AddisLidet 2017 | Page 34

የአዲስ ልደት ዓለምአቀፍ ቤተክርስቲያን ራዕይ ፤ ተልዕኮ እና የትኩረት አቅጣጫዎች / ግቦች /

የአዲስ ልደት ዓለምአቀፍ ቤተክርስቲያን ራዕይ ፤ ተልዕኮ እና የትኩረት አቅጣጫዎች / ግቦች /

ራዕይ መልካሙን የምስራች ሰምተው በኢየሱስ ክርስቶስ አምነው የዳኑ ፤ በመንፈስ ቅዱስ የተሞሉ ፤ በእግዚአብሔር ቃል ዕውቀት የታነጹ ፤ የጽድቅ ጦር ዕቃ የታጠቁና ለእግዚአብሄር ፈቃድ እና ለመንግስቱ መስፋት ዕለት ተዕለት በመሰጠትና በመስዋዕትነት የሚኖሩ እውነተኛ የእግዚአብሔር ህዝብ ማየት ። ተልዕኮ የኢየሱስ ክርስቶስን የመንግስት ወንጌል በመንፈስ ቅዱስ ሀይል ላላመኑት በመስበክ ወደ ደህንነት ማምጣት እና ያመኑትን ደግሞ በማስተማር እውነተኛ የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዝሙርትና አገልጋዩች እንዲሆኑ በማድረግ የእግዚአብሔርን መንግስት ማስፋት ። የትኩረት አቅጣጫዎች / ግቦች / * እግዚአብሔርን በእውነት እና በመንፈስ ማምለክ * ወንጌል ላልደረሳቸው ህዝቦች ወንጌልን ማድረስና የእግዚአብሔርን መንግስት ማስፋት * የዳኑትን እውነተኛ የክርስቶስ ኢየሱስ ደቀመዛሙርት ማድረግ * የምዕመናንን ህይወት ፤ ህብረትና አንድነት መገንባትና ማጐልበት * ቤተሰብን በሁሉም አቅጣጫ ማጐልበትና ማጠንከር * ተተኪ መሪዎችና አገልጋዩችን ማፍራትና ማሰማራት * በቤተክርስቲያኒቱና በህብረተሰቡ መካከል ያሉ ችግረኞችን በሁለንተናዊ መልኩ በመደገፍና
በመንከባከብ በዘላቂነት ራሳቸውን እንዲችሉ የሚያደርግ አቅም መፍጠር
34