦታ ወይም ስልጣን ሆኗል ። አገልጋይ
የተሰጠውን ቢሆንና በእግዚአብሔር ጸጋ
ብቻ ቢገለጥ መልካም ነው እላለሁ ።
4
ተቀባብሎ
እየተራረሙ
መስራት
በመሃከላችን
የለም ።
መከፋፈልና
አለመደጋገፍ
በብዛት
ይታይባታል ።
ከዚህም
የተነሳ
ሌሎችን
በመደገፍ
በአካባቢያችን
የሚተከሉ ቤተክርስትያናትን ስትረዳና
ስትደግፍ አትታይም ። የአሜሪካውያን
ቤተክርስትያናት እሩቅ ድረስ በመሄድ
ለወንጌል መስፋፋት ሲረዱ የእኛ ግን
አጠገባችን ያሉትን እንኩዋን ለመርዳት
ፈቃደኛ አይደለችም ። ይህ ሌላው
ትልቁ የብዙዎቹ ተግዳሮት ነው ብዬ
አስባለሁ ።
ቤርያ ፡ -የስነ መለኮት ትምህርት ቤትና ስልጠና የመጀመር ዓላማ እንዳለህ ነው ። ለመሆኑ ለሕይወት ለውጥና ለወንጌል መስፋፋት ጥቅሙ ምን ያህል ነው ? ጸጋ ካለ በቂ ነው ፣ የሚሉ ወገኖች በአንድ በኩል ፣ ጸጋ በትምህርት
ካልታገዘ ከአስተምሮ መዛነፍ እስከ መሳት ሊያደርስ ይችላልና ሁሉም ይማር የሚሉት በሌላ በኩል ተሰልፈዋል ። በሁለቱ መካከል ያለውን እንዴት እንዳኘው ?
ፓ / ር አህመድ ፦ ጸጋችን በእውቀት ይደገፍ ። ጸጋ በእውቀት ካልተደገፈ የምናገለግለው ህዝብ እውቀት አልባ ይሆናል ። ጸጋ ስጦታ ነው ፣ ጸጋ የተሰጣቸው እውቀትን ለመማር ፈቃደኛ ቢሆኑ ለአገልግሎታቸው እጅግ መልካም ነው ። በብዙ አገልጋዮች ቃሉ ያለአውዱ እየተጣመመ ሲተረጎም በብዙ ኮንፍረንስ እና ቴለቪዥን ላይ ሳይ አዝናለሁ ። ቅባቱ አላቸው ግን እውቀት የላቸውም ፣ አልተማሩም ፣ በአብዛኛው ስሜታውያንና የልምድ አገልጋዮች ናቸው ። ስለዚህ እግዚአብሔር ጠራኝ ፣ ጸጋው አለኝ ፣ የሚሉና እግዚአብሔርን አገለግላለሁ የሚሉ ሁሉ እውቀት የሚያገኙበትን መንገድ እንዲፈልጉ እመክራለሁ ። ሌላው ደግሞ ተምረናል ዕውቀቱ አለኝ ለምንል ሰዎች ነው ። ቅባት ከእውቀት አይገኝም ፣ ቅባት የሚገኘው በጸሎት በልመና ከመንፈስ ቅዱስ ነው ። ዝም ብዬ የቲዮሎጂ ዶክትሬት አለኝና ዕውቀት አለኝ ብል ዕውቀት ብቻ ነው ።
መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚል ፊደል ይገላል ። ቅባት እና የጸሎት ህይወት ከሌለኝ ዝም ብሎ እውቀት ብቻ ይሆናል ። ስለዚህ ሳይማሩ በቅባት ብቻ የሚያገለግሉትን እንዲማሩ ብናበረታታቸው ጥልቀትና ብስለት ያለው ክርስትና ይኖረናል ብዬ አምናለሁ ። ለዚህም ይመስለኛል በክርስትና ብዙ ዓመታት አሳልፈን አሁንም ከራሳችን አልፈን ሌሎችን መድረስ ያልቻልነው ። ለምሳሌ በአፓርትማ ውስጥ ብዙ ሰዎች እያሉ እኛ ለማገልገል የምንፈልገው ጥቂት ሃበሻን ብቻ ነው ። ይህ ያለማደግ ምልክት ነው ።
ቤርያ ፡ - በአገልግሎት የነበሩና ከፍተኛ የስነ መለኮት ትምህርትን ለተማሩ ወንድሞች የሰሜን አሜርካዋ የኢትዮጵያውያን ቤተክርስትያን በሯ ዝግ ነው :: ተምረው ሊያገለግሉን ላልቻሉት እና እነዚህን የተማሩ የስነመለኮት ሊቆች ወደ አገልግሎት ለማሰማራት ፈቃደኛ ያልሆኑትን የቤተክርስትያን መሪዎች ምን ትመክራለህ ?
ፓ / ር አህመድ ፦ እኔ የማምነው የአገልግሎትን በር የሚከፍተው ጌታ ኢየሱስ ነው ። ሌላ ማንም ሊከፍት ወይም ሊዘጋ አይችልም ። በእኔ ላይ ቅባት ካለ በሩ ይከፈታል ። ሌላው የወንጌል ስራ በየቦታው ነው ። ሊያገለግሉ ለሚወዱ ሁሉ በጣም ብዙ ክፍት በሮች አሉ ። በሌላ በኩል ደግሞ ከፍርሃት የተነሳ እግዚአብሔር በመሃከላችን ያስነሳቸውን አገልጋዮች ሳንጠቀም ስንቀር ቤተክርስትያን ትጎዳለች ። እኔ አሜሪካን ከመጣሁ አንድ ቀንም በር ክፈቱልኝ ብዬ አላውቅም ፣ አልጠይቅምም ፣ ምክንያቱም በየመንገዱ በየሰዉ ቤት ብዙ አገልግሎት አለ ። ቤተክርስትያን ተከላ ውስጥ ብዙ ስለሰራሁ አሁን ያሉት ቤተክርስትያኖች በቀላሉ እዚህ አልደረሱም ። በብዙ ድካም ነው አሁን ያሉበት የደረሱት ። በቤተ ክርስትያን ጸጋው ኖሯቸው ቦታ ሳይሰጣቸው ለተቀመጡ ደግሞ ለመድከም ፣ ለመዝራት ፣ ለመትከል ቢነሱ እና ቢደክሙ መልካም ነው ። ሳይደከም ለምን የአገልግሎት መድረክ አልተሰጠኝም ማለት አይቻልም ። የወንጌል ስራ በጌታ ክርስቶስም እንዳየነው እንባ አለው ፣ ላብ ወይም ድካም አለው ፣ መጨረሻም ላይ ክብር አለው ። ስለዚህ ለመድከም መጀመርያ ፈቃደኞች እንሁን ፣ ክብር በመጨረሻ ይመጣል ።
ቤርያ ፡ -በመጨረሻ
ለቤርያ
ተጠቃሚዎችና አገልጋዮች እንዲሁም
ለቅዱሳን
የሚተላለፍ
የጊዜው
19