AddisLidet 2017 | Page 23

ጀግና
Business Name

የዘመን ሽወዳ

አመቱ አልቆ ሌላ ሲመጣ ፣ ባዲሱ አመት ህዝቡ ሲወጣ ፣ የተውጣጣው ህዝብ እቅድ አቅዶ ፣ በቅዶቹ ላይ ዘመቻ ወርዶ ፣ ከዘመቻ መልስ ስራውን ሲያየው ፣ የገዛ ሰራው እ .... ጅግ ኣኮራው ። የራሱ ትጋት በጣም ኣርክቶት ፣ በዘመኑ ላይ ተሳለቀበት :: ከተኩራራው ህዝብ በኣጋማሹ ፣ እረፍት ኣማረው ትልቅ ትንሹ :: በመኝታው ላይ ትንሽ ተጋድሞ ፣ ህልሙን ጨርሶ ቢነሳ ደግሞ ፣ ለካ ዘመኑ ኣልደከመውም ፣ ከእነረሱ ጋር ኣብሮ ኣልተኛም :: በትንሽ እረፍት የቀደማችው ፣ ቀጣዩ ዘመን ፍዳ አበላቸው :: ፍዳ መብላቱ ቢያንገፈግፈው ፣ አዲሱን ዘመን በጣም ወረፈው :: ያላፊ ኣግዳሚ ሩጫ ኣየና ፣ አወዳደረው ዛሬን ካቻምና :: “ የድሮ ዘመን በጣም ይሻላል ፣ እንበላ ነበር ያምስት ብር ፍየል :: ከዚህ ዘመን ጋር ቆሞ ሲለካ ፣ ስሙኒ ነበር ቡትሌ ኮካ :: ዛሬ ጊዜማ በጣም ይገርማል ! የፍየል ሌጦ ሀምሳ ብር ገብቷል :: የኮካ ጠርሙስ ምንም ሳይጨምር ፣ ቁራሌው ገዛው በሶስት ድፍን ብር ::” እንዲህ እያለ እርሱ ሲዛበት ፣ አዲሱም ዘመን ስቆ አለፈበት ።
ዶ / ር አዳም ቱሉ

ጀግና

ከካሌብ አብርሃ ( ቴዲ ) አልታይህ ቢለው ቃል-ዓባይ ቢታወር ደረት እየደቃ ሙሾ ቢደረድር ይታመናል እንጂ እውነት አይፈጠር ይታመናል እንጂ እውነት አይፈጠር ! ጀግና ... ጀግናማ ሞትን ገደለ በሞቱ ሞትን ሰቀለ ጨከነ በራሱ ማለ ከፅልመት ጋራ ታገለ ፋናስ መቅረዙን ተከለ ።
23