Christian Books & Magazines - Free Berea Magazine 5 | Page 14

“ ክርስትያን ለመሆን ትፈልጋለህ ወይ ?” ስትለኝ አዎንታዬን ገለጽኩላትና ወደ ሰባኪው ወሰደችኝ ። ሰባኪውም ክርስትያን ለመሆን እፈልጋለሁ ስለው ጸጉሬን ደባበሰና “ በቃ ከዛሬ ጀምሮ ክርስትያን ሆነሃል ” ብሎ አሰናበተኝ ። እንደ እስልምናው ብዙ የሚደረግ ነገር ያለ መስሎኝ ምንድነው የማደርገው ብዬ ጠየቅሁት ፣ “ በየሳምንቱ ቅዳሜ እየመጣህ የእምነት ማጽኛ ተማር ። እሁድ እሁድ ደግሞ ቤተክርስትያን ተካፈል ” ሲለኝ ስላላመንኩት ይሄ ብቻ ነው ብዬ በመደነቅ ጠየኩት ። እሱም ይኽው ነው ብሎ አሰናበተኝ ። መስኪድ መሄድ እችላለሁ ወይ ስለው “ አሁን ክርስትያን ስለሆንክ መስጊድ መሄድ የለብህም ” ብሎ መከረኝ ። ጊዜ ጀምሮ መስኪድ መሄድ አቆምኩ ።
የእምነት ማጽኛ ትምህርቴን በፍቅር ተከታትዬ ስጨርስ ተጠመቅሁኝ ። በዚህ ዓይነት መንገድ ጌታዬ ተቀበለኝ እኔም በተለያየ አገልግሎት ማገልገል ጀመርኩ ። በተለይም መስበክና የብሉይ ኪዳን አባቶችን ታሪክ በክፍል ውስጥ ለሌሎች በትረካ መልክ ማካፈል በጣም እወድ ነበር ።
ሆኖም ሃይማኖቱን ልቀበል እንጂ ጌታን አላውቅም ። ጫት እቅማለሁ ፣ ዘፈንና መዝሙርም አዳምጣለሁ ። ቤተክርስትያን ግን አልቀርም ፣ ቃሉን በጥናት ስለማውቀው እስብክም ነበር ። በዚህ አይነት የተደበላለቀ ሃይማኖተኝነት የሚቀጥሉትን ሶስትና አራት አመታት አሳለፍኩኝ ። ጌታ ተቀብሎኛል ፣ እኔ ግን ጌታን ተቀበልኩ አወቅሁት ወይም ተረዳሁ የምለው ዘጠነኛ ክፍል ስደርስ ቦሌ በሚባል መንደር የተካሄደ ኮንፍራንስ ላይ መንፈስ ቅዱስ ከተሞላሁ በሁዋላ ነው ። ወድያውም የክርስቶስን ፊልም ሙሉውን በተመስጦና በእንባ ሆኜ ከተመለከትሁ በኋላ የክርስቶስ ሞቱና
14
ትንሳኤው በክርስቶስ ማመንም ምን ማለት እንደሆነ በደንብ ተገለጠልኝ ። የአባቴ መንፈስ ነው እንጂ ስጋ እና ደም አልገለጠላችሁም የሚለውን ቃል ሙሉ በሙሉ በመረዳት የክርስቶስ ፍቅሩ ጠልቆ ገባኝ ። ወንጌል የሚለውን ሃሳብም ከዛን ጊዜ ጀምሮ ተረድቼ በዚህ ዓይነት ነው ወደጌታ የመጣሁት ።
ቤርያ ፡ - ቤተሰቦችህ ወደ ክርስትና መምጣትህን እንዴት ተቀበሉት ? የደረሰብህ ስደት ነበር ወይ ?
