Christian Books & Magazines - Free Berea Magazine 5 | Page 10

ነው ። ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስ ልሳን እንጂ የዓለም ልሳን አይደለችም ። ቤተ ክርስቲያን ክርስቶስ ራሱን ለሠዋለት ዓላማ ልትሠዋ ተጠርታለች ። ክርስቶስ ራሱን ለሰዎች መዳን አሳልፎ ሰጠ ፤ ለፍትሕና ለድሆች ተከራከረ ፤ የዓለምን ስምና ዝና ናቀ ፤ የተላከበትን ውጥን ፈጸመ ። አሁን በዚህ ዘመን የእግዚአብሔር ሐሳብ የሚፈጸመው በቤተ ክርስቲያን በኩል ነው ። ይህች ቤተ ክርስቲያን ግን

“ አሁን

በዚህ
ዘመን
የእግዚአብሔር
ሐሳብ
የሚፈጸመው
በቤተ
ክርስቲያን
በኩል
ነው ።
ይህች
ቤተ
ክርስቲያን
ግን
የብልጽግናን
ወንጌል
የምትሰብከው
ቤተ
ክርስቲያን እንዳልሆነች
በእርግጠኛነት
መናገር

ይቻላል ።” ምኒልክ አስፋው

የብልጽግናን ወንጌል የምትሰብከው ቤተ ክርስቲያን እንዳልሆነች በእርግጠኛነት መናገር ይቻላል ። ሐዋርያው ጳውሎስ እንዲህ ዐይነቱን ወንጌል “ ልዩ ወንጌል ” ( ἕτερον εὐαγγέλιον / ሄቴሮን ኢዋንጌሊዮን ) ይለዋል ( ገላ
10
1 ፥ 6 )። የብልጽግና ወንጌል በኢየሱስም ሆነ በሐዋርያቱና በመላእክቱ አልተሰበከም ። ለሰዎች የሚመቸውን ፣ የሚጥመውንና የሚያጓጓውን ምድራዊ ፍልስፍና የሚሰብኩ በእውነተኛው “ የክርስቶስ አገልጋዮች ” አይደሉም ( ገላ 1 ፥ 10 )። ጳውሎስ የክርስቶስን ወንጌል ሊያጣምሙ የሚወዱ ሰዎች እንዳሉ ከገለጸ በኋላ “ ማንም ከተቀበላችሁት ሌላ የተለየ ወንጌል ቢሰብክላችሁ እርሱ ለዘላለም የተረገመ ይሁን [ ἀνάθεμα ἔστω / አናቴማ ኤስቶ ]” ይላል ( ገላ 1 ፥ 9 ፤ አመት )። ቤተ ክርስቲያን አዚም ካልተደረገባት በስተቀር ኢመጽሐፍ ቅዱሳዊ የሆነውን የብልጽግናን ትምህርት ተቀብላ ልትሰብክ አትችልም ። “ ለእውነት እንዳትታዘዙ አዚም ያደረገባችሁ ማን ነው ? [“ ለመሆኑ ማን መተት አደረገባችሁ ?]” ( ገላ 3 ፥ 1 ) የሚለው ጥያቄ የዛሬይቱንም ቤተ ክርስቲያን ይመለከታል ። እዚህ ላይ ጳውሎስ ብርቱ አገላለጽ እንደተጠቀመ ግልጽ ነው ። ሐሳቡ የአጋንንትን ትምህርት እንድትከተሉ ያደረጋችሁ ወይም ጤነኛውን አእምሮ አቃውሶ ያሳበዳችሁ ማን ነው ተብሎ ሊወሰድ ይችላል ። 8 እንግዲህ ሰዎችን የሚያድነውን ወንጌል በመስበክ እንትጋ ። “ የብልጽግና ወንጌል ” ሰው ሠራሽ ትምህርት ነው ።

“ ማንም ከተቀበላችሁት ሌላ የተለየ ወንጌል ቢሰብክላችሁ እርሱ ለዘላለም የተረገመ ይሁን [ ἀνάθεμα ἔστω / አናቴማ ኤስቶ ]” ይላል ( ገላ 1 ፥ 9 )

እንዲህ ዐይነቱ ትምህርት ሲጠቅም ያየነው የትምህርቱን ፈጣሪዎች ብቻ ነው ። ይህን ትምህርት የሚሰብኩ ሰዎች በእርግጥም ተጠቅመዋል ። ሰሚዎቹ ግን “ ትባረካለህ ” ( 100 ብር ከሰጠህ 1,000 ብር ታገኛለህ ) በሚል ከንቱ ማባበያ ያለ የሌላቸውን ተበድረውም ሆነ ተለክተው እንዲሰጡ ከመነዝነዝ በስተቀር ምንም ያተረፉት ነገር የለም ። ምስኪኑ ሕዝብ በብልጣብልጥ ሰባኪዎች እንዳይዘረፍ አንድዬ ለሕዝቡ መሪዎች ልቡና ይስጥ ! ምድራዊውንና አጋንንታዊውን ትምህርት የሚለዩበትን ሰማያዊ ልብ ይስጥ !
የግርጌ ማስታወሻ
7 Mark D . Mathews , “ Riches , Poverty , and the Faithful : Perspectives on Wealth in the Second Temple Period and the Apocalypse of John ,” ( PHD Diss ., Durham University , 2010 ) 186-193 . 8 Richard N Longenecker , Galatians , WBC ( Dallas : Word Bokks ) 133-134 . እንዲሁም F . F . Bruce , The Epistle to the Galatians , NIGTC ( Grand Rapids : Eerdmans , 1990 ) “ who has hypnotized you ?” 148 . Marion L . Soards and Darrell J . Pursiful , Galatians , SHBC ( Georgia : Smyth & Helwys Publishing , 2015 ) 120-121 .
የትምህርቱ ፈጣሪዎችና ሰባኪዎች እንደሚሉት በሰጠን ቁጥር ተባርከን ቢሆን ኖሮ ዛሬ ሁላችንም ባለጠጎች በሆንን ነበር ። “ ያልተባረካችሁት ‘ እምነት ’ ስላጣችሁ እንጂ ‘ ትምህርቱ ’ ልክ ስላልሆነ አይደለም ” የሚለው ማስተባበያቸው ግን እንደ ስላቅ ይቆጠራል ።