Christian Books & Magazines - Free Berea Magazine 5 | Page 18

አሜሪካን ሊጋብዘኝ እንደሚፈልግና አሜሪካን አገር በመምጣት እንዳገለግል ሁሉን ነገር እንደሚያዘጋጅ ገለጸልኝ ።
እግዚአብሔር ተናግሮኝ ስለነበር ለሞያሌ ቤተክርስትያን 7 ፓስተሮችና 4 አስተማሪዎች ተሹመው ነበር ። እግዚአብሔርም አሜርካን መጥቼ ቤተክርስትያን እንደምተክል እና ወንጌልን እንደ ማሰራጭ በተለያዩ ወገኖች እያረጋገጠ በተደጋጋሚ ነግሮኝ ስለነበር የጥሪውን ግብዣ ተቀብዪ ወደ አሜሪካ ለመምጣትና ለማገልገል ወሰንኩ ። ዓላማዬም ሁለት ነበር ፥ አንደኛው ወንጌልን በአገኘሁት አጋጣሚ ሁሉ መስበክ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ እግዚአብሔር ቢፈቅድልኝ የማስትሬት ዲግሪ መማር ነበር ። እግዚአብሔርም ረድቶኝ እንደመጣሁ በ SOUTH FLORIDA የባፕቲስት ኮሌጅ መማርና ለአሜሪካውያን የቤት ለቤት የምስክርነት አገልግሎት ጀመርኩ ፣ በሰባተኛ ወሬም በፍሎሪዳ ዋና ከተማ በታላሃሲ የአማርኛና የእንግሊዘኛ ፕሮግራም ያላት ኢንተርናሽናል ቤተክርስትያን ለመትከል በቃሁ ። ቤተክርስትያን በአንድ ሃገር ወይም ህዝብ መጠራት የለባትም የሚል ትልቅ አቋም ድሮም ስለነበረኝ የምተክለው ቤተክርስትያን ሁሉ ከሃገር ከቋንቋና ከዘር ያለፈ ኢንተርናሽናል ቤተክርስትያን ነው ። የታላሃሲ ቤተክርስትያን መሪዎችም ከኬንያ ፣ ከኢትዮጵያ ፣ ከኤርትራና ከአሜሪካን በአንድነት የተውጣጡ ነበሩ ።
ቤርያ ፡ - በሰሜን አሜሪካን በአንተ አገልግሎት የተተከሉት ቤተክርስቲያኖች ምን ደረጃ ላይ ነው ያሉት ? በእነዚህ ዓመታት ውስጥ ራዕይህ በምን አቅጣጫ ሰፍቶልሀል ?
ፓ / ር
አህመድ :
አሁን
እግዚአብሔር
ረድቶን
አራተኛው
18
ቤተክርስትያን በሂዩስተን ተተክሏል ። በተለያዩ ከተሞች የወንጌል ስርጭት ዘመቻዎችና ኮንፍረንስ አደርጋለሁ ። ቶሮንቶ ፣ ዋሽንግተን ፣ ኮሎምበስ ፣ ቺካጎ ፣ ሻርለት ፣ ቴነሲ ፣ ማያሚና ነውዮርክ ላይ አድርገናል ። እግዚአብሔር አሁን የሰጠኝ ራዕይ 1-1-1 የሚል ነው ፣ ይህም አንድ ቀን በሳምንት መጾም አንድ ሰዓት በቀን መጸለይ አንድ ነፍስ በዓመት ወደጌታ ማምጣትና አንድ ሙሉ ጊዜውን የሰጠ የወንጌል አገልጋይን በጸሎትና በምንችለው መደገፍ የሚል ነው ። ይህንን ራዕይ በማስፋት በሚቀጥለው አምስት ዓመት በአሜሪካን በሱዳን በኢትዮጵያ በኬንያና በታንዛንያ 50 ቤተክርስትያኖችን ለመትከል እና 50 ወንጌላውያንን በመጀመርያ ዲግሪ አስመርቆ ለማሰማራት እግዚአብሔር በ2014 የሰጠኝን ሃላፊነት እየሰራሁ ነው ። ጌታ አስቀድሞ የሰጠኝን ራዕይ አሁን አሜሪካንን ጨምሮ በአምስት ሃገሮች ላይ ለማድረግ ነው ። እግዚአብሔር ረድቶን አሁን የቤተሳይዳ ዓለምአቀፍ የወንጌል አገልግሎት ኮሌጅ ከ Vision International Ministry ጋር በመተባበር በነፃ ጀምረናል ። 22 ተማሪዎች ለአሶሽዬት ዲግሪ እየተማሩ ሲሆን ቤተክርስትያን ተካይ ዘጠኝ ወንጌላውያንንም ለሚሽን አሰማርተናል ። በሚቀጥሉት 10 ዓመት ውስጥ ደግሞ
250 ቤተክርስትያን ለመትከልና ጌታ ቢፈቅድ 100 ወንጌላውያንን በአምስቱ አገሮች ውስጥ ለማሰማራት እየተጋን ነው ።
ቤርያ ፡ - በሰሜን አሜሪካን ያሉ የኢትዮጵያውያን ቤተክርስቲያናት ተግዳሮት ምንድነው ታስባለህ ?
ፓ / ር
አህመድ ፦
አራት
ተግዳሮቶችን
በሰሜን
አሜሪካን
የኢትዮጵያውያን ቤተክርስትያን ላይ
አያለሁ ።
1 ስግብግቦች ሆነናል ። ትኩረታችን ሃበሻ እና ኢትዮጵያ ላይ ብቻ ሆኗል ። ስለ ኢትዮጵያ ማሰቡ መልካም ነው ። የመጀመርያዎቹ ሐዋርያት ወደ አንጾኪያ ፣ ቱርክ ፣ ግብጽ እና አውሮፓ ወንጌልን ይዘው ባይሄዱ ኖሮ ወንጌል አይስፋፋም ነበር ። እኛ ግን ወንጌል ከተቀበልን የቆየን ቢሆንም አሁንም ወደ ሌሎች ይዞ መሄድ የሚል ራዕያችን ውስን ነው ።
2 ሚዛኑን ጠብቀን ወንጌልን አብረን ማሰራጨት ሲገባን ትልቁ ትኩረታችን ህንፃ ላይ ሆንዋል ። ለምሳሌ እኛ 4000 ሰው የሚይዝ ቤተክርስትያን ስንገነባ የአስር ዓመት እቅድ አውጥተን

“ እግዚአብሔር አስቀድሞ የሰጠኝን “ የራስህን ባንዲራ አታውለብልብ ” የሚለውን መመርያ በመከተል የራሴ ወይም የእኛ የምንለው ቤተክርስትያን አንተክልም ነበር ።”

ፓ / ር አህመድ አላ

ጎን ለጎን ወንጌልን እያሰራጨን