ፓ / ር አህመድ : ለጥቂት ጊዜ ለቤተሰቦቼ ክርስትያን መሆኔን አልተናገርኩም ። መስኪድ ሄድክ ስባል አዎን ሄጃለሁ እያልኩ እኔ ግን አልሄድም ። ከሶስት ወር በሁዋላ “ በሰው ፊት የሚክደኝን በአባቴና በመላዕክት ፊት እክደዋለሁ “ የሚለውን ቃል ስብከት ውስጥ ስሰማ ፈራሁና በድፍረት ክርስትያን መሆኔን ለቤተሰቤ ለመናገር ወሰንኩ ። በማግስቱ በጠዋት አባቴ ቡና ለመጠጣት እየተዘጋጀ እያለ “ አባባ “ ብዬ ቀረብሁት ። እሱም ምነው ብሎ ሊሰማኝ ተዘጋጀ ። እኔም “ ከዛሬ ጀምሮ አልሰግድም አልኩት ” እሱም ለምንድነው የማትሰግደው ? አለ ። እኔ ክርስትያን ሆኛለሁ አልኩት ። ይህን ስል አባቴ መሳርያውን ለማምጣት ወደ ጓዳ ሲገባ ፣ ሮጬ አመለጥኩ ። ከቤት ከወጣሁ በሁዋላ ብዙ መከራና ከባድ ተጽዕኖ አደረጉብኝ ። ወላጅ አባቴም በጭራሽ ላየው አልፈልግም አለ ። የእስልምናው ማህበረስብ ከእነሱ ለይተው ገለልተኛ አደረጉኝ ። ከዚህም የተነሳ ኑሮዬን ለማሸነፍ ጋሪ መግፋት ፣ ሰው ቤት መቀጠር ፣ መሸከምና በየስፍራው ማደር ነበረብኝ ። እንደዚህም ሆኖ ከቤተክርስትያን አልቀርም ነበር ።
አንድ ቀን የቀበሌ ጥበቃዎች ትፈለጋለህ በማለት የፍርድ ሸንጎ
ላይ አቀረቡኝ ። የፍርድ ሸንጎውም ከቤተሰቦችህ በቀረበብህ ክስ መሰረት “ ከዛሬ ጀምሮ በወላጅ አባትህ በአደን ስም መጠራት አትችልም ፣ ምንም ዓይነት ውርስም አታገኝም ” ብለው አስፈረሙኝ ። በልጅነት ዕድሜዬ ብዙ ተጽዕኖና መገለል እየደረሰብኝና እየተንገላታሁ ነበር ለብዙ ጊዜ የኖርኩት ።
ቤርያ ፡ - አሁን ላለህበት አገልግሎትስ የአለፍክባቸው መንገዶችና የአገልግሎትህ ጅማሬዎች የትና እንዴት ነበሩ ?
ፓ / ር አህመድ : ሁኔታው ራስን ችሎ ኑሮን ማሸነፍን በልጅነት እድሜ ስለአስተማረኝ ወደ ንግድ ውስጥ ገባሁ ። ስምንተኛ ክፍል ስደርስ በአስራ ዘጠኝ ዓመቴ ታዋቂ ከሆኑት ባለብዙ ገንዘብ ወጣት ነጋዴዎች አንዱ ለመሆን በቃሁ ። በኢትዮጵያና በኬንያ ድንበር ላይ በግመል እንደ ወርቅ ፕላስቲክ እና የተለያዩ እቃዎች በመነገድ የተሳካለት ነጋዴ ሆንኩ ። ሆኖም ብሩና የንግዱ ጥቅም ደግሞ ወደ አገልግሎት እንዳልመጣና መንፈሳዊ ነገር ላይ እንዳላተኩር በማድረግ ይዞኝ ጠፋ ። ትኩረቴ ያገለሉኝ ቤተሰቦቼን ምን እንዳለኝ ማሳየት ስለነበረ በንግዱ ጥቅም ተወስጄ ሳላውቀው ዓለማዊያን የሚያደርጉትን ሁሉ ማድረግ ጀመርኩ ። በዚህ ሁኔታ እያለሁ ግን ከቸርች አልቀርም በተለያዩ ስፍራዎችም አገለግላለሁ ።
ለመጀመርያ ጊዜ በሞያሌ ኬንያ የሚኖሩ ጥቂት ኢትዮጵያውያንን በቤት ውስጥ ሕብረት ላይ አገልግዬ ስመለስ አበራ የተባለ ወንጌላዊ በሰንሰለት እንደተያዝኩ እና እግዚአብሔር ግን ሞያሌ ኬንያ ላይ እንደሚፈልገኝ ጌታ ያሳየውን ነገረኝ ። እኔ ግን በአለሁበት