Christian Books & Magazines - Free Berea Magazine 5 | Page 12

የእምነት እንቅስቃሴ ስለእምነት ፣ ያለው አስተምህሮ
እንቅስቃሴው ስለ “ እምነት ” ያለውን አግድም ዐደግ ትምህርት በውል በመረዳት ስሕተቱን በትክክል ማከም የሚቻለው ፣ ከርእሰ ጒዳዩ ጋር ኩታ ገጠም የሆኑትን ነጥቦች ማለትም “ በአዎንታዊ ዐዋጅ ” እንዲሁም “ በጸሎት ” ላይ የሚሰጡትን ትምህርቶች በትክክል መገንዘብ ሲቻል ነው ። ስለዚህ በቅድሚያ ፣ የእንቅስቃሴው አንጋፋ መምህራን በእነዚህ ነጥቦች ላይ የሚሰጡትን ትንታኔ ፣ ከራሳቸው ጽሑፎች በቀጥታ በመጥቀስ ከተመለከትን በኋላ ፣ ወደ ሒሱ እንዘልቃለን ።
እምነት
እንቅስቃሴው ፣ “ በእምነትህ ላይ እምነት ይኑርህ ” ይለናል ። እንደ መምህራኑ ትንታኔ ፣ አምላክ ራሱ እምነት አለው ( ማር 11 ÷ 22 )። ይህ አምላክ ገንዘቡ አድርጎታል የሚባለው ዐይነት እምነት ክርስቲያኖችም ይኖራቸው ዘንድ ፣ አምላክ ራሱ በስጦታ መልክ ለአማንያኑ ማኅበረሰብ አከፋፍሏል ( ሮሜ 12 ÷ 3 ፤ ኤፌ 2 ÷ 8 )። ይህ እምነት ደግሞ ፣ ተራራን የማናወጥ ኀይል አለው ። አምላክ ራሱ ዓለማትን የፈጠረው ፣ ይህን ዐይነቱን እምነት እንደ ግብዐት በመጠቀም ነው ( ዕብ 11 ÷ 3 ፤ እንዲሁም ሮሜ 4 ÷ 17 ) 6 ።
እንዲያውም የእንቅስቃሴው መምህራን ፣ እምነት ብቻ ሳይሆን ፣ ከአንደበታችን የሚወጡ ንግግሮች አዎንታዊም ሆነ አሉታዊ ኀይል ስላላቸው ፣ ክርስቲያን የሆነም ሆነ ክርስቲያን ያልሆነ ሰው ፣ የሚናገረው ንግግር እውን እንደሚሆን አምኖ ( እርግጠኛ ሆኖ ) ከተናገረ ፣ ንግግሩ ግዝፍ ( ሥጋ ) በመንሣት ወደ እውነታነት ( ገሓድነት ) ይቀየራል ። ምክንያቱም ይህ ( ማመን እንዲሁም ያመኑትን ነገር መናገር ) በአማኒውም ሆነ
አማኒ ባልሆነው ሰው ውስጥ በጒልሕ የሚሠራ ፣ የማይነቀስ የማይገሠሥ ቀመር ነው 7 ። ለዚህ የሚጠቀሰው ጥቅስ ኢየሱስ ፣ “ ማንም ያለው ነገር እንዲደረግለት ቢያምን ” ( ማቴ 11 ÷ 23 ) ይሆንለታል ብሏል የሚለው ነው 8 ።
የእንቅስቃሴው ዕውቅ መምህር የሆኑት ኬኔት ሐጌን ይህን ጒዳይ በተመለከተ እንዲህ ይላሉ :— “ ያልዳኑ ሰዎች ሲሳካላቸው የማየቴ ጒዳይ ግራ ይገባኛል ። ነገር ግን የቤተ ክርስቲያኔ ሰዎች [ ይህ ዐይነቱን ] ውጤት አያዩም ። ኀጥኣን ምን እያደረጉ ነው ለሚለው ያገኘሁት መልስ ፣ ከዚህ ዐይነቱ የእግዚአብሔር ሕግ ጋር መተባበራቸው ነው ፤ ይኸውም የእምነት ሕግ ነው ።” 9
በአጠቃላይ ፣“ ማናቸውንም ነገር ከእግዚአብሔር ማግኘት የሚፈልግ ሰው ፣ በእምነቱ ላይ እምነት ሊኖረው ይገባል ” 10 ። እንግዲያው እምነት ማለት ምን ማለት ነው የሚለውን ጥያቄ የእንቅስቃሴው መሪዎች ፣ “ ኀይል ነው ” 11 የሚል ትርጒም ይሰጡታል ። ይህ ደግሞ እምነት ያልሆነውን ነገር እውን እንዲሆን ፣ ያልተፈጠረውን ነገር መፍጠር እንዲችል አድርጎታል ( ሮሜ 4 ÷ 17 ) 12 ። እምነት ረቂቅ ነገር ቢሆንም ፣ የማይታየውን ነገር እንዲታይ የማድረግ ከፍተኛ ኀይል አለው 13 ። የእንቅስቃሴው መምህራን ፣ “ እውነተኛ እምነት ቁሳዊ የሆነውን እውነታ አንቀበልም ” ባዮች ናቸው ( ሮሜ 4 ÷ 19 ፣ 2ቆሮ 4 ÷ 18 ፣ 5 ÷ 17 ) 14 ። ስለዚህም እምነት ምክንዮአዊና ምክንያታዊ ሳይሆን ፣ ከአምክንዮ ሕግጋት ጋር የሚጻረር ነገር ግን እንዲያው በጭፍን የሚታመን ነገር ነው 15 ።
የእንቅስቃሴው መምህራን እስካሁን ከተመለከትነውም በተጨማሪ ስለ እምነት ሌላም ገለጻ አላቸው ። ይኸውም መጽሐፍ ቅዱስ እምነት ...........
በገፅ 43 ይቀጥላል
በወንድም ዶ / ር ተስፋዬ ሮበሌ በአቅበተ እምነት ላይ የተዘጋጁ መጽሐፍትና አገልግሎቱን በድረገጹ ይመልከቱ
www . TesfayeRobele . com www . TesfaApologetics . com
መጽሐፎቹን www . tsega . com ያገኛሉ ።
12