AddisLidet 2017 | Page 9

ለመሆኑ ክርስቲያኑን ሁሉ ምንድነው እንደዚህ ያስጎበጠው ? ጌታን ስንቀበል በውስጣችን መልካም ዘር ገብቶ ደህንነት ስንማርና ክርስትናን ስንጀምር ይህ ዘር እያደገ በእምነታችን ጠንክረን ነበር :: ዛሬ ግን አድገንና ይሔ ያልዘሩትን የማጨድ ወረርሽኝ የጠነከረውን ዘር ከውስጣችን አጥፍቶ እንደ “‘ ቁራሌው ” በድምጽ ብቻ የምንቀሳቅስ ኦሪጂናሌውን ወንጌል ትተን ከየመንደሩ ውዳቂ እቃ የምንሰበስብ አድርጎናል :: ያልዘሩትን ለማጭድ የሚደረገው ሩጫና የምናጭደው ፍሬ ዱባና ቅል ሆኖብን ነፍሳችን በባህር መአበል ያለመሪ እንደምትዋዥቅ ተስፋ ያለቀባት ጀልባ መድረሻው ወደማይታወቅ ቦታ ደንገላሳ ትጋልባለች :: እኔ ስገምት ቀድሞ የገባው በመልካም ዘር ጠባቂ አጥቶ መሬቱን አረም ውጦት የአውሬ መጫወቻ የሆነ ይመስለኛል ፡፡ አንዳንዶቹ ዘሩን ቁርጥም አድርገው በልተው ለነገ የሚሆን እንጥፍጣፊ ጉልበት ሲያጡ ለሙ መሬት ላይ ጎሳቸውን ፣ ዝናቸውን ፣ ሐብታቸውን ፣ ክብራቸውን ፣ ውበታቸውን ወይም እውቀታቸውን ስለዘሩበት ኩዋሻንኮር እንዳሳበጠው ልጅ ከርቀት ተልቀው ውስጣቸው ግን ድግስ ባለበት ደጀ ሰላም የማይታጡ የቃሉ ረሐብተኛ ሆነዋል ፡፡ በኤፌሶን 4 ፣ 19 ላይ
“ ሕሊናቸው ስለደነዘዘ በማይረካ ምኞት በርኩሰት ሁሉ እንዳሻቸው ለመሮጥ ቅጥ ለሌለው ብልግና ራሳቸውን አሳልፈው ሰጥተዋል ” ይላል ፡፡ ይህ ቅጥ ያጣ ብልግና የተባለው አለመጠን የሆነውን የአለማዊነትና ያልተገራ ሕይወት እንጂ ወሲባዊውን ነውር ብቻ አይደለም ፡፡ ወዳጆቼ ፣ ይሄ የአዱኛ መሰብሰብ አባዜ ቅጥ ለሌለው ብልግና ድሮን ይሆን ? እምነት ማለት እኮ ባንዳንዶች ዘንድ እንደሚታየው ሒሳባዊ ስሌትና መላ ምት አይደለም ፡፡ እምነት ድግምት ወይም ምትሐትም አይደለም ፡፡ እምነት በጽድቅ ኑሮ በአምላክ ተወራርዶ ከበላተኛው ውስጥ የሚበላን ማስወጣት ነው ፡፡ እምነት እየተመኙ በጨለማ መዝለልም ሳይሆን የብርሐን ልጅ ሆኖ በተገለጠ ሕይወት እያመኑ በብርሐን መራመድም ነው ፡፡ በ2017 ዓ . ም እግዚአብሄር ለብዙዎቻችን የአዝመራ አመትን ከፊታችን የዘረጋ ይመስለኛል ፡፡ በዕብራውያን 12 ፣ 17-18
“ የእግዚአብሔር ጸጋ ለማንም እንዳይጎድለው ፥ ብዙዎቹም የሚረክሱበት አንድ መራራ ሥር ወደ ላይ በቅሎ እንዳያስጨንቅ ፥ ሴሰኛም የሚሆን እንዳይገኝ ፥ ወይም ስለ አንድ መብል በኵርነቱን እንደ ሸጠ እንደ ዔሳው ለዚህ ዓለም የሚመች ሰው እንዳይሆን ተጠንቀቁ ። ከዚያ በኋላ እንኳ በረከቱን ሊወርስ በወደደ ጊዜ እንደ ተጣለ ታውቃላችሁና ፤ በእንባ ተግቶ ምንም ቢፈልገው ለንስሐ ስፍራ አላገኘምና ።” እንደሚል ቀጣዩን 2017 አመት የአዝመራ አመት እንዲሆንለት የሚፈልግ ወገን በሕይወቱ የተተከለና መነቀል ያለበት መራራ ስር ካለ ራሱን መመርመር መጀመር አለበት ፡፡ እግዚአብሔር የአዝመራ አመት ሰጥቶናል ማለት አሜን ብለን የምንተኛበት ሳይሆን ሆ ! ብለን ለስራ የምንነሳበት አመት ነው ፡፡ ሕይወታችን ዘወትር በምርጫ የተሞላ ስለሆነ የምንዘራውንና የምናጭደውን ምርጫችን ይወስነዋል ፡፡ በምድራዊ በረከቶቸ መባርክ መልካም ቢሆንም ሕይወታችን በምድራዊ ነገሮች ከተባረከ እግዚአብሄር በረከቱን የሰጠን መልካሙን ስራ እንድንሰራበትና ለሌሎች እንድንተርፍበት ስለሆነ ማናኛውንም አይነት በረከቶች በአግባቡ መጠቀም የኛ ሐላፊነትም ግዴታም ነው ፡፡ እግዚአብሄር ክብርን ይሰጣል እንጂ ክብርህን አይጠብቅልህም ፤ እግዚአቤሔር ገንዘብ ይሰጥሐል እንጂ ገንዘብህን አይጠብቅልህም ፤ አግዚአብሔር አእምሮን ይሰጥሐል እንጂ አእምሮህን አይጠብቅልህም ፤ እግዚአብሄር ትዳርን ፣ ስራን ፣ ባላንጀራን ይሰጥሀል እንጂ የእነዚህ ሁሉ ጠባቂ አንተው ነሕ ፡፡ እግዚአብሄር በምድር የሚያስፈልገንን ነገሮች ሁሉ የሰጠን ለተፈጠርንበት አላማ እንድንኖርበት እንጂ እንድንኖርለት አይደለም ፡፡ ገንዘብ በራሱ መጥፎ ባይሆንም ሁል ጊዜ ከገንዘብና ከጌታ የቱ አንተን ያገለግልሀል ከሚለው ይልቅ ከገንዘብና ከጌታ አንተ የቱን ታገለግላለህ የሚለው በቅዱሳን ዘንድ ሁሉ ምላሽ ማግኘት አለበት ፡፡ ይቅጥላል ...
9