AddisLidet 2017 | Page 7

መልዕክተ መጋቢያን

መልዕክተ መጋቢያን

በአምላካችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጽድቅ ካገኘነው ጋር የተካከለ የክብር እምነትን ላገኛችሁ ፤ ቅዱሳንና የእግዚአብሔር ውድ ቤተሰቦች እንኳን ለ2017 ዓ . ም በሰላም አደረሳችሁ ። መጭው አዲስ ዓመት በሃገርም ሆነ በቤተክርስቲያን ከደረሰብን አሳዛኝ ከሆነ ፖለቲካዊ ፣ ኢኮኖማዊና መንፈሳዊ ውድቀትና ውድመት ተነስተን ፍርስራሾቻችን የሚታደሱበት ካለፈው ስህተታችን ተምረን ታሪካዊ ስህተት ላለመድገም ሁለንተናዊ ተሃድሶ የምንገነባበት ዓመት ነው ብዩ አምናለሁ ። “ የፊተኛውን ነገር አታስተውሉ ፥ የጥንቱንም ነገር አታስቡ ። እነሆ ፥ አዲስ ነገርን አደርጋለህ ፤ እርሱም አሁን ይበቅላል ፥ እናንተም አታውቁትምን ? በምድረ በዳም መንገድን በበረሀም ወንዞችን አደርጋለሁ ።” ኢሳ43:18-19
ዘመንና ዓመትን የጨመርልን እግዚአብሔር በሰጠን የምህረት ጊዚያቶች ተጠቅመን በክርስቶስ ዳግም የተፈጥርንበትን ዓላማ ጫፍ ለማድረስ ወገባችንን አደግድገን የኋላችንን እየረሳን ከተቸነክርንበት የአዙሪት ህይውት ውስጥ ወጥተን እጅ ለእጅ ተያይዘን ወደፊት መዘርጋት ትልቅ መንፍሳዊ ብስለት ነው ።
በምድር ላይ የማስታረቅ አገልግሎት የተሰጣት የክርስቶስ ቤተክርስቲያን በአግባቡ የቤት ሥራዋን ስላልተወጣች ቀውሶችና ነውጦች ከውስጥም ከውጭም በርክተዋል ፤ አሁን ግን በነፍስ ወከፍም ሆነ በጅማላ ሆ ! ብለን የምንነሳበት ስዓት ነው ። በእጃችን ያለው የስልጣን በትር ( ወንጌል ) እኛንም ሆነ ትውልዳችን ይዞ ለመሻገር በቂ ስለሆነ የመንግስቱን ወንጌል ያለ ፍርሃትና ያለ ይሉኝታ ይዘን ልንገለጥ ግድ ይሏል ።
ይህን እሳቤ በማድረግ ቤተክርስቲያን በዚህ ዓዲስ ዓመት መባቻ ሰፊ የአገልግሎት መርሃ ግብር ዘርግታ በጸጋ የዳነ ሁሉ የአገልግሎት መክሊት አለው በሚል መረዳት ሁሉንም የአካል ክፍል በየጸጋው ለማሰማራት ቅድመ ዝግጅቷን አጠናቃለች ፡፡ ስለዚህ ከእግዚአብሔር የተቀበልነውን የወንጌል አደራ በተጠራንበት ቦታና ጸጋ ተሰልፈን አካሉን እንድናንጽ የታላቁን ተልኮ ጥሪ እንድንወጣ በአክብሮት ጥሪዬን አስተላልፋለሁ ። ማራናታ አሜን ጌታ ኢየሱስ ሆይ ቶሎ ና ! መልካም አዲስ ዓመት !
መካሻው ሽመላሽ ይግዛው ( መጋቢ )
7