AddisLidet 2017 | Page 18

ራዕይ እንዴት ይጀመራል ?

ራዕይ እንዴት ይጀመራል ?

ቢንያም በፍቃዱ አቦዬ / መጋቢ /
ቤተክርስቲያን የተለያዩ ጸጋዎች የተሰጣቸው የወንድሞችና የእህቶች ስብስብ እንደመሆኗ አካልን ለማነጽና ለክርስቶስ መንግስት መስፋት እያንዳንዱ የተሰጠውን ጸጋ ለማካፈል ብሎም መክሊቱን ለማትረፍ ሊነሳሳ ይገባል ። መጪው አዲሱን ዓመትም ልክ የ42 ኪሎ ሜትሩን ረጅም ርቀት ሩጫ በአንድ ርምጃ እንደሚጀምሩት ሁሉ ወይም ከፊት ለፊት ብዙ ሰብል ለመሰብሰብ በእምነት ባዶ መሬት ላይ ዘርን እንደሚዘራ ገበሬ ከጥቂቷ ነገር ጀምረን ወደሰፊው ራዕይ ለማደግ የምንነሳሳበት አድርገን እንድንጠቀምበት እመነቴ ነው ። በእርግጥም በሁላችን ተሳትፎ አንድ ግዙፍና ትውልድን የሚጠቅም አዲስ ነገር የሚወለድበት ዋዜማ ላይ ያለን ያህል ይሰማኛል ። ቀጣዩ መልዕክትም የህይወት አጀንዳዎቻችንን በምን መልክ እና እንዴት ልንከውን እንደምንችል ፍንጭ ይሰጣል ብዬ አስባለሁ ። በዚህ ትምህርት ብዙዎቻችሁ የተቀበላችሁትን ራዕይ ከየት እና እንዴት እንደምትጀምሩ መርህን የምትማሩበት ፡፡ ወይም ደግሞ በህይወቴ አንድ ነገር ሰርቼ ማለፍ እፈልጋለሁ ፤ ግን ከየት እና ከምን እንደምጀምር አላውቅም ፤ ለምትሉ መንገድ መንገዱን ጠቁዋሚ ትምህርት ነው ብዬ አምናለሁ ፡፡ በቅድሚያ የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 6ን ቃል በጥሞና እንድታነቡ እጋብዛለሁ ። " ኢየሱስም ዓይኖቹን አንስቶ ብዙ ሕዝብ ወደ እርሱ ሲመጣ አየና ፊሊጶስን ፡ - እነዚህ እንዲበሉ እንጀራ ከወዴት እንገዛለን ? አለው ፡፡ ራሱ ሊያደርግ ያለውን ያውቅ ነበርና ፡ ሊፈትነው ይህንን ተናገረ ፡፡ ' ዮሐ . 6 ፤ 5-6 ። ከላይ እንደተጠቀሰው ጌታ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ መካከል ጥያቄ ሲጠይቃቸው እንመለከታለን ፡፡
‹ ህዝቡን ለማብላት እንጀራ ከወዴት እንገዛለን ?› የሚል ! በመሰረቱ እየመጣ የነበረው ህዝብ ፡ ወንዶች ብቻ ተቆጥረው 5ሺህ ህዝብ ነበሩ ፡፡ ሴቶችና ህጻናት ሲቆጠሩ 13 ሺህ ገደማ ይሆናሉ ተብሎ ይታሰባል ፡፡ ነገሩን እነዚህን ሁሉ የመመገብ የራዕይ ጅማሬ ብለን ልናስበው እንችላለን ፡፡ ራዕዩ ሲታይ በጣም ሰፊ እና ገና በሐሳብ ደረጃ ያለ ነገር ነው ፡፡ እነርሱም ማሰብ ጀመሩ ፤ ከየት ነው የሚጀመረው ? ሰዎች አንድን ራዕይ ለመጀመር ከሐሳብ ቀጥሎ የሚያነሱት ጥያቄ አላቸው ፡፡ እነዚያ ቅድመ ሁኔታዎች እስካልተሙዋሉ ድረስ ምንም ነገር መጀመር ሊከብዳቸው ይችላል ፡፡ የሚጠይቁዋቸው ወሳኝ የሆኑ ሁለት መሰረታዊ ጥያቄዎችን ፊሊጶስና እንድርያስ ጠይቀውልናል ፤ ወይም በራዕይ ጅማሬ ላይ ሊነሱ የሚገባቸውን ቁልፍ ሁለት አማራጭ ሐሳቦችን አንስተውልናል ፡፡ ቀጥለን እንዳስሳቸዋለን ፡፡
ሀ . ራዕይን ለራዕዩ የሚያስፈልግ ነገር ሲሙዋላ መጀመር ...? ፊሊጶስ ፡ - ቁ . 7 '' ፊሊጶስም እያንዳንዳቸው ትንሽ ትንሽ እንኩዋ እንዲቀበሉ የ 200 ዲናር እንጀራ አይበቃቸውም ብሎ መለሰለት ፡፡''፡፡ በዚያን ጊዜ ከጌታ የተሰጣቸውን አንድ ፕሮጀክት ወይም ራዕይ ለመጀመር የሚያስፈልገውን መነሻ ካፒታል ነው አስልቶ የተናገረው ፡፡ 200 ዲናር በጊዜው በጣም ብዙ ብር ነው ፡፡ ነገሩን የበለጠ ለመረዳት ያህል ፡ ጌታ ኢየሱስን አሳልፎ ለጠላቶቹ ለመስጠት ይሁዳ ከካህናት አለቆች ጋር የተደራደረበት ብር 30 ዲናር ነበር ፡፡
ይቅጥላል ...
18