Christian Books & Magazines - Free Berea Magazine 5 | Page 15

የተሰባጠረ ሕይወት ዝም ብዬ ቀጠልኩ ። ለንግድ በምመላለስባቸው የጠረፍ ከተሞች ሁሉ ቃል በማካፈል አገለግላለሁ ። አንድ ቀን አገረ ማርያም የሚባል ከተማ ላይ ቃል ለማካፈል ቀጠሮ ተይዞልኝ እኔ ግን ረስቼው ከሰራተኞቼ ጋር ጫት እየቃምሁ ሳለ ትውስ አለኝ ። ወድያው ተነስቼ ወደ ተጋበዝኩበት ስፍራ በፍጥነት ሄድኩ ። ጫቱን በር ላይ ተፍቼ ለአገልግሎት ገባሁ ። ይህንን የምነግርህ ሰዎች ጌታን በመቀበልና በቅድስና በመመላለስ መሃከል ያለውን ልዩነት እንዲረዱኝ ነው ። ገብቼም ኢሳያስ 5 ስለ ወይኑ ግንድ አውጥቼ መስበክ ጀመርሁ ። በታላቅ የመንፈስ ቅዱስ መነቃቃት መሃከል አንዲት እህት ተነስታ ትንቢት መናገር ጀመረች ። እኔም ታላቅ ፍርሃት ወደቀብኝና ተንበረከክሁ ። እሷም “ መልካም የሆነ እግዚአብሔርን የምታገለግል ወንድም ፣ መለወጥ እንጂ ማጋለጥ የማይወድ እግዚአብሔር ፣ ሰው ማዋረድ የማይወድ እግዚአብሔር ፣ ለምን ትረክሳለህ ? ለምንድነው የምትረክስብኝ ? አንተ እኮ ለእኔ የተመረጥክ ፣ የተቀደስክ እቃ ነህ ፣ እኔ ለራሴ መርጨሃለሁ ። ለምንድነው የምትረክስብኝ ” ይልሃል ብላ በጉባኤ መሃል ተነስታ በአጠገቤ ቆማ ትንቢት ስትናገር ለእኔ እንደሆነ ተረድቼ በታላቅ
ፍርሃት ንስሃ በመግባት ከምሄድበት አካሄድ ለመመለስ ወሰንኩ ። ያ ዕለት እግዚአብሔር በትክክል ለአገልግሎት እንደሚፈልገኝ የመረዳት እና የመመለስ ቀን ሆነልኝ ። ለእኔ ጌታን ያወቅሁበት እና የተጠራሁበት ቀን ነበር ። ከዛ የንስሃ ቀን ጀምሮ በውስጤ ለሰዎች ስለጌታ መናገርና የመመስከር ፍላጎት በሃይል መጣ ። እኔም በሄድኩበት ሁሉ ስለጌታ መናገር ጀመርኩ ። በመቀጠልም በኮንፍረንስ ላይ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቼ ወደ ሌላ ከፍታ ውስጥ ገባሁ ። ለንግድ ሩጫዬ እየቀነሰ ወደ ጸሎት እና ወደ አገልግሎት ማተኮር ጀመርኩ ።
አስራ ሁለተኛ ክፍልን ስጨርስ ለብሄራዊ ዘመቻ ስፈለግ ጠፍቼ ከያቤሎ ወደ ሞያሌ ኬንያ ገብቼ ንግድና አገልግሎት በኬንያ ጠረፍ ከተሞች ጀመርሁ ። እግዚአብሔርም ከዓመታት በፊት በወንጌላዊ አበራ እ . ኤ . አ . በ1990 ወደ ተናገረኝ ከተማ ሳልወድ አመጣኝ ። ክርስትያን ወጣቶችን ማሰባሰብ ጀመርኩ ። ከተማው ክርስትያኖች ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ በማድረግ ወደ እስልምና በማስቀየር የታወቀ ነው ። አብዛኛዎቹ እዛ ከተማ የመጡ ክርስትያኖች ሰልመዋል ። በከተማዋ ወንጌል እንዲነሳ ይጸልይ የነበረ አንድ ኤልያስ የሚባል
ወንድም ሲያገኘኝ በጣም ደስ ብሎት ከቃለ ህይወት አባቶች ጋር አገናኝቶኝ ጸለዩልኝ ፣ በመቀጠልም የወጣቶች መሪ ፣ ከዚያም ቤተክርስትያን ተክለን የቤተክርስትያን ሽማግሌ ሆንኩኝ ።
መነቃቃት በከተማዋ ተጀመረ ፣ ሰዎች ይፈወሱና ከቀንበራቸው ይፈቱ ጀመር ። እግዚአብሔርም እንደማገለግለው በተደጋጋሚ በራዕይ ይናገረኝ ጀመር ። እኔም በተለያየ ጸጋ ስጦታዎች ማደግ ጀመርኩ ። ሆኖም ነጋዴ ሆኜ ብዙ ገንዘብ ስለማገኝ በ160 ብር ተቀጥሮ ወንጌላዊ ሆኖ ለማገልገል ከበደኝ ። በንግድ እና በአገልግሎት ውስጥ እያለሁ ቤተክርስትያኑ በ1992 ከ13 ሰው ተነስቶ በ1996 ወደ 180 ሰው አደገ ። ቤተክርስትያንም በመጋቢነት እንዳገለግል በ1996 ጠየቀችኝ ። እኔ ለእለት ኑሮዬ እየሰራሁ አገለግላለሁ እንጂ ወንጌላዊ ሆኜ በ160 ብር ሙሉጊዜ አልሰራም ብዬ እንቢ አልኩ ።
ቤርያ : - በኢትዮጵያ እና በኬንያ ጠረፍ ከተሞች የነበረህ አገልግሎት ምን ይመስል ነበር ?
ፓ / ር አህመድ : - አንድ
15