AddisLidet 2017 | Page 26

ስለዚህም እኔም ባለቤቴም ሐዘንተኞች ሆንን ፣ የተቀበሉንም ወገኖች ኑሮው ስለከበዳቸው ፊታቸው እየተለወጠብን መጣ ፡፡ ሰናይትም ጠዋት ማታ ማልቀስ ስራዋ አደረገችው ፡፡ ይህ የጨለማ ጊዜ ቢሆንም ጨለማው ያላሰብኩትንና ያልገመትኩትን ብርሀን ይዞ መጣ ፡፡
ይህ ብርሀን የስራ በር ነው ወይስ የስጋ ፈውስ ያመጣልህ ? እኔም ባለቤቴም ስራ ስለሌለን እኔም አቤት ከመቀመጥ አያልኩኝ በአቅራቢያዬ የሚገኘው የአዲስ ልደት ቤተክርስቲያን ፕሮግራሞች መካፈል ጀመርኩኝ ፡፡ ፕሮግራም የምካፈለው መሔጃ ስለሌለኝና ቸርች ስሔድ አንጻራዊ ሰላም ስለማገኝ እንጂ ቃሉን ናፍቄ ወይ ጌታን ፈልጌ አልነበረም ፡፡ ያም ሆኖ ግን የምሰማቸው ስብከቶችና ዝማሬዎች ሳላውቀው ደንዳናውን ሌቤን እየሸረሸሩት ነበር ፡፡ ያለስራ በሆንኩበት ወቅት የታክሲ ፈቃድ አውጥቼ በሴፕተምበር 2009 ዓ . ም . ታክሲ መንዳት ጀመርኩኝ ። ስራውን እየለመድኩትና ገንዘብ እያገኘሁኝ ስመጣ በጀንዋሪ 2010 ዓ . ም . የራሳችንን አፓርትመንት ተከራይተን ብንወጣም ራሴን በስራ ጠምጄው ቤተክርስቲያን መምጣቴን አቆምኩት ፡፡ በኦገስት ወር 2011 ዓ . ም . አካባቢ ለኔ ብዙ የምለውን በሕይወቴ ያልነበረኝን ያህል ገንዘብ ማስቀመጥ ስለቻልኩኝ ታክሲ መንዳቴን ትቼ ንግድ ለመጀመር ፈለኩኝና ስራውን ቀነስኩት ፡፡ በዚህ ጊዜ ለንግድ የሚሆን ስፍራ እያፈላለኩኝ በእረፍት ጊዜ በድጋሚ ወደ ቤተክርስቲያን የተመለስኩትና ሕይወቴን ለጌታ የሰጠሁት ፡፡
እስቲ እንዴት ጌታን እንዳገኘህ አጫውተን ፡ የታክሲውን ስራ በቀነስኩበት ወቅት ሰፊ የእረፍት ጊዜ ስለነበረኝ ከባለቤቴ ጋር ቤተክርስቲያን በመመላለስ የተለያዩ ፕሮግራሞችን መካፈል ቀጠልኩ ፡፡ ከሁሉም የማልረሳው በአንድ ምሽት ፓስተር ቢኒያም ኢታና ሲያገለግል አንድ ሰው በሀዘን ሆኖ የጸሎት ርእስ አቀረበ ፡፡ ጸሎቱም “ ከስራ ተባረርኩኝ ነገር ግን በባንክ ያለኝ ሐያ ሺህ ዶላር ብቻ ስለሆነ ግራ ገብቶኛልና እባክህ ጸልይልኝ ” የሚል ነበር ፡፡ ፓስሩ ደግሞ በወቅቱ የነበረው $ 300 ዶላር ብቻ እንደነበረ ተናገረና “ ከገንዘብ ብዛት አኩዋያ
ከሁለታችን ማነው ጸሎት የሚያስፈልገው ?” ብሎ ጠየቀ ፡፡ ፓስተሩ ቀጥሎ “ እኔ በትንሽዋ ገንዘብ ውስጥ እርካታና ሙሉ የሆነ የውስጥ ሰላም አለኝ ” ሲል በዚህ መልእክት ውስጥ እርካታና ማረፍ በገንዘብ እንዳልሆነ ትልቅ ነገር ገባኝ ፡፡ አሁን አለኝ ብዬ ስራዬን እስከመቀነስ የወሰንኩበት ገንዘብ የምፈልገውን እርካታና ሰላም እንደማይሰጠኝ ተረዳሁኝ ፡፡ በአንጻሩ ደግሞ ያለምንም ገንዘብ ጌታ አረጋግቶ ማኖር እንደሚችል ተረዳሁኝና በዚያን እለት ሕይወቴ ተለወጠ ፡፡ እኔም በምችለው ሁሉ ከቤተክርስቲያን ላለመቅረት ወሰንኩኝ ፡፡ አንድ መጨመር ያለብኝ ነገር እኔን ጌታ እያባበለ ወደቤቱ አምጥቶ በፍቅሩ ማረከኝ እንጂ ማንም ሰው ስለጌታ በግል መስክሮልኝ አያውቅም ፡፡ ባለቤቴ ጌታን ተቀብላ ከመጣች በሁዋላ ባልቃወማትም ስለ ጌታ ነገር ግን በቁም ነገር አውርተን አናውቅም ነበር ፡ አሁንም አኔ በሚገባኝ መልክ ነፍሴ ለዘላለም ድና ስትቀር እስኪታወቀኝ ድረስ በግሌ ወሰንኩኝ እንጂ ማንም ሰው ንሰሐ አላስገባኝም ነበር ፡፡ ሐጢያቱንም ንስሐውንም ራሴው ነኝ የጨረስኩት ማለት ይቻላል ፡፡
ስለደህንነት ትምህርትህና ቀጣይ ሕይወትህ እስቲ ንገረን ይህንን ውሰኔ በግሌ ከወሰንኩኝ በሁዋላ በሕይወቴ ብዙ ለውጦች ሆኑ ፡፡ ለምሳሌ በዲሴምበር 31 , 2011 በነበረው የአዲስ አመት ዋዜማ ፕሮግራም ላይ ለመካፈል ሔጄ ነበር ፡፡ በእለቱ ከሰዎች ጋር ግብዣ ነበረኝ ፡፡ የታክሲ ስራውም በእጥፍ የሚገኝበትን ምሽት ስለነበረ ለማንም ታክሲ ነጂ የሚያጉዋጉዋ ነበር ፡፡ እኔ ግን ለምን እንደሆነ ባላውቅም በምሽቱ ወደ ቤተክርስቲያን መሔድ ፈለኩኝ ፡፡ በፕሮግራሙ ላይ ተጋባዥ አገልጋይ የነበረው ፓስተር መካሻው አጭር ቃል ካካፈለን በሁዋላ እጅ ለእጅ ተያይዘን ስንጸልይ በመንፈስ ቅዱስ ተሞላሁኝና ራሴን መሬት ላይ ወድቄ አያለቀስኩኝ በልሳን ስጸልይ አገኘሁት ፡፡ ይህች ቀን ለእኔ ወደማልመለስበት አቅጣጫ የዞርኩበት ደስታዬን እጥፍ ወዳደረገው የጌታ ልጅ መሆን ያረጋገጥኩበት ቀን ሆነችኝ ፡፡
26