AddisLidet 2017 | Page 24

የወንድም ኤርሚያስ የሕይወት ምስክርነት

በዚህ ልዩ እትም የወንድማችንን ኤርሚያስ ቦሾና የቤተሰቡን የሕይወት ምስክርነት ይዘን ቀርበናል ፡፡ ለቀጣዮች አዲስ ልደት መጽሔት እትሞች ለወገኖች የሚጠቅም ምስክርነት ያላችሁ የመጽሔት አዘጋጅ ክፍሉን ያነጋሩ ፡፡
ስምህንና የልጅነት ሕይወትህ እስቲ ንገረን ስሜ ኤርሚያስ ያደኔ ቦሾ እባላለው ፡፡ የተወለድኩትና ያደኩት በአዲስ አበባ ከተማ ሲሆን የልጅነት ሕይወቴን መራርና ሀዘን የተቀላቀለበት ነበር ፡፡ በልጅነቴ ወላጅ እናቴና አባቴ ስለተለያዩና አባቴ ሌላ ሚስት ስላገባ ወላጅ እናቴ ቤቱን ጥላ ወጣች ። እኔም ከአባቴ ጋር እንድቀርና በእንጀራ እናት እጅ ማደግ እጣ ፈንታዬ ሆነ ፡፡ አባቴ ባለው ባሕሪና ግዴለሽነት ለልጆቹ ተገቢውን ክትትልና የወላጅ እንክብካቤ ማድረግ ካለመቻሉ በላይ በአባቴ ዘር የሚመለከው የ “ አመቺሳ ” ባእድ አምልኮ የልጅነት ሕይወቴን መራር አድርጎት ነበር ፡፡ ለምሳሌ በእኔ እድሜ ያሉ ልጆች ላይ ከሚደርሰው በላይ ብዙ ጊዜ ከፍተኛ መፈንከት ፣ ስብራትና የተለያዩ ሕይወቴን ላደጋ የሚያጋልጡ አደጋዎች ገጥመውኛል ፡፡ በሰውነቴ ላይ ያሉ ትልልቅ የቁስል ጠባሳዎች እስከዛሬ ድረስ እንደመረጃ አሉ ፡፡ የትምህርትና የወጣትነት ሕይወትህ ምን ይመስል ነበር ? የመጀመሪያ ደረጃና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን በዚሁ የሕይወት ውጣ ውረድ ስለገፋሁበት በጉርምስና እድሜዬ ያለመካሪና ያለገላጋይ ሁሉንም የጥፋት አይነቶች መራራ ጽዋ አንድ በአንድ ቀመስኩት ፡፡ ገና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ሆኜ ጫት መቃም ፣ መጠጣት ፣ ማጨስ ዝሙትና የመሳሰሉትን ሳደርግ የሕሊናም ሆነ የወላጅ ወቀሳ አይደርስብንም ነበር ፡፡ በዚሁ እድሜ ክልል ውስጥ ሊገድለኝ የሚችል ከሰዎች ጋር መደባደብና ብዙ ጊዜ የመኪና አደጋዎች ገጥመውኛል ፡፡ የማልረሳው በአንድ ወቅት ሰዎች በሀይል ደብድበውኝ ሞቶአል
ብለው ጥለውኝ እንደሔዱ አስታውሳለው ፡፡ ነገር ግን ለራሴም ሳይገባኝ ሕይወቴ ቀጠለ ፡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን ከጨረስኩኝ በኃላ በ1997 ዓ . ም . ከዲላ ከተማ እስከ ሞያሌ በተለያዩ ስፍራዎች በሚገኘው የአባቴ የመጠጥ ማከፋፈያ ውስጥ በአሻሻጭነት ለመስራት ተቀጥሬ ከተወለድኩባትና ካደኩበት አዲስ አበባ ከተማ ወደዲላ ኑሮዬን አቀናሁ ፡፡ ምንም እንኳን የመኖሪያ ስፍራ ለውጥ ባደርግም ሕይወቴ ግን በተመሳሳይ ሁኔታ ስለቀጠለ የመኖር ትርጉምና ለነገ የሚባል ተስፋ አልነበረኝም ፡፡
የትዳር ሕይወትህ እንዴት ተጀመረ ? በዚሁ በምኖርበት የዲላ ከተማ እየኖርኩኝ ባለሁበት ተመሳሳይ የሆነ የዘቀጠ ሕይወት ውስጥ እያለሁኝ ነበር ለሕይወቴ መሰረታዊ ለውጦች ምክንያት የሆነችውን ባለቤቴን ሰናይት መለሰን የተዋወቅኩት ፡፡ ከሰናይት ጋር ጥቂት በጓዋደኝነት ከቆየን በኃላ ተጋብተን አብረን መኖር ጀመርን ፡፡ ነገር ግን ትዳር መመስረቴ አሰልቺ የነበረውን ሕይወቴን ስላልለወጠው ሁሉም ነገር ባለበት ከመቀጠሉ በላይ ባለቤቴንም በዚሁ የውድቀት ሕይወት ውስጥ ተካፉይ አደረኳት ፡፡ ትዳር መስርቶ ከመኖር ባለፈ በህይወቴ ላይ ምንም መሰረታዊ ለውጥ ባልነበረበት በዚሁ ዘመን የመጀመሪያ ልጃችንን ኤማንን ወለድን ፡፡ ነገር ግን ልጃችን ኤማ በልጅነትዋ ፊትዋን የሚያሳክክና ሰውነትዋን የሚያሳብጥ ተደጋጋሚ ህመም ሲኖራት በሐኪም በኩል ለማዳን ያደረግነው ሙከራ ተስፋው እየመነመነ መጣ ፡፡ አንዳንዴ ያሳክካታል ፣ ሌላ ጊዜ ፊትዋ ያብጣል ፣ ሌላ ጊዜ ሌላ ይሆናል ፡፡ በዚህ መሀል ወላጅ
24