AddisLidet 2017 - Page 6

የአዘጋጆች መልእክት
ይህንን መጽሔት በአጭር ጊዜ ለማዘጋጀት ሕልማችንን እውን እንዲሆን የረዱንን ወገኖች በሙሉ በፈረንጅኛው ከልባችን ጫፍ ፣ በሐገርኛው ካንጀታችን ፣ በአራድኛው ከምር እናመሰግናለን ፡፡ በተለይ ጽሑፎችን በማበርከት ፣ በአስተያየትና በድጋፍ የተባበረችሁንን ሁሉ በጸሎት ጊዜ ፓስተሮች ፣ በጉዞ ጊዜ ሆስቴሶች ፣ ባደጋ ጊዜ ፖሊሶች ፣ በድግስ ጊዜ በላተኞች ፣ በፈተና ጊዜ መምህሮች ይተባበሩአችሁ ፡፡ የአሁን ድጋፋችሁ ለወደፊትም የስራ እምነት ሆኖናልና እንደደገፋችሁን በአበው ምርቃት የማታ ድጋፍ አትጡ ብለናል ፡፡ ይህ መጽሔት ለቤተክርስቲያናችንና ለአዘጋጁ ክፍል የመጀመሪያ አዝመራ እንደመሆኑ አንባቢ ፍሬውን ቀምሶ አስተያየቱን እንደሚሰጠን ተስፋችን ነው ፡፡ እንደወጋችን ደሞ የደገሰውን ሲበሉለት የወለደውን ሲስሙለት ደስ የማይለው የለምና ብሉልን ፣ ሳሙልን ብለን በሰፋፊ ወረቀት እነሆ ብለናል ፡፡
አዘጋጆች ፣ ዶ / ር አዳም ቱሉ እህት ሩት ( ቹቹ ) መንግስቱ እህት እናትዓለም ( እናት ) ኤጀርሳ
ከቤተክርስቲያኗ የፎቶ ማህደር
6