AddisLidet 2017 | Page 30

የቤተክርስቲያን አገልግዮች ጠቅላላ ሪተሪት ፕሮገራም
በክላርክስበርግ , ሜሪላንድ ከተማ በሚገኘው የሕዝብ መዝናኛ ስፍራ በተደረገው የሙሉ ቀን የአገልጋዮች ሪትሪትና የምስጋና ጊዜ ቁጥራቸው ከአርባ የሚበልጡ አገልጋዩች የተገኙ ሲሆን በእለቱ የእግዚአብሔርን ቃል ከመካፈልና አብሮ ከማምለክ ባሻገር የተለያዩ ጨዋታዎችን በመጫወት ለቀጣዩ ዘመን ስራ በመምከር መልካም ጊዜን አሳልፈናል ፡፡
የአገልጋዮች ስልጠና
የአንድ አጥቢያ ቤተክርስቲያን እድገትና ስኬት የሚለካው ባላት ገንዘብና ሕዝብ ቁጥር ሳይሆን አባላቶች ባላቸው እውነተኛ ደቀ መዝሙርነት ልክ እንደሆነ ይታወቃል ፡፡ በቤተክርስቲያናችንም በተደጋጋሚ በተደረገ የአገልግሎትና የደቀመዝሙርነት ስልጠና በርካታ ወገኖች ተካፋይ ሆነዋል ፡፡ ለቀጣዩም አገልጋዮችን በወንጌል ለማስታጠቅና የቤተክርስቲያናችንን አባላት በሙሉ መሰረታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ እውቀት እንዲኖራቸው በታለመ የረጅም ጊዜ መርሐ ግብር መሰረት ከጀንዋሪ 2017 ዓ . ም ጀምሮ የአዲስ ልደት የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ቤት እንከፍታለን ፡፡ በመጀመሪያው ዙር የትምህርት መርሐ ግብርም ከ20 እስከ 25 የሚሆኑ ወገኖችን በሰርቲፊኬት ለማስመረቅ ዝግጅቶችን አያጠናቀቅን እንገኛለን ፡፡
30