Christian Books & Magazines - Free Berea Magazine 5 - Page 47

የእምነት እንቅስቃሴ መምህራን አሉታዊ ዐዋጅ የሚሉትን አስተምህሮ በቃለ እግዚአብሔር ላይ ለማስደገፍ የሚጠቀሙባቸው ጥቅሶች፣መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል ያለውን ኀይል ለመግለጽ፣ የሚጠቀምባቸውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ነው። ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል ኀይለኛ የሆነበት ምክንያት የእግዚአብሔር ስለሆነ (እግዚአብሔር ስለተናገረው) እንዲሁም እውነት ስለሆነ እንጂ (ሮሜ 4÷1621)፣ ቃላት በራሳቸው ኀይል ስላላቸው አይደለም። ዘማሪው፣ “እርሱ ተናግሮአልና ሆኑም፤ እርሱ አዘዘ፤ ጸኑም” (መዝ 33÷9) ያለበት ምክንያት፣ “ምድር ሁሉ እግዚአብሔርን እንዲፈራው፤ በዓለም የሚኖሩም ሁሉ ከእርሱ የተነሣ እንዲደነግጡ” (ቊ10-11) ነው። እንግዲህ ፍሬ ነገሩ እዚህ ላይ ነው:— እግዚአብሔር ያለው ወይም የተናገረው ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል፤ሰዎች ያሉት ግን (በነሲብና በግምት) ሊፈጸምም ላይፈጸምም ይችላል። ዘማሪው፣ “ሰብአውያን የሚናገሩት ቃል እውን እንዲሆን፣ በእምነት ተሞልተው ይናገሩ” የሚል ምክር አይመክርም። ይልቁንም ዘማሪው እስራኤል አምላኳ የሆነውን እግዚአብሔርን እንድትፈራ፣ ምሕረቱንም ተስፋ እንድታደርግና ርዳታውንም እንድትሻ ይመክራል (ቊ16-22)። “በአፍህ ቃል ተጠመድህ፤ በአፍህ ቃል ተያዝህ” (ምሳ 6÷2) የሚለውን ነው። ነገር ግን ክፍሉ የሚያወራው፣ ለጐረቤቶቹ ዋስ ሆኖ፣ በዋሱ መሠረት ስለተያዘ ሰው ነው፣ “ልጄ ሆይ ለጐረቤትህ ዋስ ብትሆን፣ ስለሌላ ሰው እጅህን አጋና ብትመታ፣ በአፍህ ቃል ተጠመድህ፤ በአፍህ ቃል ተያዝህ” (ምሳ 6÷1-2)። ቃላት የሕይወትና የሞት ኀይል አላቸው ለሚለው ትምህርት የሚጠቀስ ሌላው ጥቅስ፣ “ሞትና ሕይወት በምላስ እጅ ናቸው፤ የሚወድዱአትም ፍሬዋን ይበላሉ” (ምሳሌ 18÷21) የሚለው ክፍል ነው። ቃላት የሕይወትና የሞት ኀይል አላቸው የተባለው፣ ቃላት የእምነትን ኀይል ስለሚያስተላልፉ ሳይሆን፣ የምንናገራቸው ንግግሮች ጥሩም ሆነ መጥፎ ውጤት ሊያስከትሉ ስለሚችሉ ነው። በዚህ ዐውድ የሰነፍ ንግግር ጠብን ስለሚጭር በዚህም የሰዎችን ሕይወት ስለሚቀጥፍ ነው (ቊ 6(7)። ዘመዶቻችን፣ “በለፈለፉ በአፍ ይጠፉ” እንደሚሉት መሆኑ ነው። ለአዎንታዊ ዐዋጅ የሚጠቀሰው ሌ ላ ው ጥቅስ ማቴዎስ 12÷36-37 ነው። በክፍሉ ኢየሱስ ፈሪሳውያን በንዝላልነት የሚናገሩትን ከንቱ ንግግር ሲነቅፍ ይታያል። የእንቅስቃሴው መሪዎች ከዚህ ጥቅስ በመነሣት አሉታዊ ዐዋጅ የሚያስከትለውን ጥፋት የሚገልጽ ቀመር የቃለ እግዚአብሔርን ሥልጣን ኀይል በማተም ቀምረዋል፣ ይኸውም፣ “ለምትመኘው ነገር ጠንቃቃ ሁን፤ ከሚታወቁ ክፍሎች መኻል ኢሳይያስ 55÷11 አንዱ ምክንያቱም የተመኘኸውን ነገር ድንገት ከተናገርኸው ነው፣ “ከአፌ የሚወጣ ቃል እንዲሁ ይሆናል፤ የምሻውን ታገኘዋለህና”። ነገር ግን በዚህ ክፍል ኢየሱስ ለማስተማር ያደርጋል፤ የላክሁትንም ይፈጽማል እንጂ ወደ እኔ በከንቱ የፈለገው ነገር ፍጹም ከዚህ የተለየ ነው። ይኸውም ኢየሱስ አይመለስም”። እግዚአብሔር እንዲህ ያለበት ምክንያት ሲያወግዘው የነበረው ንግግር ፈሪሳውያን መንፈስ ቅዱስን እስራኤል የተሐድሶ ዘመኗ የእግዚአብሔርን ምሕረት (እግዚአብሔርን) የመሳደባቸውን ጒዳይ ነው (ቊ 31-32)። ለማግኘት ፊቷን ወደ አምላኳ እንድትመልስ ለመግለጽ ነው መንፈስ ቅዱሰንም የመሳደባቸው ውጤት፣ (ቊ 6- 13)። ይህ የሚሆንበት ምክንያት፣ እግዚአብሔር ፍጹም ስለሆነ፣ መንገዱ ከሰብአውያን መንገድ ሰማይ ከምድር በራሱ በእግዚአብሔር እንደሚፈረድባቸው ወይም እንደሚቀጡ እንደሚርቅ የራቀ ስለሆነ፣ እርሱ የሚለው ሁሉ እውነት እንደ እንጂ፣ አሉታዊ ነገር በመናገራቸው ምክንያት ብቻ፣ የተናገሩት ንግግር በራሱ አሉታዊ ውጤት ያመጣባቸዋል ሆነ እርግጠኞች ነን (ቊ. 8-9)። ማለት አይደለም። ለምንናገራቸው አዎንታዊም ሆኑ መጽሐፈ ምሳሌ ቃላት መንፈሳዊ ኀይል አላቸው አሉታዊ ንግግሮች ተጠያቂዎች መሆናችን እሙን ነው፤ የሚል ትምህርት አያስተምርም።