AddisLidet 2017 | Page 31

የጀማ የወንጌል
በእግዚአብሔር እርዳታ ባሳለፍነው ዓመት ከአምልኮ ፣ ጸሎትና ሌሎች ቁዋሚ ፕሮግራሞች ባሻገር በሲልቨር ስፕሪንግ እና በቨርጅንያ አጥቢያዎች የጀማ የወንጌል ስርጭት የተደረገ ሲሆን በዚህ ፕሮግራም ከአንድ ሺ ህዝብ በላይ የተለያዩ ሐገር ዜጎችን በአማርኛ በእንግሊዘኛና በፈረንሳይኛ ቁዋነቁዋዎች የኢየሱስ ክርስቶስን አዳኝነት የምስራች ሰምተዋል ። ከነዚህም መሐከል ሰላሳ ሰዎች ጌታን የግል አዳኛቸው አርገው ተቀብለዋል ። ይሄ አገልግሎት ለአገልጋዮችና ለቤተክርስቲያን መልካም ጅማሬ ከመሆኑም በላይ ቤተክርስቲያን ወደተጠራችበት ቀዳሚ አላማዋ የሚመልስ የተስፋ ጎህ ያየንበት ስለሆነ በቀጣዩ የአዝመራ አመት ታምነን ወንጌልን ለፍጥረት ሁሉ ለማዳረስ ( ለመዝራት ) ስልቶችን እንተልማለን ፡፡
የደህንነት ትምህርትና የውሀ ጥምቀት ፡ -
በቤተክርስቲያናችን በጌታ እርዳታ ከተሰሩት አበይት ክንውኖች አንዱና ዋናው አዲስ ጌታን የተቀበሉ ወገኖችን ተከታታይ የደህንነት ትምህርት አስተምሮ ለደቀመዝሙርነት ማብቃት ነው ፡፡ ባሳለፍነው 2016 ዓ . ም 18 መሰረታዊ የደህንነት ትምህርት የተማሩ ወንድሞችና እህቶች በጁላይ ፣ 2016 የውሐ ጥምቀት ስርአት ድርገው ወደቤተክርስቲያን ሕብረቶች ተቀላቅለዋል ፡፡
31