AddisLidet 2017 | Page 19

መጠኑ በዚያን ጊዜ እንጀራ ቀርቶ መሬት እንኩዋ የሚገዛበት ብር እንደነበረ ከቃሉ መረዳት እንችላለን ፡፡ ጌታውን የሸጠበትን ገንዘብ በቤተ መቅደስ ሄዶ በተነ ፤ ነገር ግን መሬት ገዙበት ፤ ቦታውም አኬልዳማ ተባለ ፤ የተባለው ነገር ነው ፡፡ እንግዲህ 30 ዲናር በጊዜው እንዲህ ትልቅ ከነበረ ፡ 200 ዲናርማ ምን ያህል ይሆናል ? የፊሊጶስ ሒሳብ ለሰው አዕምሮ ትክክል ይመስላል ፡፡ በሺዎች የሚቆጠሩትን ለመመገብ ይህን የሚያክል በጀት አስፈላጊ ነው ማለቱ ፡፡
ለ . ራዕዩን በእጅ ላይ በተገኘው ትንሽ ነገር መጀመር ......? በቁ . 9 ላይ እንድርያስ ''.. አምስት የገብስ እንጀራ እና ሁለት ዓሳ የያዘ ብላቴና በዚህ አለ ፤ ነገር ግን እነዚህን ለሚያህሉ ሰዎች ይህ ምን ይሆናል ፡፡ '' አለ ። ይህ ሁለተኛው የአማራጭ ሐሳብ ነው ፡፡ ገንዘብ ተፈላልጎ ፡ አልያም በሆነ መንገድ ከሚገኝ ገቢ መጀመር የማይቻል ከሆነ ፡ ምናልባት እጃችን ካለው ጥቂት ነገር መጀመር ሊያስፈልግ ይችላል ፡፡ ነገር ግን እጃችን ላይ ያለው ነገር ለምንም ካልሆነስ ? ነው ጥያቄው ፡፡ ፐሮጀክቱ ያቀፈው ህዝብ በሺህ የሚቆጠር ፣ በእጃቸው ያለው መነሻ ካፒታል ደግሞ ለአንድ ለሁለት ሰው ብቻ የሚበቃ ፡፡ እንድርያስ ' ይህ ምን ይሆናል ? ' ያለው ለዚያ ነው ! በርካታ ራዕዮችና ውጥኖች ሳይሰራባቸው ተቀምጠው ያሉት በነዚሁ ሁለት ግዙፍ ጥያቄዎች ውስጥ ወድቀው ነው ፡፡ መነሻ ካፒታል ሲታሰብ ፣ ለመነሻ የሚሆን ብር ሲጠበቅ አይሞላም ፡፡ ስለዚህም ፈቀቅ ማለት አይቻልም ፡፡ ቤሳ ቤስቲ የሌላቸው ሰዎች ከመሬት ተነስቶ 200 ዲናር ከየት ያመጣሉ ? ሌላው ደግሞ እጃችን ላይ ያለው ነገር ለምንም የማይበቃ መሆኑ ነው ፡፡ በተለይም ከታሰበው ራዕይ ጋር ሲነጻጸር ማለቴ ነው ፡፡ ጀምሩት ቢባል እየቆረሱ ድንገት ቢያልቅስ ? ፣ ጀምሮ መዋረድ አይሆንም ? አዕምሮ ያለው ሰው ይህንን ሊያደርግ ይችላልን ? ስለዚህም ነው በሁለቱም ጎራ የተነሱት ሐሳቦች ብዙዎቻችንን ይወክላሉ ብዬ የማምነው ፡፡ ሁለቱም ነገሮች ከባባዶች ናቸው ፡፡ ሙሉ
የፐሮጀክቱን መነሻ ካፒታል ማግኘትም ቀላል ነገር አይደለም ፡፡ ካላችሁ ነገር ጀምሩ ማለትም በሁዋላ ላይ የሚመጣውን መዘዝ በማሰብ የሚያንቀሳቅስ አይደለም ፡፡ በዚህ ሁሉ የጌታ ሐሳብ ለመሆኑ ምንድን ነው ?
የጌታ ሐሳብ “ ከየት ይገኛልን እንጂ በምን ይገኛልን አታስብ !“ የሚል ይመስላል ። ታስታውሱ እንደሆነ ሲጀመርም የጌታ ጥያቄ እንጀራ ከወዴት እንገዛለን ? ነው እንጂ በምን እንገዛለን ? የሚል አልነበረም ፡፡ ለጌታ በምን ? የሚለው አያስጨንቀውም ፡፡ ስለዚህም ነው በምን ? ን ትቶ ከየት ? የሚለውን የጠየቀው ፡፡ ሰው ደግሞ በምን ? የሚለው ሳይመለስለት ከየት ? ወደሚለው ቀጣይ ነገር ውስጥ መግባት አይፈልግም ፡፡ ስለዚህም ነው ሳይጠየቁ ሒሳብ መስራት የጀመሩት ፡፡ ለተሰጠ ራዕይ ሁሉ የሰው አስተሳሰብ ይኸው ነው ፡፡ በቅድሚያ እንዲመለስለት የሚፈልገው ነገር አለ ፡፡ ካልተመለሰለት በቀር መጀመር ይፈራል ፡፡ ጌታ ደግሞ እርሱን ለእኔ ተወውና ከየት እንደሚገዛ ንገረኝ ይላል ፡፡ በተለይ '' እራሱ ሊያደርገው ያለውን ነገር አውቆ ይህን አለ ፡፡'' የሚለው ቃል አስደናቂ ነው ፡፡ ምንም ወደ ሌላቸው ሰዎች ትልልቅ ራዕይ ሲያመጣ እርሱ አዋቂ ነው ፡፡ እርሱ ሊያደርግ ያለውን ነገር ስለሚያውቅ ነው ፡፡ በቅድሚያ በጀቱን ሰጥቶ ሂዱና ህዝቡን አብሉ !፤ ይህንና ይህን ስሩ ! ቢለን መልካም ነበር ፡፡ ነገር ግን ብዙ ጊዜ እንደዚያ አይሆንም ፡፡ ለመሆኑ ከእነዚህ ከሁለቱ ነገሮች ማለትም ፊሊጶስ ካቀረበውና እንድርያስ ካቀረበው ሐሳብ ጌታ የትኛውን መረጠ ? ወይም ምን አደረገ ? የሚለውን ነገር ከቃሉ ላይ አብረን እንመልከት ፡፡
ይቅጥላል ...
19