Christian Books & Magazines - Free Berea Magazine 5 | Page 17

ሰዎችን ደርሰን ወደ 2500 ሰዎች ወደ ጌታ መጡ ። ከዚያም “ የእግዚአብሔር እሳት በጠረፍ ከተሞች ” የሚል መጽሔት አሳተምን ።
ቤርያ : በአገልግሎቱ ውስጥ ከገጠማችሁ ተቃውሞ እና መከራ እስቲ ጥቂቱን አካፍለን ።
ፓ / ር አህመድ : በሶስተኛው ዓመት ነጌሌ ቦረና ላይ ከየአጥቢያው የተውጣጡ 100 አገልጋዮችን ይዘን ነበር ዘመቻውን የጀመርነው ። የማልረሳው ፥ አንድ ጠዋት በተመደበበት አካባቢ ሊያገለግል የወጣ ወንድም አናቱን በጦር ተወግቶ ደም በደም ሆኖ እየሮጠ መጣና ሌሎች አብረውት የተላኩትንም ሁለት ወንድሞች ቀጥቅጠው እንደ ገደሉዋቸው ነገረን ። እኛም እየሮጥን ወደ ስፍራው ሄድን ። ፖሊስ መጣና ስብከቱን አቁሙ ተባልን ። ተሰብስበን የልጁን ደም ይዘን “ የእኛ ደም እንዲሁ በከንቱ ፈሶ አይቀርም ፣ የቅዱሳን ደም የቤተክርስትያን ዘር ነው ተብሏል ስለዚህ እግዚአብሔር ሆይ ተመልከት ብለን ” በሃይል ጸለይን ። ጸልየን ስንጨርስ ስልክ ይፈልግሃል ተባልኩ ፣ ስልኩ ከኢትዮጵያ ወንጌላውያን ሕብረት የወንጌል ስርጭት ዳይሬክተር ከዶ / ር ጣልአርጋቸው ነበር ። “ በምትሰሩት የወንጌል ስርጭት እጅግ ስለተደሰትን ሕብረቱ ለወንጌላውያን ድጋፍ ማድረግ ይፈልጋል ፣ ስለዚህ ለአስር ወንጌላውያን ድጎማ ( ደመወዝ ) እንሰጣለንና ስማቸውን አስታውቀኝ ” የሚል ነበር ። በጣም ደስ አለን ። ምክንያቱም መስክረን ወደ ጌታ የምናመጣቸው በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች በሚቀጥለው ዓመት ላይ ስንሄድ የሚከታተላቸው ባለመኖሩ ወደ ዓለም መመለሳቸው ያሳስበን ስለነበር ነው ። ከዚህ የነገሌ ቦረና መከራ ውስጥ ስናልፍ እግዚአብሔር በነዚህ አስር ወንጌላውያን ድጋፍ ጀምሮ ወደ ቤተክርስትያን ተከላ
እንቅስቃሴ አሳደገን ። እግዚአብሔር አስቀድሞ የሰጠኝ “ የራስህን ባንዲራ አታውለብልብ ” የሚለውን መመርያ በመከተል የራሴ ወይም የእኛ የምንለው ቤተክርስትያን አንተክልም ነበር ። የሚተከሉት ቤተክርስትያኖች ሁሉ በቅርብ ባለው ቤተክርስትያን ስር በመሆን ነበር የሚያገለግሉት ። ስንሰራም አንድ አካባቢ መቶ ሰው ይሄዳል ፣ ስምንቱ ከተማ ውስጥ የወንጌል ክሩሴድ ያደርጋሉ ፣ ማታ ማታ ደግሞ ፊልም ያሳያሉ ። ሌላውን 90 ሰው አራት አራት እያደረግን በመኪና ወደ ገጠር እንወስዳቸዋለን ። ከወር በሁዋላም እናመጣቸዋለን ። በዚህ ዓይነት ለሰዎች ወንጌል እየሰበክን የሚያስፈልጉ አጥቢያ ቤተክርስትያኖችን እንተክል ነበር ። ሆኖም የምናገለግለውን የገጠሩን የቦረና ህዝብ በቁዋንቋው ሊያገለግሉ የሚችሉ አገልጋዮች በኬንያም ሆነ በኢትዮጵያ በኩል ማግኘት አልቻልንም ነበር ። ስለዚህ ነዋሪውን ለሚያገለግሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ቤት መክፈት በማስፈለጉ ” አንጾኪያ የሚሽን ትምህርት ቤት “ በሞያሌ ላይ ከፍተን ከየአጥቢያው የማገልገል ጥሪና ፍላጎት ያላቸውን እያመጣን ሙሉ ወጪያቸውን በመሸፈን ለአንድ ዓመት ማሰልጠን ጀመርን ። ስለጸሎትና ስለጾም ፣ ስለወንጌል ተልእኮ ፣ ስለ ስነ መለኮት ፣ ስለ ሚሽን እየተማሩና በተግባርም እያገለገሉ በሳምንት አምስት ቀን እየጾሙ ከ2002 እስከ 2008 ድረስ
ብቻ 120 ወንጌላውያንን አሰልጥነን በማሰማራት 75 አጥቢያዎችን ተከልን ። በ2008 ላይ የመጨረሻውን “ የአንድ ወር ለክርስቶስ ” የወንጌል ዘመቻን ያካሄድነው በ298 አገልጋዮች ነበር ። ለዚሁ የወንጌል ዘመቻ ከሻሸመኔ ድረስ የመጡ አገልጋዮች ተሳትፈው ነበር ።
ቤርያ ፡ - እንዴት ወደ ሰሜን አሜሪካን መጥተህ ወደ አገልግሎት ልትገባ ቻልክ ? አሁንስ በምን መልኩ ነው የምታገለግለው ?።
ፓ / ር አህመድ : - በ2003 ላይ እግዚአብሔር ያሳየኝ 4000 ሰዎች የሚይዘውና ከ 5 እስከ 7 ሚልዮን ብር የሚፈጀው የሞያሌ ቤተክርስትያን በእምነት ተጀመረ ። እኔም በደቡብ ኢትዮጵያ ፣ ሰሜን ኬንያ ፣ ዩጋንዳ ፣ ታንዛንያ ፣ ደቡብ ሱዳን ፣ ሩዋንዳ እና ቡሩንዲ ድረስ የሚሽን ቡድኖችን በመያዝ እየሄድኩ ተመሳሳይ የወንጌል ዘመቻና ቤተክርስትያን ተከላ አደርግ ነበር ። ለአስር ዓመታት ከአገለገልኩ በሁዋላ አስቀድሞ “ ያሳየኝን የሞያሌ ቤተክርስትያን ሰርቼ ሲያልቅ እንደምሄድ ” የተናገረኝ እግዚአብሔር እንደገና ይናገረኝ ጀመር ። የህንጻው 80 % ተሰርቶ እንዳለቀ እግዚአብሔር ሂድ አለኝ ። ናዝሬት ላይ ላገለግል ተጋብዤ በስፍራው ላይ ከአንድ የውጪ አገር ዜጋ አገልጋይ ጋር ተዋወቅሁ ። አገልጋዩም ሙሉ ወጪውን ችሎ ወደ
17