AddisLidet 2017 | Page 32

የታዳጊ ወጣቶች አገልግሎት
የታዳጊ ወጣቶች አገልግሎት እድሜያቸው ከ12 አመት በላይ የሆኑ ደሕንነት ከሚማሩ ልጆች ጀምሮ መሰረታዊ የደህንነት ትምህርት ተምረው የውሐ ጥምቀት የወሰዱ ወጣቶችን የሚያገለግል የቤተክርስቲያኒቱ የአገልግሎት ዘርፍ ነው ፡፡ ይህ አገልግሎት እንደ ንኡስ ራእይ በቤተክርስቲያኒቱ መሪዎች ተቀባይነትን ካገኘ ከ2013 ዓ . ም ጀምሮ ለ45 ወጣቶች የደህንነት ትምህርትን አስተምሮ የውሐ ጥምቀት ያበቃ ሲሆን ከእነዚህ ወጣቶች መሐከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑት የደቀመዝሙር ትምህርት እየተማሩ በጌታ ጸጋና በቃሉ እውቀት እንዲያድጉ እየሰራ ያለ አገልግሎት ነው ፡፡ አገልግሎቱ ዘወትር አሁድ ከ 10 ፡ 30 A . M እስክ 11 ፡ 30 A . M ድረስ የደቀመዝሙር ትምህርትና የደህንነት ትምህርት በተለያዩ ክፍሎች የሚያስተምር ሲሆን ፣ ዘወትር ቅዳሜ ከሰአት በሁዋላ ከ5 P . M እስከ 7 P . M ድረስ ደግሞ የዝማሬ የድራማና ልዩ ልዩ ወቅታዊ ፕሮግራሞችን ለወጣቶቹ ያከናውናል ፡፡ የታዳጊ ወጣቶች አገልግሎት በኖቬምበር 5 ለግማሽ ቀን “ ፕሮጀክት ዮሴፍ ” በሚል ርእስ በተደረገው ልዩ ፕሮግራም ቁጥራቸው ከ30 በላይ ለሆኑ የጎዳና ተዳዳሪዎች ወንጌልን በመስበክ ፣ ምግብ በማብላትና ልብሶችን በመስጠት የክርስቶስን ፍቅር ለማካፈል ተችሎአል ፡፡ ቤተክርስቲያንም ፕሮጀክቱን ሲመሩ ለነበሩ አራት ታዳጊ ወጣች የምስክር ወረቀት የሰጠች ሲሆን በቀጣይም ተመሳሳይ ስራዎችን ለመከወን አቅደናል ፡፡ በዚህ አገልግሎት ውስጥ ለማገልገል የምትወዱ ወገኖች ( 301 ) 728 5345 በመደወል አስተባባሪዎችን ያነጋግሩ ፡፡
በእለቱ ወንጌል የሰሙ ጎዳና ተዳዳሪዎቸ በከፊል
የወጣት ጎልማሳ ህብረት
ህብረቱ ቀን ሳለ የላከኝን ሥራ ላደርግ ይገባኛል ፤ ማንም ሊሠራ የማይችልባት ሌሊት ትመጣለች ።” በሚለው ዮሐ 9:4 መሰረት በእግዚአብሄር ጊዜ ፤ ፈቅድና አላማ መሰረት በማርች ወር 2016 ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ወጣት ተኮር የሆኑ ዘርፈ ብዙ ፕሮግራሞችን በማካሄድ ላለፉት 9 ወራትን በርካታ ፍሬዎችን አፍርቶአል ። የህብረቱ አላማ በዋነኝነት በቤተክርስቲያኒቷ እንዲሁም በሌሎች አብያተ ክርስቲያናት ያሉ ወጣቶችን በመሰብሰብ የእግዚአብሄርን ቃል በመመገብና አብሮ እግዚብሄርን በማምለክ በህይወትና በአገልግሎት የተመሰከረለት ወጣት ማፍራት ነው ። በተጨማሪም ወንጌልን ለሌሎች በማዳረስ ለክርስቶስ ደቀመዛሙርት ማፍራት ነው ። ይህንንም ራእይ ለማሳካት ዘወትር እሁድ ከ6 ፡ 30PM ጀምሮ ሳምንታዊ የአምልኮና የፌሎሺፕ ጊዜ እናደርጋለን ፡፡ በወር አንድ ጊዜ ለየት ያለ ፕሮግራሞች እንዲሁም በአመት ሁለት ጊዜ ወጣቶችን ያማከለ ትምህርታዊ ኮንፍራንሶችን እናደርጋለን ። በዚህ አገልግሎት ውስጥ ለማገልገል ሸክሙና ፍላጎቱ ያላችሁ ወገኖች አስተባባዎችን ያነጋግሩ ፡፡
32