Christian Books & Magazines - Free Berea Magazine 5 | Page 13

ፓስተር አህመድ አላ

የእግዚአብሔር እሳት በጠረፍ ከተሞች

ፓስተር አህመድ አላ
ከቤርያ የመጽሔት ዝግጅት ክፍል ወንድም ኮነ ፍስሐ ከፓስተር አህመድ አላ ጋር ያደረገውን ልዩ ቃለ መጠይቅ ይዘንላችሁ ቀርበናል ። ቃለመጠይቁ ወደ አገልግሎት ለመግባት ለሚያስቡ እና እያገለገሉ ላሉ ሁሉ እጅግ ጠቃሚ ምሳሌነት ያለው ነው ።
ቤርያ ፡ - የቤርያ መጽሔት እንግዳ በመሆንህ አመሰግናለሁ ። ከግል ሕይወትህ እንጀምርና ፣ ስለትውልድህ ፣ የልጅነት ጊዜህና እንዴት ወደ ጌታ እንደመጣህ ብታጫውተን ።
ፓስተር አህመድ : ስሜ አህመድ አላ ይባላል ። ያደኩትና የተወለድኩት በደቡብ ኢትዮጵያ ጠረፍ አካባቢ ነው ። ትውልዴ ከእስላም ቤተሰብ ሲሆን ለቤተሰቤ የመጀመርያ ልጅ ነኝ ። እናቴን የመጀመርያ ባልዋ ከሁለት ወይም ከሶስት ዓመት ጋብቻ በሁዋላ አትወልድም ብሎ ስለተዋት እኔ የተወለድኩት ከብዙ ተደጋጋሚ ጋብቻ በሁዋላ ነው ። በመጨረሻው ጋብቻዋ ፥ እናቴና አባቴ የእስላም ቃልቻዎችን ሰብስበው ብዙ ልመና መጅሊስና ዱኣ አስደረጉ ። በዚህ ዱኣ ላይ የቃልቻዎቹ መሪ “ የዛሬ ዓመት ዓርብ ቀን አህመድ የሚባል ወንድ ልጅ ትወልዳላችሁ ። እርሱም በዘመኑ ሁሉ የአላህ አገልጋይና ባርያ ይሆናል ” የሚል ትንቢት ተናገራቸው ። በዓመቱም ቃልቻው እንደተነበየው ዓርብ ቀን ተወለድሁ ። ቤተሰቦቼም አህመድ ብለው ሰይመውኝ ከአራት ዓመቴ ጀምሮ እስልምናን በቁራን ትምህርት ቤት አጥብቀው እያስተማሩ አሳደጉኝ ። የቤተሰቦቼ ዓላማ ወደፊት ኢማም ሆኜ መንፈሱ አስቀድሞ እንደተናገራቸው እስልምናን
እንዳስፋፋ ነበር ። በዚህ ሁኔታ ውስጥ የማድግ ሰው ስለነበርኩ እውነተኛውን የወንጌል ብርሃን አይቼ እድናለሁ የሚል ተስፋ ጭራሽ ባልነበረበት ሁኔታ ውስጥ ነበርኩኝ ።
እኔ የማምነው ጌታ ወደ እኔ መጣ ነው የምለው ምክንያቱም ባለሁበት ሁኔታ እኔ ጌታን ፈልጌ የማገኝ አልነበርኩም ። ገጠር አያቴ ቤት ሆኜ ቁራን ስማር ዓይኔን በጣም ታመምኩና እናቴ አሳክሜ እመልሰዋለሁ ብላ ይዛኝ ወደ ከተማ መጣች ። እድሜዬ በዛን ጊዜ ዘጠኝ ዓመት ይሆነኛል ። ዓይኔን በህክምና ታክሜ ሲሻለኝ ከተማ ውስጥ ሌላ የቁራን ትምህርት ቤት አስገብተውኝ እስከ 11 ዓመቴ ድረስ ቁራን ብቻ ተማርኩ ። በአጋጣሚ ሊጠይቀን የመጣ አጎቴ ይህ ልጅ ትምህርት ቤት ገብቶ መማር አለበት በማለት በአካባቢው ወደሚገኘው የመካነ ኢየሱስ ሚሽን ትምህርት ቤት አስገባኝ ። ቤተሰቦቼ ግን እሱ ለአላህ የተለየ ነውና ትምህርት ቤት ቢገባ ይሞታል በማለት በጣም ተጨነቁ ። ትምህርት ቤት እንደገባሁ የአንደኛ ክፍል የመጽሐፍ ቅዱስ መማርያ መጽሐፍ በመጀመርያው ቀን ተሰጠኝ ። በዓመቱ መጨረሻም ጥሩ ውጤት በማምጣት የሁለተኛ ክፍል የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ማጥኛ እና ሙሉ መጽሐፍ ቅዱስ ተሸለምኩ ።
መጽሐፎቹን ቤት ይዤ መምጣት ስለማይፈቀድልኝ እርሻ ውስጥ ደብቄ አስቀምጣቸው ነበር ። ይህ ሁሉ ሲሆን በየቀኑ ጠዋት አምስት ሰዓት ላይ እሰግድ እና ቁራን ትምህርት ቤት ደግሞ ሄጄ እስከ ጠዋቱ ሰባት ሰዓት ተኩል ቁራን እማራለሁ ። ከዛ በሁዋላ በስምንት ሰዓት ላይ ወደ ሚሽን ትምህርት ቤት እሄዳለሁ ። መጽሐፍ ቅዱስ እያነበብኩ ስመጣ ብዙ ጥያቄዎችን በምሄድበት መስኪድ ውስጥ ማንሳት ጀመርኩ ። ለምሳሌ ለምንድነው ወደ አንድ አቅጣጫ የምንሰግደው ? ጥሩ እስላም ወንድ በሰማይ ሰባ ደናግልት ለሚስትነት ይሸለማል ። ጥሩ እስላም ሴትስ የምትሸለመው ምንድነው ? ለመዳኔ እርግጠኛ የምሆነው እንዴት ነው ? በማለት ብዙ ጥያቄዎችን በመስኪድ ውስጥ አነሳ ነበር ። በዚህ ሁኔታ ሁለቱንም ሃይማኖቶች እያጠናሁ እስከ ስድስተኛ ክፍል ተማርኩ ። ውስጤ የመዳንን እውነተኛ መንገድ ለማወቅ በጣም ይፈልግ ነበር ። አንድ ቀን ትምህርት ቤታችን ያለው ቤተክርስትያን ውስጥ ሰባኪው እያለቀሰ ስለ መስቀሉ ፍቅር ሲሰብክ ሰምቼ እኔም ማልቀስ ጀመርኩ ። አጠገቤ ገነት የምትባል እህት መጨረሻ ላይ “ ለምንድነው የምታለቅሰው ? ክርስትያን ነህ ወይ ?” ብላ ጠየቀችኝ ፣ እኔም አለመሆኔን ነገርኳት :። እሷም
13