AddisLidet 2017 | Page 5

3 . የውሃ ጥምቀት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትዕዛዝ መሠረት አማኝ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም በውሃ እንደሚጠመቅ እናምናለን ፡፡ ማቴ 28 ፡ 19 አንድ ክርስቲያን ለዚህ ዓለምና ለኃጢአት የሞተ ፣ ለፅድቅ ደግሞ ህያው መሆኑን በእግዚአብሔርና በቅዱሳን ፊት የሚያረጋግጥበት ምሳሌያዊ ተግባር መሆኑን ታምናለች ፣ በዚሁም መሠረት የአዋቂ ጥምቀትን በተግባር ታውላለች ፡፡ ሮሜ 6 ፡ 1-7 ፤ ማር 16 ፡ 16 ቤተክርስቲያንዋ በምታዘጋጀው ትምሕርት መሠረት የውሃ ጥምቀት ይከናወናል ። ሮሜ6 ፡ 1-7
4 . ቅዱስ ቁርባን በህብስትና በወይን ጭማቂ የሚዘጋጀውን ቅዱስ ቁርባን ፣ የጌታችን የመድኃኒታችን ስቃይና ሞት የምናስብበትና ሞቱንም የምንናገርበት ቅዱስ ሥርዐት መሆኑንና ስለዚህም ጌታ እስኪመጣ ድረስ በቤተ ክርስቲያን መከናወን ያለበት መሆኑን እናምናለን ፡፡ ማቴዎስ 26 ፡ 26-28 ፣ 1ቆሮንቶስ 11 ፡ 23-30
5-ቅድስና የክርስቲያኖች ጥሪ ለእግዚአብሔር ቃል በመታዘዝና በቅድስና ማለትም በእግዚአብሔር ቃል መሰረት የተለየና ከሃጢያት የፀዳ ሕይወትን በመለማመድ መንፈሳዊ ፍሬ ማፍራትና ምሳሌነት ያለው ህይወት በመኖር ኢየሱስ ክርስቶስን ከፍ ማድረግ እንደሆነ እናምናለን ፡፡ ኤፌሶን 2 ፡ 10 ፣ 1ጴጥሮስ 1 ፡ 15 ፣ 2ቆሮንቶስ 7 ፡ 1 ፣ ዮሐንስ 15 ፡ 1-11 ፣ 1ጢሞ4 ፡ 12
6-የክርስቶስ ዳግም ምፅአት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በክብር እንደገና እንደሚመጣ ፣ በእርሱ አምነው የሞቱት ቀድመው እንደሚነሱ ሕያዋን የሆኑት ደግሞ እርሱን ለመቀበል እንደሚነጠቁ እናምናለን :: 1ቆሮንቶስ 15 ፡ 51-52 ፣ 1ተሰሎንቄ 4 ፡ 15-17
7-ፍርድ ጻድቃን ከጌታ ጋር ለዘላለም እንደሚኖሩ ኃጢአተኞች ግን ከእግዚአብሔር ፊት ተለይተው በገሃነም እሳት ለዘላለም ተፈርዶባቸው እንደሚሰቃዩ እናምናለን ፡፡ ራዕይ 7 ፡ 9-15 ፣ 19 ፡ 11-14 ፣ ሉቃስ 13 ፡ 23-30 ፣ ማቴዎስ 25 ፡ 31-46 ፣ ራዕይ 20 ፡ 10-15 ፣ ማቴዎስ 24 ፡ 38-44 ፣ 25 ፡ 1-13 ፣ ዮሐንስ 14.2-4
8-ቤተክርስቲያን ቤተክርስቲያን የክርስቶስ አካል እንደሆነች በዚህ ምድር ታላቁን ተልዕኮ ለመፈጸም እና የእግዚአብሔርን መንግስት እንድትወክል ስልጣንና ኃላፊነት የተሰጣት እርሷ እንደሆነች እናምናለን ፡፡ ማቴዎስ 28 ፡ 19-20 ፤ ማቴዎስ 16 ፡ 18 ፤ ኤፌሶን 1 ፡ 22-23 ፤ ኤፌሶን 2 ፡ 20 ፤ 1 ጴጥሮስ 2 ፡ 5
9-መጽሐፍ ቅዱስ 66 / ስልሳ ስድስት / መጽሐፍት ያለው መጽሐፍ ቅዱስ ያለ ስህተት የተጻፈ የእግዚአብሔር ቃል እንደሆነ እና የመዳን ዕውቀት ፣ ለጽድቅ ኑሮ መምሪያን በመስጠት ፣ ለሚነሱ የትኛውም ክርክሮችና አስተምህሮዎች የመጨረሻው ወሳኝ ይህ የእግዚአብሔር ቃል እንደሆነ እናምናለን ፡፡ ዕብራውያን 4 ፡ 12 ፤ 2 ጢሞቴዎስ 3 ፡ 16 ፤ መዝሙር 119 ፡ 105 ፤ ማቴዎስ 24 ፡ 35 ፤ ዮሐንስ 1 ፡ 1
5